• ደም በሰውነት የደም ስር ውስጥ በመዘዋወር የተለያየ ስራን ለመስራት ይጠቅማል።
• በልብ ተገፍቶ በተለያዩ የደም ስሮች አማካኝነት ወደ ሳንባና ወደ ተለያዩ አካላቶች ይደርሳል።
• የሰው ልጅ አካልን ከበሽታ አምጪ ህዋሳት የመጠበቅ ድርሻን ይወጣል።
• በአማካኝ በአንድ ጎልማሳ ሰው ውስጥ ከአምስት እስከ ስድስት ሊትር ደም ይገኛል።
• ግማሽ ያህሉ ደም የደም ረቂቅ ህዋሳትን ይይዛል። ቀሪው ደግሞ ውሃ መሰልና ፕላዝማ በመባል የሚጠራ ነው።
• ምግብ ከአንጀት ውስጥ ከሰረገና ከጉበት ከተላቀቀ በኋላ በደም ውስጥ ይጓጓዛል።
• ሰውነታችን የማይፈልጋቸውን ተረፈ ምርቶች በፕላዝማ አማካኝነት ወደ ኩላሊትና ጉበት እንዲጓጓዙ ያደርጋል።
• ፕላዝማ ፕሮቲኖች ደም እንዲረጋ በማድረግ የሰውነት በሽታን መከላከል ሥርዓት አካል ይሆናል።
• ቀይ የደም ረቂቅ ህዋሳት በጤነኛ ደም ውስጥ አርባ አምስት በመቶ ያህሉ ወይም በአንድ ሊትር ውስጥ ከአራት እስከ ስድስት ሚሊዮን ያህል መጠን ድርሻ አላቸው።
• ንፁህ አየርን ከሳንባ ወደ ጥቃቅን ህዋሳት ያመላልሳሉ።
• እያንዳንዱ የደም ህዋስ ቀይ ቀለም እንዲይዙ በሚያደርግ ወይም ሄሞግ ሎቢን በኢንዛይም፣ በማዕድንና ስኳር የታሸገ ነው።
• ነጭ የደም ህዋሳት ከቀይ የደም ህዋሳት የሚለየው በመጠን መተለቅ፣ ማዕከል ወይም ኑክለስ ያላቸው በመሆናቸው፣ ቀይ ቀለም የሚሰጣቸው አካል ባለመኖሩና መልካቸውን እስካልቀየሩ ድረስ ብርሃን አስተላላፊ መልክ በመያዛቸው ነው።
• ነጭ ደም ህዋሳት እንደ ቀይ ደም ህዋሳት በብዛት አይገኙም። በአንድ ሊትር ደም ውስጥ ከአምስት እስከ አስራ አንድ ሺ ብቻ ነው ቁጥራቸው።
• ከውጭ የሚመጣ ወራሪ ህዋሳትን በመከላከል የሰው ልጆች ጤነኛ ሆነው እንዲኖሩ ያደርጋል።
• ብዙዎቹ ነጭ የደም ህዋሳት እድሜ ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው። አንዳንዶች በሽታ አምጪ ህዋሳትን በሚዋጉበት ወቅት ይሞታሉ። ቀሪዎች ደግሞ ምንም ጉዳት ካልደረሰባቸው የወራት ወይም የዓመታት እድሜ ብቻ ይኖራቸዋል።
አዲስ ዘመን ሰኔ 2/2011
ሞገስ ፀጋዬ