ኤርትራ ለቱርክ ተገዳዳሪዎች በር ብትከ ፍትም ቱርክ ግን ከተገዳዳሪዎቿ የሚመጣ ፈተናን ለማለፍ በምስራቅ አፍሪካ የተከተለችው ሌላ ስልት በታሪካዊ ወዳጇ በሶማሊያ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ እጅግ ግዙፍ /ሰፊ/ የሚባለውን የውጭ ወታደራዊ ጣቢያ ማቋቋሟ ነው።
የሶማሊው ጦር ሰፈር ሦስት ወታደራዊ ትምህርት ቤቶችን የያዘ ሲሆን፣ በአንዴ 1,500 ወታደሮችን ለማሰልጠን የሚያስችል ነው። የቱርክ ጉዳዮችን በተለያዩ መጽሔቶች የሚዳስሰው ሞሃመድ አብድል ካዴር ካህሊል ተርኪሽ አፌርስ /the Turkish Affairs/ በተባለው ሚዲያ እንደተነተነው ሶማሊያ ለቀይ ባህር መግቢያ መሆኗ እና ሌሎች ኃይሎች ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ሽሚያ የሌለበት መሆኑን በቱርኮች ታሳቢ ተደርጓል ይላል።
ሶማሊያ በችግሬ ደራሽ የምትላትን ቱርክን ሳታስ ከፋ ለጥያቄዋ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ተባብራለች። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ቱርክ አስቸጋሪ በሚባለው ሶማሊያ የፖለቲካ ትርምስ፣ የድርቅ እና ረሃብ አደጋ ወቅት እና የሽብር አውድ ውስጥ ሆና በፈረንጆቹ በ2011 ላይ አብራ ለመሥራት መቅረቧ ነው። ቱርኮች በወቅቱም በሀገሪቱ ተገኝተው ለድርቅ ችግሩ ተጋላጮች ዕርዳታ ለማድረግ እና የንግድ ስምምነትም ለመፈ ራረም ደፍረዋል።
በወቅቱ ቱርክ አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዘመቻ በማድረግ የሶማሊያን የድርቅ እና የረሃብ ቀውስ ለመፍታት ዘመቻ አድርጋ ነበር። በሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር እርዳታም ማሰባሰብ እና ለሶማሊያ ዜጎች መድረስ ችላ ነበር። በሶማሊላንድ እና ሶማሊያ መካከል ያሉ ግጭቶችም እንዲፈቱ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ በማድረግ ለማርገብ ጥራለች። በቱርክ የሚመሩ እና ተባባሪ የሆኑ አገራት የዓለም አቀፉ የእስልምና ትብብር ደርጅት በሶማሊያ ላለው ችግር ፈጥኖ ለመድረስ መሞከራቸው አሁን ቱርክ በሶማሊያ ላላት ብርቱ ተጽዕኖ መነሻ ነው።
ከዚያ በኋላ በየዓመቱ በኢስታንቡል የቱርክ እና ሶማሊ የግንኙነት መድረክ ይካሄዳል። ቱርክ በሶማሊያ ላላት ስልታዊ ትብብር በሚመጥን ደረጃ እጅግ ግዙፍ ኤምባሲ በሞቃዲሾ መገንባቷ የዚሁ ትኩረቷ ማሳያ ነው። አሁንም ድረስ ቱርክ ለሶማሊያ ዋነኛዋ የኢንቨስትመንት አጋር እና ተባባሪ በመሆኗ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ኢንቨስትመንት አላት። ቱርክ በሶማሊያ ያላት ትብብር በተቋማት ግንባታ፣ በመልካም አስተዳዳር፣ በወጣቶች ልማት፣ በድህነት ቅነሳ ላይ እንደሚያተኩር ትገልፃለች።
ቱርክ በሱዳን እና በሶማሊያ የተከተለችው ስልት የሚያመለክተው በምስራቅ አፍሪካ የጀመረችውን ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ ግንኙነት በየጊዜው ወደ ፖለቲካ እና ደኅንነት ጉዳዮች ማሳደ ጓን ነው። እኔ መዩ ቱርክ ባይ ፤ የምሸሽ ነኝ ወይ!!!
ይህቺ የዜማ ግጥም በምሥራቅ አፍሪካ ደገኛ ክርስቲያኖች ዘንድ ቢያንስ ለመቶ ዓመታት በበገና ደርዳሪዎች ስታቀነቀን ኖራለች። የኢትዮጵያ ደገኛ ክርስቲያን ነገሥታት ዘንድ ከኢብን አህመድ ኢብራሂም አልጋዚ /ግራኝ/ ጦርነት በኋላ የነጭ ጦረኛ ሰርጎ ገቦችን ሁሉ ‹‹ቱርክ›› ብሎ መጥራት የተለመደ ነበር።
ቱርክ ኢብን አህመድ ኢብራሂም አልጋዚ የሚመራው ሙስሊም አማፂ ኃይል በደገኛው ክርስቲያን ንጉሥ ዐፄ ልብነ ድንግል ላይ ዘምቶ ድል አግኝቶ የክርስቲያኑን መንግሥት ወደ ሰሜን እንዲሸሽ ካደረገ በኋላ የዚህ ዐማፂ ኃይል ብርቱ ወዳጅ፣ አባሪና ተሰላፊ የኦቶማን ቱርክ መንግሥት ወታደሮች ስለነበሩ፤ ቱርክ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የምትታይበት መነጽር ሁለት መልክ ያለው ሆኗል። ይሄን መልክ መሰረት ያደረገ ታሪካዊ እና የባህል ግንኙነትም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካ አላት።
ቱርክ በምስራቅ አፍሪካ በምትከተለው የውጭ ግንኙት እና ደኅንነት ፖሊሲ ኢትዮጵያ የምታተርፈውም፤ የምትሰጋበትም ሊኖር እንደ ሚችል እሙን ነው። ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንዲጠብቅ ዋነኛ ምክንያት እየሆነ ያለው በአባይ ግድብ ላይ የሱዳን እና ኢትዮጵያ አቋም ተቀራራቢ እንዲሆን በመሥራት ረገድ ሚናዋ ትልቅ ነበር።
በአንድ በኩል ግብጽ ላይ ጫና የመፍጠር ቢሆንም በኢትዮጵያ ላላት ሰፊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴም የግድቡ ልማት አቅም እንደሚሰጥ ስለሚያምኑበት ነው። ይሁን እንጂ በሱዳን እና በሶማሌ የተመሠረተው ወታደራዊ ጦር ሰፈር እና ማሰልጠኛ በአካባቢው ኃይል ሚዛን ውድድር አንፃር ሥጋት ሊፈጠር መቻሉ ሌላ ነጥብ ነው።
ኢትዮጵያ ሌላው ከቱርክ ጋር በተያያዘ ያለባት የደኅንነት ሥጋት በውስጥ ካለ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ነው። ቱርክ በአፍሪከ አህጉር የወታዳራዊ ኢንዱስትሪ ምርቶቿ ንም ገበያ እንዲያገኙ ማድረግ ትፈልጋለች።
በምሥራቅ አፍሪካም አረብ አገራት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጫና ከግምት ሳታስገባ የጦር መሳሪያ ገበያ እንዲፋፋም መፈለጓን የግብጹ አልሃራም ጋዜጣ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ያነሣሉ። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ የሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር እና ገበያ ውስጥ በግልጽ መታየቱ ነው። ምክንያቱም የተያዙት መሣሪያዎች ቱርክ ሠራሽ ናቸው።
ዘመን መፅሄት መጋቢት 2011