ነፍሰ ጡሮቹ ተፋላሚዎች በፓሪስ ኦሎምፒክ

በየአራት አመቱ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር በፓሪስ ሲካሄድ 16ኛ ቀኑን ይዟል።

206 ሀገራት በሚሳተፉበት በዘንድሮው ውድድር ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶችም እየተሳተፉበት ይገኛል::

ሀገራት ከውድድሩ ተሳትፎ የዘለለ ስኬት ማስመዝገብ የሚፈልጉ ሲሆን ዋናው ደግሞ ሜዳሊያዎችን በማንሳት የሀገራቸውን ስም በዓለም አደባባይ ማስተዋወቅ ነው::

በዚህ ውድድር ላይ ለየት ያሉ ክስተቶች በብዙሃ መገናኛዎች ሽፋን እያገኙ ናቸው::

ከዚህ መካከል በውድድሩ ላይ ለሀገራቸው ሜዳሊያ ለማምጣት እየተፋለሙ ያሉ ነፍሰጡር ስፖርተኞች የመኖራቸው ጉዳይ ነው::

ግብጻዊቷ የሻሞላ ስፖርተኛ ናዳ ሃፌዝ አንዷ ስትሆን ይህች ስፖርተኛ የሰባት ወር ነፍሰጡር መሆኗ ታውቋል:: የፓሪስን ጨምሮ ባለፉት ሶስት ኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ግብጽን በመከተል የተወዳደረችው ይህች ስፖርተኛ ከውድድሩ በጊዜ ተሰናብታለች::

በፓሪስ ኦሎምፒክ ያለ ፈቃዷ ዳሌ የነካው ግብጻዊ ስፖርተኛ ለእስር ተዳረገ ስፖርተኛዋ በኢንስታግራም ገጿ ላይ ባጋራችው መልዕክት በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ የሰባት ወር ነፍሰጡር ሆና መካፈሏን ተናግራለች::

ሌላኛዋ ነፍሰ ጡር ሆና በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፈችው የአዛርባጂያኗ የቀስት ስፖርተኛዋ ያይላጉል ራማዛኖቫ ነች::

ያይላጉል በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ የስድስት ወር ከ15 ቀናት ነፍሰጡር ሆና የተወዳደረች ሲሆን ልጄ ሆዴን እየረገጠችኝ ነበር የተወዳደርኩት ብላለች::

ነፍሰጡር ስፖርተኞች በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ሲሳተፉ የፓሪሱ የመጀመሪያ ያልሆነ ሲሆን በ2012 በተካሄደው የለንደን ኦሎምፒክ ውድድር ላይ አሜሪካዊቷ የእጅ ኳስ ስፖርተኛ ኬሪ ዋልሽ አንዷ ነበረች::

ይህች ስፖርተኛ ከቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን የእጅ ኳስ የወርቅ ሜዳሊያ ለአሜሪካ አስገኝታለች::

የሕክምና ባለሙያዎች ነፍሰጡር ሴቶች ከባድ እንቅስቃሴ ማድረግ ጽንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶች እንዲደርሱ ሊያደርጉ ስለሚችሉ እንዲጠነቀቁ ያሳስባሉ::

በጋዜጣው ሪፖርተር

 አዲስ ዘመን ነሐሴ 5/2016 ዓ.ም

 

 

 

Recommended For You