የመነሳት ልምድ ያለው በመሆኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት መሞከር ከንቱ ልፋት ነው ብለዋል፡፡
እንደ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ገለጻ፣ የጠላቶችን ዓላማ መረዳት ካልቻልን እንደሀገር ጸንተን ለመቆም ያዳግታል፡፡ የኢትዮጵያ ጠላቶች መንግሥትን እወጋለሁ ሀገርን አፈርሳለሁ ለሚሉ አካላት የሎጀስቲክስ ድጋፍ ሰለሚያደርጉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የጠላቶቻችንን ዓላማ መረዳት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኅብረተሰቡ ከውጭም ከሀገር ውስጥም ከሚነሱ ጠላቶች ራሳቸውን መጠበቅና ሀገራቸውን ማስከበር እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡
አልሸባብ ላለፉት ዓመታት በሰሜንም፣ በምሥራቅም፣ በደቡብ ምሥራቅም ሃይማኖትን፣ ዳር ድንበርን እና ብሔረሰብን ሽፋን አድርጎ ጥቃት ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
እንደ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ገለጻ፣ አልሸባብን ከኋላ የሚገፉት ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ጠላት የሆኑ አሉ፡፡ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚያዳክም፣ ሀገርን የሚያፈርስና ሉዓላዊነትን የሚነካ ድርጊት ሲኖር መከላከል ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የምትፈልገው ከማንም ሳትደርስ ሕዝቧን፣ ሀብቷን፣ ሠላምና ደኅንነቷን መጠበቅ ቢሆንም፤ አንዳንድ ሀገራት ጥቅሟን በመፈለግ ይበጠብጣሉ፡፡ እነዚህ ሀገራት ከድርጊታቸው ተቆጥበው በመከባበር አብረው ቢሠሩ ያዋጣቸዋል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከቀጣናው ሀገራት ጋር አብሮ ለመልማት፣ ለማደግና ለመበልፀግ የጋራ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ትስስሮችን ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ኢትዮጵያን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ሆነው የሚበጠብጡ አካላት ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አዲስ አበባ፡– የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ የጨቅላ ሕፃናትን ሞት መቀነስ የሚያስችሉ የሕክምና ማዕከላትና ግብዓት ማሟላት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።
ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በክልሉ የጨቅላ ሕፃናትን ሞት መቀነስ የሚያስችሉ የሕክምና ማዕከላትና ግብዓት ማሟላት የሚያስችል ነው ተብሎለታል።
በመድረኩ ላይ በጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ ሕፃናትና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ዓለማየሁ ሁንዱማ እንዳሉት፤ የጨቅላ ሕፃናት ሞትን ለመቀነስ ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር እየተሠራ ነው።
በተለይም እናቶች በምጥ ጊዜ ፈጥነው ወደ ጤና ተቋማት እንዲደርሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይኖር አምቡላንሶችን ተደራሽ የማድረግ እንዲሁም ፈጣንና ጥራት ያለው ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከጨቅላ ሕፃናት ማሞቂያ በተጨማሪ የፅኑ ሕሙማን የሕክምና መርጃ ማዕከልን ለማደራጀትና የሕክምና ቁሳቁስ ለማሟላት እንዲሁም የጨቅላ ሕፃናት ሞት መንስኤዎችን በጥናትና ምርምር ለመለየት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር እየሠራን ነው ብለዋል።
የጨቅላ ሕፃናት ኢንፌክሽንና የመታፈን ችግሮችን ለይተን ከሠራን 90 በመቶ የሚሆነው ያለጊዜ የሚወለዱ የጨቅላ ሕፃናትን የጤና ችግር እንፈታለን ሲሉም ተናግረዋል።
ለዚህም ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት መመደቡን ዶክተር ዓለማየሁ ጨምረው ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጀ አብደና በበኩላቸው፤ የጨቅላ ሕጻናትን ሞት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በክልሉ እናቶች ጥራት ያለውና ቀልጣፋ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እየሠራን ነው ብለዋል።
በክልሉ ያሉ የጤና ተቋማትም ለእናቶች ጤና ትኩረት በመስጠት በቅድመ ወሊድና ድህረ-ወሊድ ተገቢውን አገልግሎት በወቅቱ እንዲሰጡ፣ ምልልስ እንዳይኖር፣ በቂ የሰው ኃይል፣ መድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች እንዲሟላ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የጨቅላ ሕፃናት ሞት ትልቁ መንስኤ ኢንፌክሽንና መታፈን በመሆኑ ሕጻናት እንደተወለዱ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት እንዳለባቸው ገልጸው፤ ለዚህም የጨቅላ ሕፃናት ማሞቂያ ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ያለጊዜ የሚወለዱ ጨቅላ ሕፃናትን ሕይወት ለመታደግ በጤና ተቋማቱ የጨቅላ ሕፃናት ማሞቂያ ማዕከል ከ50 በላይ በሚሆኑ የክልሉ ሆስፒታሎች ማደራጀቱን አስታውቀዋል።
በቀሪዎቹ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
ይፋ በተደረገው ፕሮጀክት በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት እስከ 108 የሚደርሱ ሆስፒታሎች የጨቅላ ሕፃናት ሕክምናና ማሞቂያ ማዕከል እንዲኖራቸው ማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።
የእናቶችና ጨቅላ ሕፃናት ጤናን ለይተን ማየት አንችልም ያሉት ምክትል ኃላፊው፤ ሕፃናት የኢንፌክሽንና የመታፈን ችግሮች እንዳይገጥማቸው ተገቢ የሆነ ክትትልና ሕክምና እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም