የኢኮኖሚ ምሁራን የካፒታል ገበያን አስፈላጊነት ከሀብት ክፍፍልና ከኢኮኖሚ ፋይዳው አንጻር አጉልተው ያነሱታል። በሌላ በኩል፤ ለታዳጊ አገራት አያስፈልግም፤ በገበያው የሚሳተፉት ኩባንያዎች ውስን ስለሚሆኑ ለልማት የሚያመጣውም የረባ ጥቅም የለም ሲሉ የሚሞግቱ ምሁራንም አሉ።
የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ክቡር ገና የካፒታል ገበያ ለኢትዮጵያ አያስፈልግም ይላሉ። እንዲህ የሚሉበት ምክንያትም አንደኛ፤ በተለያዩ ምክንያቶች በካፒታል ገበያ (ስቶክ ኤክስቼንጅ ማርኬት) የሚሳተፉ ኩባንያዎች ውስን ይሆናሉ የሚል ስጋት ስላላቸው ነው። በገበያው ላይ ለመሳተፍ ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች መካከል ሕጎችና ደንቦች ማክበር፤ ታክስ በአግባቡ መክፈልና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሂሳብ አያያዝ መኖር የሚሉት ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኩባንያዎች በጣም ውስን ናቸው። አብዛኛዎቹ ኩባንያዎች ታክስ በመፍራት ብዙ አተረፍን ማለት አይወዱም። በዚህ ምክንያት ብዙ ኩባንያዎች በካፒታል ገበያ ውስጥ ላይሳተፉ ስለሚችሉ የገበያው አስፈላጊነት ብዙም አይደለ ይላሉ።
በጥቅሉ የካፒታል ገበያ እንደየአገሩ፤ ጊዜውና አስፈላጊነቱ ሊለያይ ቢችልም፤ በታዳጊ አገራት በገበያው የሚሳተፉ ድርጅቶች ውስን በመሆናቸው ለልማትና ለሀብት ክፍፍል የሚኖረው ሚና አናሳ ነው፤ የሚል መከራከሪያም ክቡር ገና ያነሳሉ።
ለምሳሌ፤ የካፒታል ገበያ ያላቸው የአፍሪካ አገራት ለኢኮኖሚው ሊወራለትና ሊጻፍ የሚችል ጥቅም እያገኙ አይደለም። ምክንያቱ ደግሞ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ኩባንያዎች ያላቸው የፋይናንስ ሥርዓት የተዝረከረከ ነው። 19 የአፍሪካ አገሮች የካፒታል ገበያ አላቸው። በተለይ
የደቡብ አፍሪካው ከታዳጊ አገሮች አኳያ ትልቅ ገበያ ቢሆንም፤ በዓለም ካሉት ትላልቅ የካፒታል ገበያዎች ተርታ ግን አይመደብም።
በሌሎቹ የአፍሪካ አገራት ያሉት 18 የካፒታል ገበያዎችም በጣም ትንንሽ የሚባሉ ናቸው። ምክንያቱም፤ የሚንቀሳቀሱት የተወሰኑ ድርጅቶችን ይዘው ነው። የገበያ ካፒታላቸውና እንቅስቃሴያቸውም በጣም አነስተኛና ውስን በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸውም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በኢትዮጵያም ገበያው ቢኖር ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም ብለዋል።
ሁለተኛ፤ የካፒታል ገበያ ለውጭ ኩባንያዎች ከተፈቀደ አክሲዮኖችን በመሸጥ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ለሌላ ልማት ሊውል ይችላል የሚል መከራከሪያ ነጥብ ቢነሳም ውሃ የሚያነሳ እሳቤ አይደለም፤ ሲሉ ክቡር ገና ይሞግታሉ። ምክንያቱም በካፒታል ገበያው የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ ትልልቅ ኩባንያዎች ያስፈልጋሉና፤
‹‹የፌር ፋክስ አፍሪካ ፈንድ›› የተባለ የአሜሪካ ኢንቨስትመንት ዓለም አቀፍ ኩባንያ ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ፤ የካፒታል ገበያ ለኢትዮጵያ አያስፈልግም የሚለውን የክቡር ገናን ሃሳብ ይቃወማሉ። ግልጽ የሆነ የሂሳብ አያያዝና በቂ ድርጅቶች ስለሌሉ የአክሲዮን ገበያ አያስፈልግም የሚለው ሃሳብ ተቀባይነት የለውም።‹‹ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም›› እንደሚባለው ሁሉም ነገሮች አልተሟሉም ብሎ ቁጭ ማለት ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ያሉት ኢንቨስትመንቶች ከፍተኛ ካፒታል የሚጠይቁ ናቸው።
አሁን ባለው ሁኔታ ለምሳሌ፤ በኢትዮጵያ በካፒታል (አክሲዮን) ገበያው ላይ መስፈርቱን አሟልተው የአክሲዮን ድርሻ (ሼር) መሸጥ የሚችሉት ትልልቅ የግል ኩባንያዎችና መንግሥት ወደ ግል የሚያዛውራቸው ድርጅቶችንም ጨምሮ 16ቱ ባንኮችና 16ቱ ኢንሹራንስ ድርጅቶች ናቸው። ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸውና በብዙ መቶ ሺህ የአክሲዮን ድርሻ የሸጡ ናቸው።
የኢትዮጵያ ባንኮች በ25 ዓመታት ጊዜ ውስጥ አክሲዮን በመሸጥ ማሰባሰብ የቻሉት 30 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው። ይህ በጣም ትንሽ ገንዘብ ነው። ከሰሀራ በታች ሦስተኛ ትልቅ ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ ናት። ይህም ሆኖ የኢትዮጵያ ባንኮች አጠቃላይ ካፒታላቸው አንድ ቢሊዮን ዶላር ነው። እናም የተደራጀ የካፒታል ገበያ በሚኖርበት ጊዜ በቀላሉ የአክሲዮንን ድርሻ (ሼር) በመሸጥ ከፍተኛ ካፒታል መሰብሰብ ይችላሉ። እናም በገበያው ላይ የሚሳተፉ ኩባንያዎች ውስን ናቸው ብሎ አያስፈልግም ከማለት፤ በተወሰኑት ድርጅቶች ተጀምሮ ቀስ በቀስ ሌሎች ኩባንያዎች እየተዘጋጁና ጥቅሙን እያዩ ሲሄዱ ወደ ገበያው እየተቀላቀሉና እየበዙ ይሄዳሉ፤ ሲሉ አቶ ዘመዴነህ ይሞግታሉ።
ሌላው የክቡር ገና መከራከሪያ ነጥብ ደግሞ በኢትዮጵያ አብዛኛው ሰው የአክሲዮን ድርሻ በእጁ የለም። የካፒታል ገበያ ያስፈልጋል የሚሉትም የአክሲዮን ድርሻ በእጃቸው ያለና የተለየ ደረጃ የተቀመጡ ውስን ግለሰቦች ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች በፈለጉ ጊዜ የአክሲዮን ድርሻቸውን ወደ ገንዘብ ሊቀይሩ የሚችሉበት መንገድ ስለሌለ ይህ ይመቻች የሚል ሃሳብ ነው የሚያነሱት። ለዚህ ብቻ የሚውል የካፒታል ገበያ ደግሞ ምንም ጥቅም አይኖረውም።
አቶ ዘመዴነህ በተጨማሪ፤ የካፒታል ገበያ አሁን አያስፈልግም የሚለውን የክቡር ገናን ሃሳብ አይቀበሉትም። በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ካፒታል የሚፈልጉ ብዙ የግል ኩባንያዎች አሉ። ለምሳሌ፤ በአሁኑ ጊዜ ሕጋዊና ግልጽ ባልሆነ መንገድ የባንክና የኢንሹራንስ የአክሲዮን ድርሻ በየቀኑ እየተገዛና እየተሸጠ ነው። እናም ሕጋዊና የተደራጀ የካፒታል ገበያ አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም።
ሌላው፤ መንግሥት እንደ ኢትዮ ቴሌኮም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤሌክትሪክ ኃይል ያሉ መሰል የመንግሥት ትልልቅ ኩባንያዎች አክሲዮናቸው እንዲሸጥ ወስኗል። ተቋማቱ በአዲስ አበባ የካፒታል
ገበያ ላይ ቢሸጡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ባለድርሻ መሆን ይችላሉ። ለዚህ ነው የካፒታል ገበያ የሀብት ክፍፍል ያመጣል የሚባለው።
ክቡር ገና የካፒታል ገበያ አያስፈልግም ሲሉ ሌላም ማጠናከሪያ ሃሳብ አላቸው። በአሁኑ ጊዜ የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ የሚፈለገው ኢንቨስትመንት እንዲስብ ነው። ምክንያቱም፤ ኢንቨስተሩ የአክሲዮን ድርሻውን ይሸጣል ወይም ይገዛል። ሆኖም ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት እያደገ ከሚገኝባቸው የዓለም አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። በኢትዮጵያም ብዙ ኩባንያዎች መጥተው ፋብሪካ እየከፈቱ ይገኛሉ። እናም በዚህ ሁኔታ ኢንቨስትመንትን መሳብ ከተቻለ የካፒታል ገበያው መኖር የሚያመጣው ብዙም ለውጥ አይኖርም።
አቶ ዘመዴነህ የዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን ከመሳብ አኳያ የተለየ አተያይ አላቸው። ብዙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት እያደረጉ ነው። ለምሳሌ፤ ዲያጆ ኬንያና ናይጀሪያ ባሉት የንግድ ተቋማቱ የአክሲዮን ድርሻውን በሁለቱ አገር ባለው የአክሲዮን ገበያ ይሸጣል። በዚህም ናይጀሪያውያንም ሆኑ ኬንያውያን የአክሲዮን ድርሻ የመግዛት ዕድል አላቸው። በኢትዮጵያም የካፒታል ገበያ ቢኖር የዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን ድርሻ (ሼር) በመግዛት ኩባንያው ከሚያተርፈው ትርፍ ውስጥ የድርሻቸውን ያህል የመጠቀም ዕድል ይኖራቸዋል።
ሌላው በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ኩባንያዎች ለመቋቋም፤ ለማደግና በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ካፒታል ይፈልጋሉ። በሕግ የተቋቋመ፤ ልክ የምርት ገበያ የግብርና ምርቶችን እንደሚያገበያየው ሁሉ ለአክሲዮኖች ድርሻ የሚሸጥበትና የሚገዛበት የተደራጀ ገበያ ቢኖር የሕዝቡን፤ በተለይ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች ተጠቃሚነት ከፍ ያደርጋል። ጊዜንም ይቆጥባል። በአጭር ጊዜ ውስጥም ብዙ ካፒታል ማሰባሰብ ያስችላል፤ ሲሉ አቶ ዘመዴነህ የካፒታል ገበያን ጥቅም ያብራራሉ።
የፋይናንስ ባለሙያው አቶ ዛፉ እየሱስ ወርቅ ዛፉ በበኩላቸው፤ የካፒታል ገበያ አስፈላጊነት የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም ይላሉ። ምክንያቱም ካፒታል ለማሰባሰብና ትልቅ ኩባንያዎችን ለመፍጠር የካፒታል ገበያ ትልቅ ጥቅም አለው። ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ መንግሥት የካፒታል ገበያ እንዲፈጠር እየተቀሳቀሰ የሚገኘው ብለዋል።
የአቶ ዘመዴነህ ምክረ ሃሳብ የካፒታል ገበያ ከመጀመሩ በፊት የኢንቨስተሩን ጥቅም የሚጠብቅና በየቀኑ የሚደረገውን ግብይት የሚቆጣጠር የመንግሥት ድርጅት ያስፈልጋል። ገበያውን ሥርዓት የሚያሲዙ ሕግና ደንቦች መውጣት አለባቸው። ኩባንያዎች ወደ ካፒታል ገበያ በሚመጡበት ጊዜ ፈቃድና ክህሎቱ ያላቸውና በደንበኛቸው ስም በየቀኑ የአክሲዮን ድርሻ የሚገዙና የሚሸጡ የአክሲዮን ደላሎች ያስፈልጋሉ። ኩባንያዎቹ የአክሲዮን ድርሻ ከመሸጣቸው በፊት ለገበያ ብቁ መሆናቸውን መስፈርት የሚያዘጋጅ የኢንቨስትመንት ባንክ መቋቋም አለበት የሚል ነው።
በኢትዮጵያም በ1952 ዓ.ም የአክሲዮን ማህበራት የሚተዳደሩበት የንግድ ሕግ ወጥቶ የስኳር ፋብሪካዎች የአክሲዮን ድርሻዎችን በመሸጥ የአክሲዮን ገበያ ቢጀመርም ብዙ ርቀት ሳይጓዝ በደርግ መንግሥት ተቀጭቷል። ኢትዮጵያ ገበያ መር ኢኮኖሚ መከተል ከጀመረች ከ1985 ዓ.ም ወዲህ እስካሁን ድረስ አንድ ሺህ የሚደርሱ የአክሲዮን ማህበራት ቢኖሩም ማህበራቱ የአክሲዮን ድርሻቸውን መሸጥ ቢፈልጉ የሚሸጡበት የካፒታል ገበያ (የስቶክ ኤክስቼንጅ ማርኬት) የለም። በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እኤአ 2020 ኢትዮጵያ ውስጥ የካፒታል ገበያ እንደሚኖር ይፋ አድርገዋል።
ስለዚህ፤ በካፒታል ገበያ ለመሳተፍና የጥቅሙ ተጋሪ ለመሆን የሚፈልጉ ኩባንያዎች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ አለባቸው። መንግሥትም በእጁ የሚገኙትን ትልልቅ ተቋማት በየደረጃው ወደግል ይዞታ እንደሚያዛውር በያዘው እቅድ መሠረት የካፒታል ገበያ የሚጀመርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርበታል።
ከፍታ ያለው ማንኛውም ህንፃ የአሳንሰር ወይንም ተመሳሳይ አገልግሎት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። ነገር ግን እነዚህና መሰል አዋጆች ተግባራዊ ባለመሆናቸው ዜጎች በተለይም አካል ጉዳተኞች በየጊዜው ደህንነታቸው አደጋ ላይ ሲወድቅ ይታያል።
የየዕለት እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ በዊልቸር እገዛ የሆነው አካል ጉዳተኛ ወጣት አቤኔዘር እዝቅኤል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ ነው። ወጣቱ እንደገለፀውም፤ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥም ሆነ ከግቢ ውጪ ያለው እንቅስቃሴ በተለይም ለአካል ጉዳተኞች እጅግ ፈታኝ ነው። አጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ብዙ ችግሮች አሉ። አካል ጉዳተኞች በየትም ቦታ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ
አዲስ ዘመን መጋቢት18/2011
በጌትነት ምህረቴ �I`wWF˩