በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የክለቦች ቻምፒዮና ተሳታፊ በመሆን ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ፤ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን ዛሬ ከብሩንዲው ፎፊላ ፒኤፍ ጋር ያደርጋል። ከጠንካራ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ጨዋታውን በአሸናፊነት እንደሚያጠናቅቅም ይጠበቃል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ካለፈው ዓመት አንስቶ እንዲጀመሩ ካደረጋቸው ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ቻምፒዮና ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ እየተካሄደ ሲሆን፤ ዛሬ የምድብ አንድ ሁለተኛ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ከብሩንዲ አቻው ፎፊላ ፒኤፍ ጋር ይጫወታል። የምድቡ ሌላኛው ጨዋታ ደግሞ በሩዋንዳው ኤኤስ ኪጋሊ እና የዛንዚባር ዋሪየርስ ኩዊንስ ክለቦች መካከል ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ አምና በኬንያ አስተናጋጅነት በተደረገው ቻምፒዮና ላይ ዋንጫ ለማንሳት ቢቃረብም ስላልተሳካለት በሁለተኛነት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ ንግድ ባንክ የዚህ ዓመት የቀጣናው አሸናፊ በመሆን ወደ አህጉራዊው ቻምፒዮና ለማለፍ ራሱን አጠናክሮ ወደ ውድድሩ ገብቷል። ለዚህም ስድስት ተጫዋቾችን ከሀገር ውስጥ ክለቦች ማስፈረሙ የሚታወስ ነው። ክለቡ ከነሀሴ 7 እስከ 22 ቀን 2014 ዓም በሚካሄድው ቻምፒዮና ላይ ውጤታማ ለመሆን አራያት ኦዶንግ፣ ኒቦኚ የን፣ ቅድስት ዘለቀ፣ መሳይ ተመስገን፣ ብርቄ አማረ እና ናርዶስ ጌትነትን ማስፈረሙ ይታወቃል። ጠንካራ የሴት እግር ኳስ ቡድኖች እምብዛም በሌለበት በዚህ ቃጠና ንግድ ባንክ ካለው ልምድና ጠንካራ ተጫዋቾች አንጻር የዛሬውን ጨዋታ እንዲሁም ውድድሩን በአሸናፊነት እንደሚያጠናቅቅም ይገመታል።
ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ክለቦች ቻምፒዮና በታንዛኒያዋ ከተማ አሩሻ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ቀናትን አስቆጥሯል። በውድድሩ ላይ ስምንት ቡድኖች ተካፋይ ሲሆኑ፤ በሁለት ምድብ ተከፍለውም የዋንጫ ፍልሚያቸውን ያደርጋሉ። በዚህም መሰረት በመጀመሪያው ምድብ የኢትዮጵያውን ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ጨምሮ፤ የዛንዚባሩ ዋሪየርስ ኩዊንስ፣ የብሩንዲው ፎፊላ ፒኤፍ እና የሩዋንዳው ኤኤስ ኪጋሊ ተደልድለዋል። በሌላኛው ምድብ ደግሞ የአዘጋጇ ሃገር ታንዛኒያ ክለብ የሆነው ሲምባ ኩዊንስ፣ የጅቡቲው ጋርዴ ሪፐብሊካን፣ የዩጋንዳው ሲ ኮርፖሬት እንዲሁም የደቡብ አፍሪካው ዬ ጆይንት ስታርስ ይገኛሉ።
የምድብ ጨዋታዎቹ በሳምንቱ መጀመሪያ አንስቶ እየተካሄደ ሲሆን፤ የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ በከፍተኛ የግብ ብልጫ ድል ተቀዳጅቷል። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ከዛንዚባሩ ዋሪየርስ ኩዊንስ ጋር የተገናኘው ንግድ ባንክ 9 ለምንም በሆነ ውጤት ነበር ተጋጣሚውን የረታው። በጨዋታው ሁለት ተጫዋቾች ሃትሪክ የሰሩ ሲሆን፤ አምበሏ ሎዛ አበራ 5 ግቦችን ከመረብ ስታሳርፍ ሌላኛዋ ተጫዋች መዲና አወል ደግሞ 4 ግቦችን ከመረብ ማዋሃዳቸው የሚታወስ ነው። ይህም ተጫዋቾቹን ገና ከውድድሩ ጅማሬ አንስቶ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ሊያደርጋቸው ችሏል።
በቻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያ ከንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን ባሻገር በዓለም አቀድ ዳኞቿም እየተወከለች ትገኛለች። እነርሱም በካፍ ጥሪ መሰረት በዋና ዳኝነት ጨዋታዎችን የምትመራው ጸሃይነሽ አበበ እንዲሁም ረዳት ዳኛ ወይንሸት አበራ ናቸው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ኬኒያ ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የመጀመሪያው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ክለቦች ቻምፒዮና ላይ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ የኬንያው ቪጋ ኩዊንስ አሸናፊ ነበር። በቻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ 13 ግቦችን በስሟ በማስቆጠር ቀዳሚ ተጫዋች እንደነበረች ይታወሳል።
እርምጃ የመውሰድ ስራ ሲሰራ የነበረ ቢሆንም፤ የህብረተሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ በቀጣይ በጀት ዓመትም የቅንጅት ስራውን በማጠናከር በሕገወጥ ምግብና የጤና ግብዓቶች ዝውውር ላይ የተሰማሩ አካላትንና ግለሰቦችን ወደ ሕግ አቅርቦ ማስቀጣት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ በገምገማው ማጠቃለያ ላይ በሰጡት አቅጣጫ፣ ‹‹በቀጣይ በ2015 በጀት አመት ተቋማዊ ግንባታን በማጠናከርና ስትራቴጂክ ዕቅዶች መሰረት በማድረግ ስራዎች መስራት እንደሚገባና ቁጠባን መሰረት ያደረገ ከብክነት የጸዳ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ስራዎችን በልህቀት በመስራት፣ የእርምት ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ፣ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በቁርጠኝነት በመታገል ወደ ልህቀት የሚደረገውን ጉዞ ለማሳካት ጠንክሮ በመሰራት አርአያ የሚሆን ተቋም መገንባት አለብን››ብለዋል፡፡
እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጎልበት በምግብ፣በጤና ግብዓቶች እና ሌሎች የጤና ጉዳት በሚያደርሱ ቁጥጥር በሚደረግባቸው ምርቶች ዙሪያ የሚደርጉ ቁጥጥሮችን ውጤታማ በማድረግ በህብረተሰቡ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ቀድሞ በመከላከል ሃላፊነት መዋጣት እንደሚገባም አጽእኖት ሰጥተውታል፡፡ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የባለስልጣኑ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማም፣ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት ግምገማው በስኬት ተጠናቋል።
ብርሃን ፈይሳ
አዲስ ዘመን ነሐሴ 12 /2014