
ባለሙያዎች ሙዚቃን «ድምጸቱ ልዩ ውበት ያለውና በሰው ልቡና ሰርስሮ ሊገባ የሚችል ኃይል አለው።» ሲሉ ይተረጉሙታል። ይህ ትርጓሜ በእርግጥ ቃላት አስፈላጊ በመሆናቸው የሰፈረ እንጂ ሙዚቃ ምን ማለት ነው ብሎ ለጠየቀ፤ ለአድማጩ በሰጠው ስሜት ዓይነት ሊተረጎምም ይችላል። ብቻ ግን ዓለም በአንድነት ከተግባባቸው ሰዋዊ ባህርያት ባሻገር፤ የጋራ አግባቢ ቋንቋ ነው፤ ሙዚቃ።
ወዲህ ደግሞ በአገራችን ስላለው አዝማሪ እናነሳለን። አዝማሪዎች እንደ አየርና እንደ ውሃ በአገራችን በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ባለሙያዎች ነበሩ። ከቤተ መንግሥት ጀምሮ «ታችኛው» እስከሚባለው የማኅበረሰብ ክፍል ድረስ አዝማሪ ያገለግላል።
ታድያ አዝማሪ ሙዚቃ ለሌሎች ማስደመጥ ብቻ ሳይሆን በግጥሞች ታላላቅ መልዕክትን ማስተላለፍ አንዱና ትልቁ ሚናው ነው። መልዕክቶችን በቅኔ ያደርሳል፤ ያቀብላል።
ከስያሜው እንጀምር፤ «አዝማሪ» የሚለውን ስያሜ የተለያዩ አካላት በተለያየ ብያኔ ግን መሰረቱ አንድ በሆነ አተረጓጎም ይተረጉሙታል። አንዷለም አባተ ሞገስ ለአማርኛ ቋንቋ፣ የሥነ ጽሑፍና ፎክሎር ትምህርት ክፍል በሠሩት ጥናት ላይ ስለትርጓሜው ተከታዩን ሃሳብ አስፍረዋል፥
«ደስታ ተክለወልድ (1962፡ 496)። ‘ያዘመረ፣ የሚያዘምር፣ ዘፋኝ፣ ባለማሲንቆ፣ አርኾ፣ ጯሂ’ በማለት የአዝማሪን ማንነት በይነውታል። አዝማሪ የሚለው ቃል ‘ዘመረ’ ከተባለው የግዕዝ ቃል የተገኘ መሆኑና ትርጉሙም «አመስጋኝ» ማለት እንደሆነ ደግሞ አሸናፊ (1971, 168)፤ ‘ግጥምና ዜማውን በሃገረሰባዊ መሣሪያ(መሰንቆ) በማጀብ በታዳሚው ፊት ብቻውን ወይም በጥንድ ሆኖ የሚከወን እና ታዳሚውን የሚያዝናና ዘፋኝ ማለት ነው’ በማለት የአዝማሪን ማንነትና ሙያ ይገለጻሉ።…»
ይህ እንዳለ ሆኖ፤ አዝማሪ ሲሰጥ በኖረውና አሁንም እየሰጠ ባለው አገልግሎቱ ልክ ነው ወይ የተቀመጠው ስንል እውነታው እንደዛ አይደለም። ከአራት ዓመታት በፊት በባህርዳር ከተማ «አዝማሪ ከየት ወዴት» በሚል ርዕስ በተካሄደው ሁለተኛው ዓለምአቀፍ የአዝማሪ ጉባኤ ላይ ይኸው ጉዳይ ተነስቶ ነበር። በጉባኤው ተሳታፊ ከነበሩ ምኁራን መካከል ዶክተር ሙሉቀን አንዷለም በአዝማሪ ሙያ ላይ በቂ ጥናት እንዳልተደረገ ገልጸዋል።
በንግግራቸውም «ኢትዮጵያ ዉስጥ አዝማሪ ብዙ ትኩረት የተነፈገ ሆኖ ነው ለረጅም ጊዜ የቆየው።» ብለዋል። በእርግጥም አንድ አዝማሪ ብቻውን የባህል ሙዚቃ ቡድንን ሥራ ይሠራል ማለት ይቻላል፤ ግጥም ያዘጋጃል፣ ግጥሙን ከዜማ ያዋህዳል፣ ሙዚቃውን ያቀርባል። ሙያውም ሕዝቡን የሚያገለግል፤ ሕዝቡን በዚህ ሙያ የተገለገለ ቢሆንም ባለሙያው ግን ሲጠቀምም ሆነ ክብር ሲያገኝ አይታይም።
የኢትዮ – ጃዝ አባት የሚባለው አንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያ ሙላቱ አስታጥቄ፤ ስለአዝማሪዎች የተነሳ እንደሆነ «አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው» ማለታቸው ይታወሳል። እንደውም የሚበጀው የአዝማሪን የሙዚቃ ስልት ብቻም ሳይሆን የኢትዮጵያ ሙዚቃ መሣሪያዎችንና ሙዚቃን አሁን ካለበት ደረጃ ካደረሱት ላይ ተቀብሎ ማሻሻልና ማስቀጠል ነው ብለዋል።
በአዝማሪ ዙሪያ ታዲያ በቁጥር ብዙ የሚባሉ አይደሉም እንጂ የተሠሩ ጥናቶችን እናገኛለን። ለዚህም በየዓመቱ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የአዝማሪ አውደ ጥናት ጥሩ መንገድ ሆኗል። ጥናቶቹን አይቶ በግኝቶቻቸውና በምክረ ሃሳቦቻቸው መሰረት ወደ ተግባር የሚለውጥ ሲገኝም ስኬቶች ሊታዩ ይችላሉ። ታዲያ ከተሠሩ ጥናቶች መካከል በ2ኛው የአዝማሪ አውደ ጥናት ላይ ከቀረቡ ሥራዎች አንዱን ወዲህ ልናመጣው ወደናል።
ረዳት ፕሮፌሰር ውቤ ካሳዬ «አገር በቀል እውቀትን ዳግም መቃኘት» በሚል ዐቢይ ጉዳይ የአዝማሪን ባህል በማንሳት /Revisiting Indigenous Knowledge: the case of Azmari Culture/ በሚል ርዕስ ጥናት አዘጋጅተዋል። በዚህም ጥናት ላይ እንዳሰፈሩት፤ አገር በቀል እውቀት በተቋም ደረጃ የተደራጀም ይሁን ያልተደራጀ፤ ለአገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ይሁንና እነዚህ አገር በቀል እውቀቶች በተግባቦት ችግር ምክንያት ሳይተላለፉ ይቀራሉ፤ በመካከል ይጠፋሉም።
የተግባቦት ችግር ሲባል በአንድ በኩል በአስረካቢውና በተረካቢው መካከል የሚፈጠር ክፍተት ነው። በተጓዳኝ አገር በቀል እውቀቶች ብዙ ጊዜ በቃል የሚተላለፉ በመሆናቸው ነው። ይሁንና በቃል መተላለፋቸው ላይ ምንም ፈተና ባይጋረጥና የባህል ወይም የእውቀት ልውውጥ ቢደረግ እንኳ፤ በቃል ያለ በመሆኑ እየተለወጠና እየተቀየረ መሄዱ አይቀሬ ነው።
ታዲያ በዚህ ጥናት መሰረት፤ አጥኚው ያነጋገሯቸው አዝማሪዎችን የአዝማሪን ባህል ለማስፋፋትና ባህሉን ለአገር በማስተዋወቅ ደረጃ የተደረጉ ሙከራዎች ብዙ የሚባሉ አይደሉም። አዝማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ በአዲስ አበባ እንኳ ቢታይ የአዝማሪን አኗኗር ለመቃኘትና ለመቀየር በማንም የተደረገ ሙከራ የለም፣ ኅብረት ፈጥሮ መንቀሳቀስ ላይ ፍጥነት አይታይም፣ በመንግሥት ደረጃ የሙያ ብቃት ትኩረት አላገኘም፣ የመገናኛ ብዙኅን ሚናቸውን በአግባቡ አልተወጡም፣ አዝማሪን ለማስተዋወቅ የተሄደው ርቀት እምብዛም ነው…ወዘተ።
በአንጻሩ ደግሞ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ይገልጻሉ ሲል ጥናቱ አካትቷል። የተለያዩ አውደ ጥናትና ጉባኤዎች እንደሚካሄዱ፣ ፌስቲቫሎች እንደተዘጋጁ፣ በቱሪዝም ሥራ ላይ አዝማሪዎችም መካተታቸውና የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎችም ተጠቅሰዋል። ይሁንና ግን አሉ የምንላቸው በጣት የሚቆጠሩ የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች ሳይቀር ለአገር በቀል የሙዚቃ መሣሪያዎች የሚሰጡት ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑ ሲነሳ እንሰማለን።
ይኸው ጥናት ታድያ አስታራቂ የሚሆኑ የመፍትሄ ሃሳቦችን ያቀብላል። በተለይም አዝማሪዎች ተሰባስበው የሚመካከሩበትን አውድ ማሰናዳት ሁሉንም የሚያስማማ ይመስላል። ከዛ ባሻገር የአዝማሪ ውድድሮችን ማዘጋጀትና የአዝማሪዎች የሙያ ማኅበር በማቋቋም ችግሮችን ተቋቁሞ አገር በቀል የሆነውን የአዝማሪን የሙዚቃ ጨዋታ ከትውልድ ትውልድም፣ ከአገር አገርም ማስተላለፍና ማስተዋወቅ ይቻላል።
ጥናቱ ታዲያ በጠቅላላው ምንም እንኳ የአዝማሪን የሙዚቃ ጨዋታ ለማስተዋወቅና ለማስተላለፍ ብሎም ለማቆየት የተደረጉ ጥረቶች መኖራቸውን ጠቅሶ፣ ዘላቂነታቸው ግን አጠራጣሪ ከመሆን እንዲወጣም ምክረ ሃሳቡን ያቀብላል።
ከተገቢው ቅጣት ጋር ይቀበላል።አጥፊው ሰውዬ ግን አንዳች የመጸጸት ስሜት ካልታየበት ልበ ደንዳና ሰው ነው ተብሎ በ “አፎቻ” ፊት “ናሙስ ቀሊል” ይሰኛል። ከዚያም ከ “ጌይ ኡሱአች” ህብረቶች ጋር በህይወት እስካለ ድረስ እንዲቆራረጥ ይወሰንበታል ማለት ነው።
“አደብ” የጌይ ኡሱእ የዘወትር ትኩረት ነው። በሀረሪ ውስጥ ስትዘዋወሩ “አደቡሽ” የሚሉ ሰዎች በየቀኑና በየሰዓቱ ሊያጋጥሟችሁ ይችላል። ይህ አባባል በአማርኛ ሲመነዘር “አደብ አድርግ” ወይም “ አደብ ግዛ “ እንደማለት ይሆናል። “የጌይ ኡሱአች” ሌሎች ሰዎች “አደብ” እንዲገዙ የሚገስጻቸው በዚህ አባባል ነው። እያንዳንዱ ሰው ትኩረትም “አደብ” ላይ ይሆናል።
የኢትኖግራፊ አጥኚው አፈንዲ ሙታቂ ይናገራል አዎን ! “ጌይ ኡሱእ” ከሰዎች ጋር ያለው ማህበራዊ ግንኙነት እንዳይበላሽበት ስለሚፈልግ በ “አደብ” ላይ በጣም ያተኩራል። እንቅስቃሴዎችን በሙሉ በ”አደብ” ዙሪያ ያጠነጠኑ ናቸው። ሌላኛው ደግሞ “ ዚጋል” ነው ።
ፀጥተኛው የሞራል ደንብ ይህንን ሲያስረዱ አቶ አፈንዲ ሙታቂ አንድ ሰው ጥፋት ቢያጠፋ እና ሌላ ተመልካች ቢኖረው ሄዶ አጥፍተሃል በደለኛ ነህ አይለውም። ይልቅ ከቻለ ቀርቦ ይነግረዋል። ወይም ለምን ድርጊቱን እንዳደረገው ለመረዳት ይሞክራል።በዚህ ሁሉ ግን ያን ግለሰብ አሳልፎ ለሽማግሌም ፤ለሌላም ሰው አይሰጠውም በዝምታ ግን ድርጊቱን እንዲያስተካክል ያልፈዋል ፤ ይህም አንዱ የሞራል ደንብ ነው።
በእያንዳንዱ ክልሎች እና ብሔረሰቦች የራሱ የሆነ በባህላዊ ዕውቀት ፣ የደረጀ ድንቅ የመቻቻል፣ የሰላም እና የፍቅር እሴቶች አሉ፤ የመጣብንንና የሚመጣብንን ሰይጣናዊ የጥፋት ውሃ ለመከላከልና ለመግታት የሚረዱ።
ስለዚህም ልክ እንደ ሐረር የሌሎችም ብሔር ብሔረሰቦች ድንቅ ባህላዊ ዕውቀት ከአገር አልፎ ለዓለም ምሳሌ እንዲሆን ማበልጸግ እና ለአገራዊ መግባባት መጠቀም አስፈላጊ ነው።ኢትዮጵያ የፍቅር ፣ የመቻቻል አገርና ምድርነቷ ።ሰላም!!
የሚመለከታቸው ሁሉ አዝማሪን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አገር በቀል እውቀቶችን በማቆየት በኩል ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ ያቀርባል።
እንግዲህ ይህ ጥናት ከዓመታት በፊት የተሠራ ቢሆንም ከአዝማሪነት ሙያ ጋር ተያይዞ የተገኘ ይሄ ነው የሚባል ለውጥ አልታየምና ዛሬም ድረስ በተግባር ያገለግላል። በእርግጥ ዛሬ ላይ በምናያቸው አንዳንድ ኪነጥበባዊ እንዲሁም የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች ላይ አዝማሪዎች ሥራዎቻቸውን ሲያቀርቡ መታዘባችን አይቀርም። ይህም ይበል የሚያሰኝ ሆኖ፤ ትውልድ ከቀደመ ነገሩ እንዳይፋታ ማስተሳሰሪያና መቋጠሪያ በመሆን ሊያገለግል ይችላል።
እናም ይህ አገር በቀል እውቀትን ዳግም መቃኘትን መሰረት አድርጎ የአዝማሪን ባህል የቃኘ ጥናት ዛሬም ቢሆን ጆሮ ሊሰጠው የሚገባ ነው። በትላልቅ አገራዊ ጉዳዮችና ወቅታዊ ክስተቶች ምክንያትም አጀንዳዎች በየጊዜው የሚቀያየሩ ቢሆንም ከቀደመው አገር በቀል እውቀት መፍትሄ አይታጣምና መለስ ብሎ መቃኘቱ መልካም ነው። ይህን በአዝማሪ ጨዋታ ምክንያት አነሳን እንጂ፤ ለጠቅላላው ማኅበራዊ ትስስራችንም የሚበጅ እንደሆነ ልብ ይሏል!
አዲስ ዘመን ሰኔ 30/2011
ሊድያ ተስፋዬ