
በሩሲያና ዩክሬን የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በበርሜል 105 ዶላር መድረሱን ተሰማ።የስንዴ እና የበቆሎ ገበያዎችም የአምስት በመቶ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡
ጭማሪው ባለፈው ሰባት ዓመታት ከተስተዋሉ ጭማሪዎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ጭማሪ መሆኑንም ነው የተገለጸው፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ በዩክሬን የተፈጠረው ሁኔታ በርካታ የዓለም አክሲዮኖች ከስረዋል እንዲሁም የወርቅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
የዩክሬን ትርምስ ከነዳጅ ባሻገር ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ መስተጓጎል መፍጠሩንም የብሉምበርግ መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም ሩሲያ ወደ ዩክሬን መግባቷንና በዚህም ወደቦች እና የባቡር ሀዲዶች መዘጋታቸውን ተከትሎ የምግብ ምርቶች የሚጫኑባቸው የትራንስፖርት ማሽነሪዎች ለመቆም ተገደዋል ተብሏል፡፡
በሩሲያና ዩክሬን መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ እስካሁን ወደቦቿ መዘጋታቸውንና ነጋዴዎች ዕቃዎቻቸውን ወደ አገሪቱ ወደቦች ለማዘዋወር እና ለማውጣት መርከቦችን መጠቀም አለመቻላቸው የአገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡
የለም አፈር አገር እንደሆነች የሚነግርላትና “የአውሮፓ የዳቦ ቅርጫት” በሚል ቅጽል ስም በምትታወቀው ዩክሬን ሁለተኛዋ ትልቁ የዓለም እህል እና ዋና የሱፍ አበባ ዘይት ላኪ በጋዜጣው ሪፖርተር የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን አገሪቱ ስትጠቀምበት የቆየውን የግሪጎሪያን የቀን መቁጠሪያ (ካላንድር) በአያታቸው የልደት ቀን እንዲተካ መወሰናቸው ተሰምቷል። ከ1992 የሚጀምረው አዲሱ ቀን መቁጠሪያ፤ ዘንድሮ “ጁች 111” በሚል ይጠራል ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት አገሪቱ የግሪጎሪያን አቆጣጠርን ከቀን አቆጣጠር ስርዓቷ ያወጣች ሲሆን፤ አሁን ያለንበትን የፈረንጆቹን 2022 ዓመትንም ሰርዛለች። ይህንን ተከትሎም የሰሜን ኮሪያ የዜና ኤጀንሲ የግሪጎሪያን የቀን አቆጣጠርን በመተው በሰሜን ኮሪያው መሪ አያት ልደት ቀን የሚጀምረውን የቀን አቆጣጠር መጠቀም መሆኗ ይታወቃል፡፡ አገሪቱ የምታመርታቸው ምርቶች ለማንቀሳቀስ የባቡር እና የወደብ መሠረተ ልማት የሚያስፈልጋቸው ግዙፍ ዕቃዎች እንደሆኑም ይነገራል።
ሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ ከመጀመሯ በፊት ሁኔታው ያሰጋቸው አንዳንድ የአውሮፓ ባንኮችም በሩሲያ እና በዩክሬን የሸቀጦች ንግድ ላይ ገደብ ሲጥሉ ቆይቷል፡፡ እንደተሰጋው አልቀረም አሁን ላይ ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯን ተከትሎ ወሳኝ የግብርና ምርቶቸ ላይ የዋጋ ንረት እየተስተዋለ ነው፡፡
የስንዴ እና የበቆሎ ገበያዎች በቺካጎ ልውውጥ በሚፈቀደው ከፍተኛ መጠን ጨምረዋል፣ የሁለቱም ሰብሎች ዋጋ ከ5% በላይ እየላቀ ሲሆን በፓሪስ ያለው የስንዴ ዋጋ በ16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በጥቁር ባህር (Black Sea) እና በሌሎች ቦታዎች ላይ ያሉ የሩሲያ ወደቦች የተለመደ እንቅስቃሴ ቢኖርም፤ በአዞቭ ባህር ውስጥ የነበረው የመርከብ ጭነት አገልግሎት መቆሙ የሩሲያ የፌዴራል ወንዝ እና የባህር ውስጥ ትራንስፖርት ኤጀንሲ አስታውቋል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬኗ ምስራቅ ዶንባስ ክልል ጦራቸውን በማስማራት ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማስጀመራቸው ትናንት ምሽት በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ዛሬም ቀጥሎ የዋለው ወታደራዊ ዘመቻ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዋና አጀንዳ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን የካቲት 19 /2014