አዳማ፡- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስል ጠና ዘርፉ ለህብረተሰቡ ውጤት በሚያመጣ የተግባር ተኮር ስራ ላይ ማተኮር እንደሚገባ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒ ስቴር አሳሰበ፡፡ ዘርፉ አማራጮችና ተግባራት ላይ ማተኮር እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም፣ የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ የቀጣይ እጣ ፈንታ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ላይ ያረፈ ነው፡፡ ስለዚህ በዘርፉ መሬት ሊወርድ የሚችል ተግባር ለማከናወን ጥናትና ምርምሮች ላይ ያተኮረ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለው ይህም ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ለማምጣት ይረዳል፡፡
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፤ በአገራት መካከል የተፈጠረው የኢኮኖሚ እድገት ልዩነት በት ምህርትና ስልጠና ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የእደ ጥበብ ስራዎች የዚህ ዘርፍ ውጤቶች እንደመሆናቸው፤ ኢንዱስትሪው በዘርፉ ላይ ያለውን አመኔታ ማነስ ሂደት መቀየር የሚያስችል ተግባር ማከናወን፤ ለዚህ ደግሞ ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ እውቀቶችን ጭምር በጥናት አስደግፎ በማሳደግና ከዘመኑ ጋር በማዋሀድ መስራት ያስፈልጋል፡፡
ከመሰረተ ልማት፣ ፋይናንስና ቴክኖሎጂ ጋር ያሉ ክፍተቶች በአንድ ጀንበር አይፈ ቱም፡፡ ይልቁንም ከዘመኑ ጋር አብረው እያደጉና እየጨመሩ የሚሄዱ መሆኑን ተገንዝቦ ከዩኒቨርሲቲዎችና ኢንዱስትሪዎች ጋር ጠንካራ ትስስር ፈጥሮ መስራት ይገባል ሲሉ ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው ዘርፉ የሚመራበት ውጤት ተኮር አገር አቀፍ ስትራቴጂ ብቃት ያለው፣ የተለወጠ፣ የፈጠራ ባለቤትና ከወቅቱ ጋር የሚራመድ አቅም የጨበጠ ዜጋን በመፍጠር የአገሪቱን እድገት ማፋጠን ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ዘርፉ የተደራሽነት፣ የአቅም፣ የክህ ሎት፣ የቴክኖሎጂና ሌሎችም በርካታ ያልተሻገራቸው ችግሮችም አሉበት ብለው እነዚህን ችግሮች በጋራ በመቅረፍም በጋራ ለላቀ ውጤት መረባረብ፤ የተናበበና የተቀናጀ ስትራቴጂያዊ አመራር መስጠት የግድ ይላል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 5/2011
በወንድወሰን ሽመልስ
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ