በእውቀት እና በኃላፊነት ላይ የተመሰረተ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ለመገንባት

በሀገራችን በማህበራዊ ሚድያ የሚሰራጩ የጥላ ቻና ሀሰተኛ ንግግሮችን በህግ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 1185/12 የተደነገገ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ አዋጅ ላይ የጥላቻ ንግግር ማለት በአንድ ሰው ወይም በተወሰነ ቡድን ማንነት ላይ ያነጣጠር ብሄርን፣ ብሄረ ሰብንና ህዝብን፣ ሃይማኖትን፣ዘርን፣ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ሆን ተብሎ መድሎን፣ ጥላቻን ወይም ጥቃትን የሚያነሳሳ ንግግር እንደሆነ ያስ ረዳል፡፡

በተጨማሪም ሀሰተኛ መረጃ መረጃ ማለት፤ ሀሰተኛ የሆነና የመረጃውን ሀሰተኝነት በሚያውቅ ወይም መረጃ ውን ባሰራጨው ሰው ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንፃር የመረጃውን እውነትነት ለማጣራት በቂ ጥረት ሳያደ ርግ የሚሰራጭ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ከፍ ያለ ንግግር እን ደሆነም ያመላክታል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፤በሀገራችን መገናኛ ብዙኃን በተ ለይም ማህበራዊ ሚዲያዎች በተለያየ መንገድ ጥላቻ አዘል መረጃዎች በአደባባይ ሲሰራጩ ይስተዋላል፡፡ ችግሩ ስራዬ ተብሎ ወይም ባለማወቅ /ከሙያ እጥረት የተነሳ ሊከሰት የሚችልበት ክፍተት ሰፊ ቢሆንም፤ በኛ ሀገር ያለው እውነታ ግን ከችግሩ ፖለቲካዊ ትርፍ ከመ ፈለግ የመነጨ ስለመሆኑ ብዙም ለጥያቄ የሚቀርብ አይ ሆንም፡፡

በአሁኑ ወቅት የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ለሀገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ለሰብ አዊ ክብር ጠንቅ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይኸው ድርጊት በህ ዝቦች ዘንድ ያሉ መልካም እሴቶችን በመሸርሸር ለሀገር አንድነት ስጋት እየፈጠረ መሆኑንም በተለያዩ መድረኮች ሲገለፅ ቆይቷል፡፡

ሰሞኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ይፋ ባደረገ በት ወቅት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ እየተስፋፋ መሆኑን ከተሰበሰበው መረጃ መረዳት መቻሉን ግልፅ አድርጓል።

በተለይም ብሄርን ሃይማኖትን እና ፖለቲካዊ አመ ለካከትን መሰረት በማድረግ ህዝብን በጠላትነት የሚፈ ርጁ እና አንዱ ለሌላው ስጋት እንደሆነ የሚያስመስሉ የሃሰት መረጃዎች በስፋት መሰራጨታቸውንና የጥላቻ ንግግር አስጊነት ካለፈው አመት አንጻር በይዘትም በአ ቀራረብም ተባብሶ የቀጠለ መሆኑን በሪፖርቱ አመል ክቷል፡፡

እውነታው የሚያሳየው፤ በማህበረሰባችን ዘንድ መረጃዎችን የማጣራት፣የመመርመር፣የማገናዘብ፣ከሌ ሎች ምንጮች ጋር የማመሳከር ልምድ እጅግ አናሳ መሆኑ ነው፤ ከዚህ የተነሳም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኗቸው እየበረታ በሀገር ላይ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑን ነው፡፡

አሁን ላይ አንድ ተፅእኖ ፈጣሪ ወይም አንቂ ሰው የሆነ ይዘትን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚለቀቅበት ሰአት ፅሁፉ እንኳን ተነቦ በማያልቅበት ፍጥነት፣ የተ ፃፈው ምን እንደሆነ፣ ስለምን እንደተጻፈ ትክክለኛነ ቱን ሳያጣሩ፣ ሙሉ መልእክቱም ሳይገባን ለሚሊዮኖች ማጋራት ፣በአድናቆት የተሞላ አስተያየት መስጠትም የተለመደ ሆኗል፡፡ከማህበራዊ ሚዲያ ባለፈም አንዳንድ ጊዜ የጋራ በሆነ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መደበኛ በሚባ ሉት የመገናኛ ብዙኃን ፅንፍና ፅንፍ የረገጡ ሃሳቦች ሲን ፀባረቁ ይታያል፡፡

ከይዘቱ ይልቅ መረጃ ያቀበለውን ሰው ወይም ተቋም በመመልከት ብቻ የጥላቻ ንግግሮችን፣የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ተለምዷል፡፡ ችግሩ እንደ ሀገር ይዞ ከመጣው አደጋ አንጻር ማህበረሰቡ መረጃን የመ ተንተንና የማጣራት ብሎም መርጦ የመውሰድ አቅም እንዲጎለብት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሀሰተኛ መረጃን ጨምሮ ሌሎች የጥላቻ ንግግሮች እንደ ሀገር ሊያስከትሉት የሚችለውን ጥፋት ምን እን ደሚመስል ማስተማር፣በችግሩ ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው ማስቻል ያስፈልጋል። ችግሩ ሊያስከትል ከሚችለው ጥፋት አንጻር፤ የሚመለከታቸው አካላት ብቻ ሳይሆኑ ዜጎች በሙሉ በኃላፊነት ሊንቀሳቀሱ ይገባል።

ህዝቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ መረጃ ዎችን በምን አይነት መልኩ ማጣራት እንዳለበት ፣ የትኛው ሚዲያ አስተማማኝ መረጃ ይሰጣል፣የትኛው ሚዲያ ለማህበረሰብ ጠቃሚ ነው፣የትኛው ሚዲያ ለሀገር ጠቃሚ ነው፣የትኛው ሚዲያ ለሀገርና ለህዝብ የሚሆነውን በጎ ነገርን ያስባል፣ የትኛው ሚዲያ ከግ ጭትና ከጦርነት ይልቅ በመተሳሰብ በመነጋገር ሰክኖ በማሰብ ትውልድን የመቅረፅ ሚና ይጫወታል፤ በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ የጠራ እውቀት እንዲኖረው ማስቻል ያስ ፈልጋል፡፡

ትናንት ይሁን ዛሬ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ሀገር እና ህዝብን ለከፍተኛ አደጋ አጋልጦ ብዙ ያልተ ገባ ዋጋ እንድንከፍል አድርጎናል፡፡ ይህ አደጋ ዳግም እን ዳይፈጠር የማስተማር፣ የመመከት፣ተጠያቂነት እንዲሰ ፍን ማድረግ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የተቋቋመው ይህንኑ እውነታ ታሳቢ አድርጎ ነው፡፡

በእርግጥ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ደረጃውን የጠበቀ በሌላው ዓለም ጋዜጠኞች የሚጠቀሙበት የስነ ምግባር ደንብ አውጥቷል፡፡ ይህ ደንብ ለመደበኛው የመ ገናኛ ብዙኃን ብቻ ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ዲጂታል ሚዲያ ላይ ለተሰማሩ ጋዜጠኞች ወይም ራሳቸውን እንደ ጋዜጠኛ ለሚቆጥሩ ግለሰቦች መሰረታዊ የሚባል የጋዜ ጠኝነት ስነ ምግባር ደንብ ነው፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህግ ጥሰቶችና የስነ ምግባር ግድፈቶች በሚኖሩበት ጊዜ ሊታረሙ የሚችሉበትን ስር አትም አዘጋጅቷል፡፡ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተ ውጣጡ ግለሰቦችን የያዘ የግልግል ዳኝነት አቋቁሟል። በዚህም የጥላቻ ንግግር ጉዳት ደርሶብኛል ወይም አላ ግባብ ስሜ ተነስቷል፣ ስሜ ጠፍቷል የሚል ማንኛውም ግለሰብ፣ ተቋም ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሄዶ በማ መልከት መፍትሄ የሚያገኝበት መንገድ ተዘርግቷል፡፡

ይህም ሆኖ ግን አሁንም ችግሩን ለዘለቄታው መፍታት የሚቻለው፤ህዝቡ በመገናኛ ብዙኃን የሚተ ላለፉ መረጃዎችን እውነት ይሁኑ የተሳሳቱ ፤በአግ ባቡ ተረድቶ የሚያስተናግድበትን ንቃተ ህሊና ማሳደግ ነው። መረጃዎች ከማንም ይምጡ ከማን፣ በጥላቻ የተለወሱ ስላለመሆናቸው ፣ ህብረተሰብን የማይከፋ ፍሉ እና በቂ መረጃ የሚቀርብላቸው ተአማኝ ስለመሆ ናቸው ማረጋገጥ የሚችልበትን ባህል መፍጠር ያስፈ ልጋል፡፡

አሁን ላይ እንደሀገር እያጋጠሙን ያሉ ችግሮች በአ ንድም ይሁን በሌላ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ጋር የተያያዙ ከመሆናቸው አኳያ፤ ችግሮ ቹን ለመሻገር የመገናኛ ብዙኃኑ ኃላፊዎች በተለይም በርካታ ተከታይ ያሏቸው የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች በኃላፊነት መንገድ ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡

በሀገሪቱ የሚዲያ ነጻነት መኖሩ የተለያዩ መረጃ ዎች እና ሃሳቦች በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አማራጮች እንዲሰራጩ የተሻለ እድል ፈጥሯል። ይህ ማለት ግን በስመ ነጻነት የትኛውንም መረጃ እንደፈለግነው የማሰራጨት መብት አለን ማለት አይደለም ። ሌላም አካል ቢሆን የተሳሳቱ መረጃዎችን በየትኛውም ምክ ንያት ተቀብሎ በስሜትና ባልተገባ መልኩ ማሰራጨት ይችላል ማለት አይደለም፡፡

ይህ አይነቱ አካሄድ ለተጀመረው የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ዋነኝ ፈተና እየሆነ ነው፡፡የጀመርነው የዲ ሞክራሲ ስርአት ከሁሉም በላይ በመገናኛ ብዙኃን አካባቢ ያሉ አካላትን እና ባለሙያዎችን በኃላፊነት መን ቀሳቀስ የሚጠይቅ ነው። መላው ህዝባችንም ቢሆን ፤ ሀሰቱን ከእውነት፣ስሜቱን ከስክነት ተደበላልቀው የሚሰ ራጩ መረጃዎችን በአግባቡ የመለየት ኃላፊነት አለበት፡፡

በእርግጥ የማህበራዊ ሚዲያዎች መስፋፋት ዓለምን ወደ አንድ መንደርነት እያቀራረባት ይገኛል፡፡ በዚህም የሰው ልጆች የሚዲያና የፖለቲካ ተሳትፎም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው፡፡ የዴሞክራሲ ባህልን ለማሳደግና ህይወትን ለማቅለል የተሻሻለ እድል ይዞ እን ደመጣ ችግር ይዞ መምጣቱ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ በችግሩ በእድገት ወደ ኋላ በቀሩት ሀገራት አመዝኖ ይስተዋ ላል፡፡

በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዝሃነት ባለባቸው ሀገራት ፤ሀገረ መንግስቱን ለማስቀጠል ሆነ ህዝቦች የሚፈልጉትን ልማት እውን ለማድረግ ማህበራዊ ሚዲ ያውን በኃላፊነት መንፈስ መጠቀም ወሳኝ ነው፡፡ ከሰ ላምና አብሮነት ይልቅ ጦርነትንና መለያየትን፣ግጭትና ጥላቻን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማቀንቀን ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን የሚችል አደጋ ይዞ መምጣቱ የማይቀር ነው ፡፡

ከቅርብ አመታት ወዲህ ከጥላቻና ያልተገቡ መል እክቶች ባለፈ አሰቃቂና ፀብ አጫሪ ምስሎችን በፌስቡ ክና መሰል ማህበራዊ ሚዲያዎች መመልከት የየእለት አጋጣሚያችን ሆኗል፡፡ እነዚህ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የውሸት መልእክቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ካለው መረጃን የማጣራት ባህል አናሳነት የተነሳ እንደ እውነት የመወሰዳቸው አጋጣሚ ሰፊ ነው። በዚህም የሀ ገሪቱ ሰላምና የህዝቦቿ በጋራ የመኖር እሴቶች እየጸ ጎዱ ነው፡፡ ችግሩ የህዝቦችን አብሮነትን ከመሸርሸር አልፎ ለህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያ ትም እየሆነ ነው፡፡

በተለይም አብዛኛው በሚባል ደረጃ ወጣቱ ትውልድ የማህበራዊ ሚዲያን ጥቅም የተረዳበት መንገድ ትክክለኛ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ብዙዎቹ እየተጠቀ ሙት ያሉት ለመሰዳደብ፣ ለመኮራረጅ፣ አንዱ ማኅበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ ብዙ ሰው ሲያንቀሳቅስ ሲያዩ እነሱም እንደዛ ለመሆን ለመሞከር ነው። በአብዛኛው የማኅበ ራዊ ሚዲያን ዋጋ እና ጥቅም በማወቅ እና በማስተዋል ሳይሆን የጊዜያዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት እና ለማርካት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል።

በመሆኑም አጠቃቀሙ ስርአት ያስፈልገዋል፡፡ ስርአት የምንለው ነገር ለዘለቄታዊ ጥቅም ጊዜአዊ ፍላ ጎትን መግታት ነው። ስለዚህ ወጣቶች የትምህርት መጽ ሐፍቶችን ማንበብ ለዘለቄታ የሚሆን ነገርን መሥራት ሲገባቸው ከጠዋት እስከ ማታ አንዳንድ ጊዜ እንደውም እስከ ሌሊቱ ዘጠኝና አስር ሰአት በዋይፋይ እየተጠቀሙ ቀን ላይ ደግሞ ስድስት ሰአት፣ ሰባት ሰአት የሚነሱና ምግብ የሚጠይቁ ልጆች እንዳሉ እየተመለከትን ነው።

ማህበራዊ ሚዲያው በእውቀት፣ በህግ / በተጠያ ቂነት በጠንካራ ዲሲፕሊን ካልተመራ ፤ሊያስከትለው የሚችለው ጥፋት ሀገርን ህዝብን ያልተገባ ዋጋ ከማስ ከፈል ባለፈ የሀገር ህልውና ስጋት ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ለዚህ ደግሞ በዚህ ችግር ምክን ያት ትናንት የከፈልነውን፤ ዛሬም እየተፈታተነን ያለውን አደጋ በስክነት መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡

የማህበራዊ ሚዲያው በህግና በተጠያቂነት እንዲ መራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በእርግጥ ኢትዮጵያ የማህበ ራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ህግ እያረቀቀች መሆኑ ከተሰማ አመታት ቢቆጠርም መሬት ላይ ወርዶ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፈር የሚያሲዝ ነገር አልተገኘም፡፡ ስለዚህ በሌሎች ሀገራት እንደምናየውን የማህበራዊ ሚዲያ አጠ ቃቀም ህግ እንዲኖር ማድረግ ለነገ የሚባል ተግባር መሆን የለበትም፡፡

አሁን ላይ ዘመኑ የሰጠውን ቴክኖሎጂ በልኩና በተ ገቢው መንገድ በማስተናገድ በእውቀት እና በኃላፊነት ላይ የተመሰረተ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ለመገን ባት፣ ከሁሉም በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎ ችን ንቃተ ህሊና ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ማህበረሰቡም መረጃን እንዳለ በመውሰድ እራሱን ከዛም ባለፈ ሀገሩን አደጋ ውስጥ ከሚከት አካሄድ መቆጠብ አለበት፤ ለዚህ ደግሞ ቆም ብሎ ማሰብ ይኖርበታል፡፡

ታሪኩ ዘለቀ

አዲስ ዘመን ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም

Recommended For You