ሰው በምድር ላይ ሲኖር የሚያገኛቸው ጥሩም ሆኑ መጥፎ ነገሮች በሙሉ በሁለቱ ጆሮዎቹ መካከል በሚገኘው በታላቁ ህያው ኮምፒውተር አማካኝነት የሚፈጠሩ ናቸውአስደሳችም ሆኑ አሳዛኝ፣ ክፉም ሆኑ በጎ፣ በህይወት ዘመናችን የሚፈጠሩ ነገሮች ሁሉም በእኛው የሚታዘዘው የዚህ ህያው ኮምፒውተር ውጤቶች ናቸውፈረንሳዊው የሃሳብ ሊቅ ሞንቴስኩ እንዳለው በዚህ ዓለም ላይ በየቦታው ራሱን የእስር ሰንሰለት ውስጥ ቢያገኘውም ሰው በተፈጥሮው ነጻ ሆኖ ነውና የተወለደው ሰው የሚሆነውን ፈልጎ የመረጠውን አስተሳሰቡንና አመለካከቱን ነውየሆንነውና የምንሆነው ነገር ሁሉ በራሳችን ምርጫ የተፈጠረና የሚፈጠር ነው፤ ዕጣ ፋንታችንንም የምንጽፈው በገዛ እጃችን ነው፤ ያልዘራነውን አናጭድምና!
እናም መሆን የምንፈልገውን ለመሆንና ማግኘት የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት፣ በአጠቃላይ የምንመኘውን ዓይነት ስኬታማ ህይወትን ለመምራት የኮምፒውተራችንን አሰራር ማወቅ ዋናውን ቁልፍ በእጃችን እንደ መያዝ ይቆጠራልዕጣ ፋንታችን የሚወሰንበት የዚህ ግዙፍ ህያው ኮምፒውተር አሰራሩ ልክ እንደ ሰው ሰራሹ ኮምፒውተር ነው“ኮምፒውተር” የምንለው መሳሪያ ራሱ ከየት የመጣ ነው? በሁለቱ ጆሮዎቻችን መካከል በጭንቅላታችን ውስጥ የሚገኘውን “አዕምሮ” በመባል የሚታወቀውን ይህንን ሰብዓዊ ኮምፒውተር ሞዴል አድርጎ ነው እኮ ኮምፒውተር የተፈለሰፈው
ከሰማይ በታች ሁሉን የማድረግ አቅም ከፈጣሪው የተሰጠው ይህ አዕምሮ ብለን የምንጠራው ግዙፍ ተፈጥሯዊ ኮምፒውተር ታዲያ ብዙዎቻችን በየቦርሳችን ውስጥ ይዘን በየቀኑ ከምንጠቀምበት መሳሪያችን ጋር ተመሳሳይ ነውለዚያም ነው አሰራራቸው አንድ በመሆኑ የኃያሉን ተፈጥሯዊ ኮምፒውተራችንን አሠራር ለመገንዘብ ከሰው ሰራሹ ኮምፒውተር መነሳት የወደድነውምክንያቱም ብዙዎቻችን በተለይም የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች የኮምፒውተር አሠራርን በደንብ የምንናውቀው በመሆናችን ከዚሁ ብንነሳ የገዛ አዕምሯችንን አሠራር ለማወቅ ስለሚቀል ነውአዕምሮ የሚሠራው ኮምፒውተር በሚሠራበት መንገድ ነውና
በዚህ ከተግባባን የኮምፒውተር አሠራር ደግሞ “Garbage In Garbage Out” በሚባል መሰረታዊ የአሠራር ህግ ላይ የተመሰረተ ነውይኸውም “ትክክለኛ ግብዓት ትክክለኛ ውጤት” እንደማለት ነው ህጉ በአማርኛችን ሲተረጎምማለትም ለኮምፒውተራችን ትክክለኛውን ዳታ ስንሰጠው የምንፈልገውን ትክክለኛውን ውጤት ይሰጠናል፤ የተሳሳተ መረጃ ከሰጠነው ደግሞ የምናገኘው ውጤትም ያው የተሳሳተ ይሆናል፡፡
በሌላ አነጋገር ኮምፒውተራችን የምናገኘው ውጤት እኛ የሰጠነው ነው፤ ትክክለኛም ሆነ የተሳሳተ የምናገኘው ውጤት ሁሉ እኛ ለኮምፒውተሩ ያቀበልነው ነው እንጂ እርሱ በራሱ የሚፈጥረው አይደለምያልሰጠነውን አይሰጠንም
እናም በኮምፒውተራችን አማካኝነት ሥራችንን ስናከናውን ኮምፒውተራችን “ቢሳሳት” ለተሰራው ስህተት ተጠያቂው እኛ እንጂ ኮምፒውተሩ አይደለምምንጊዜም ቢሆን እርሱ የሚሰራው እኛ በምንሰጠው ግብዓት ላይ ተመስርቶ ነውና፤ በህጉ መሰረት የተሳሳተ መረጃ ባንሰጠው እርሱም አይሳሳትም ነበርና!
የአዕምሯችን አሠራርም እንዲሁ ነው! በአዕምሯችን መልካም ነገሮችን ስናስብ በህይወታችን ውስጥ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ፣ መጥፎ መጥፎውን ስናስብም መጥፎ ነገሮች ይገጥሙናልደስታን ስናስብ ደስታን፣ ሰላምን ስናስብ ሰላምን፣ ክፋት ስናስብ ክፋትን፣ ጦርነትን ስናስብ ጦርነትን እንጠራለንበአዕምሯችን ያሳሰብነውን መቼም አንሆንም፣ ያልተመኘነውንም መቼም አናገኝም፣ ስለ ፍቅር እያሰብን ጥላቻን ከሚያራምዱ ጋር ልንገጥም፣ ሰላም ናፋቂ ሆነን ጦርነት ውስጥ ልንገባ አንችልምወደድንም ጠላንም፣ ተቀበልነውም አልተቀበልነውም ይህ እውነት ነው ህጉ ሲጠቃለል ልክ እንደ “Garbage In Garbage Out”፣ መልካም ስታስብ መልካም፣ ክፉ ስታስብ ክፉውን ታገኛለህ” በሚል መሰረታዊ ህግ ላይ የተመሰረተ ሆኖ እናገኘዋለንከትውፊት እስከ ባህል፣ ከሳይንስ እስከ ሃይማኖት፣ ከፍልስፍና እስከ ሥነ ልቦና…ሁሉም ያረጋገጡትም ይህንኑ ነውተመልከቱ፤ “ቸር ተመኝ፣ ቸር እንድታገኝ” በማህበረሰባችን ውስጥ ዘወትር እየሰማነው ያደግነው ብሂል ነውይህ “መልካም ነገሮችን ስታስብ መልካም ነገሮች፣ መጥፎ መጥፎውን ስታስብ ደግሞ በህይወትህ ውስጥ መጥፎ ነገሮችን ትፈጥራለህ” ከሚለው የአዕምሮ አሠራር ህግ ጋር በቀጥታ የሚዛመድ ነው፡፡
በሃይማኖቱ ብትሄድ “ሰው በልቡ የሚያስበውን እንዲሁ ደግሞ ይሆናል” በሚል በግልጽ ተቀመጦ ታገኘዋለህሳይንስ በበኩሉ “Negative energy creates negative vibes, positive energy creates positive ones” በማለት ሲገልጸው ዲበ አካላዊ የሆነውን የአፅናፈ ዓለም ክፍል የሚያጠናው ረቂቃዊው ሳይንስ ወይም ሜታ ፊዚክስ፣ የሥነ ልቦናና የሥነ አዕምሮ የዕውቀት ዘርፎች ደግሞ “ሃሳብ ተመሳሳዩን ይስባል” በማለት “የስበት ህግ” በሚል ይህንኑ ህግ በሌላ አገላለጽ ያስቀምጡታል
የማይታመን የሚመስለውን ይህንን አስደናቂ የአዕምሮ አሰራር ህግን አስመልክቶ “ምስጢሩ” በተሰኘው በዝነኛዋ የሮሆንዳ ባይንሬ መጽሃፍ ውስጥ የተካተተው ታዋቂው የዘመናችን አሳቢ ቦብ ፕሮክተር እንዲህ ይላል“የትም ሁን፤ ህንድ፣ አውስትራሊያ፣ ኒውዚላንድ፣ ስቶክሆልም፣ ለንደን፣ ቶሮንቶ፣ አዲስ አበባ ወይም ኒውዮርክ ሁላችንም የምንሰራው በአንድ ኃይል ነውበአንድ ህግ ነው- እርሱም የስበት ህግ ነውወደ ህይወትህ የሚመጣ ማንኛውንም ነገር ወደ ህይወትህ የሳብከው አንተው ነህወደ አንተ የተሳበውም በአዕምሮህ ውስጥ ስለህ በያዝካቸው ምስሎች አማካኝነት ነው
በመሆኑም በአዕምሮህ እያሰብከውና እያውጠነጠንከው ያለኸው ማንኛውም ነገር ወደ አንተ እየሳብከው መሆኑን ተረዳ”የምስጢሩ ደራሲ ትቀጥልና “የስበት ህግ የዓለማችን እጅግ ሃይለኛው ህግ መሆኑን በህይወት የነበሩ እጅግ ታላላቆቹ መምህራን ነግረውናል” ትለናለችእንደ ዊሊያም ሸክስፒር፣ ሮበርት ብራውኒንግና ዊሊያም ብሌክ የመሳሰሉት ገጣሚያን በግጥሞቻቸው ብለውታልእንደ ሉድ ቫን ቬቶቨን የመሳሰሉት ሙዚቀኞች በዘፈናቸው ገልጸውታልእንደ ሊዮናርዶ ዳቬንች የመሳሰሉ ሰዓሊያን በስዕሎቻቸው አመላክተውታልሶቅራጥስ፣ ፕሌቶ፣ ኤመርሰን፣ ፓይታጎረስ፣ ሰር ፍራንሲስ ቤከን፣ ሰር አይዛክ ኒውተን፣ ዮሐንስ ወልፍጋንግ ቮን ጎተና ቪክተር ሁጎን የመሳሰሉ ፈላስፋዎች በጽሁፎቻቸውና በአስተምህሮወቻቸው አዳርሰውታልየሁሉም ስሞች ህያው ናቸውበታሪክም ሁሌም እንደተዘከሩ ይኖራሉ፡፡
እንደ ሂንዱይዝም፣ የሄርሜቲክ ልማዶች፣ የቡድሃ፣ የአይሁድ፣ የክርስትናና እስልምና ሃይማኖቶች የአስተምሮቻቸው አካል አድርገው ሰብከውታልየባቢሎን፣ የግብጽና ሌሎችም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ጽፈው አስተላልፈውታልበሁሉም ዘመናት የተደረጉ ጥናታዊ ጽሁፎች በተለያየ መንገድ ዘግበውታልከክርስቶስ ልደት በፊት በሦስት ሺህ ዓመተ ዓለም በድንጋይ ላይ ተጽፎ ተገኝቷልህጉ ከጊዜ ጋር የጀመረ ነውሁልጊዜም እዛው የነበረና የሚኖር ነውየዓለምን ሥርዓት፣ የህይወት ተሞክሮህን የሚወስን ህግ ነውየትም ሁን ማን የስበት ህግ የህይወትህን ተሞክሮ የሚሰራው እርሱ ነው፡፡
ይህ ኃያል ህግ ይህን ሁሉ የሚያደርገው በሃሳቦችህ አማካኝነት ነውእናም ክፉም ይሁኑ በጎ በህይወትህ የሚፈጠሩ ነገሮች ሁሉ የአስተሳሰብህ ውጤቶች ናቸው፣ የህይወትህ ፈጣሪ በአዕምሮህ ውስጥ የምታውጠነጥነው ሃሳብህ ነውመጥፎ ስታስብ መጥፎ፣ መልካም ስታስብ መልካም ነገሮችን ትፈጥራለህGarbage In Garbage Out” ለኮምፒውተር “Garbage Idea Garbaje Life” ለሰው! ይኸው ነውሰው በልቦናው እንደሚያስበው እንዲሁ ነውና!
ይበል ካሳ
አዲስ ዘመን መስከረም 21/2015 ዓ.ም