አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በ11ኛው ጉባኤ ግንባሩ የሚመራበትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም ለማጎልበት አቅጣጫ ማስቀመጡን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ገለጹ፡፡
ግንባሩ ላለፉት 27 ዓመታት ሲመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚተካ ርዕዮተ ዓለም ተጠንቶ ለመጪው ጉባኤ እንዲቀርብ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፏል ተብሎ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ ስህተትና በጉባኤው ሪፖርት የሌለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
እንደ ኃላፊዋ ማብራሪያ፤ አንዳንድ የግንባሩ አባል ብሄራዊ ድርጅቶች አባላት በጉባኤው ግንባሩ የሚመራበት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራም መለወጥ አለበት የሚል ሀሳብ አንስተው ነበር፡፡
አባላቱ ባነሱት ጥያቄ ዙሪያ በጉባኤተኛው አስተያየት ከሰጠበትና ውይይት ከተደረገበት በኋላ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራምን ይዞ ለመቀጠል ከስምምነት መደረሱን የገለጹት ወይዘሮ ፈትለወርቅ፤ ግንባሩ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አቅጣጫ በመጓዝ ለውጥ ማምጣት እንደሚችልም በሁሉም ዘንድ መግባባት መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
የፕሮግራም ለውጥ ለማድረግ ማሰብ ክልክል እንዳልሆነ ያነሱት ወይዘሮ ፈትለወርቅ፤ በተለያዩ ጊዜያትም ግንባሩ የፕሮግራም ለውጦችን ሲያደርግ እንደነበር አውስተዋል፡፡ የፕሮግራም ማሻሻያዎችን ለማድረግና የሚተካ ርዕዮተ ዓለም እንዲጠና የሚወሰነው ግን በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፕሮግራም ለውጥ ለማድረግ በስሜት ሳይሆን ጥናቶች ሊካሄዱ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
እንደ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ማብራሪያ፤ ከዚህ ቀደም ግንባሩ የፕሮግራም ለውጦችን ሲያደርግ ነበር፡፡ ማሻሻያዎች ሲደረጉ የነበሩት ጥናት ከተካሄደና መላው የድርጅቱ አባላት እንዲሁም ህዝብ እንዲወያይበት ከተደረገ በኋላ ነው፡፡ በርካታ ጥናታዊ ጽሁፎችና ኮንፍረንሶችም ከተካሄዱና መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ ማሻሻያዎች ሲደረግ ነበር፡፡
ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሓላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ በገፅ 11 ይመልከቱ፡፡አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራምን ይዞ ለመቀጠል ከስምምነት መደረሱን የገለጹት ወይዘሮ ፈትለወርቅ፤ ግንባሩ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አቅጣጫ በመጓዝ ለውጥ ማምጣት እንደሚችልም በሁሉም ዘንድ መግባባት መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
የፕሮግራም ለውጥ ለማድረግ ማሰብ ክልክል እንዳልሆነ ያነሱት ወይዘሮ ፈትለወርቅ፤ በተለያዩ ጊዜያትም ግንባሩ የፕሮግራም ለውጦችን ሲያደርግ እንደነበር አውስተዋል፡፡ የፕሮግራም ማሻሻያዎችን ለማድረግና የሚተካ ርዕዮተ ዓለም እንዲጠና የሚወሰነው ግን በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፕሮግራም ለውጥ ለማድረግ በስሜት ሳይሆን ጥናቶች ሊካሄዱ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
እንደ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ማብራሪያ፤ ከዚህ ቀደም ግንባሩ የፕሮግራም ለውጦችን ሲያደርግ ነበር፡፡ ማሻሻያዎች ሲደረጉ የነበሩት ጥናት ከተካሄደና መላው የድርጅቱ አባላት እንዲሁም ህዝብ እንዲወያይበት ከተደረገ በኋላ ነው፡፡ በርካታ ጥናታዊ ጽሁፎችና ኮንፍረንሶችም ከተካሄዱና መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ ማሻሻያዎች ሲደረግ ነበር፡፡
ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሓላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ በገፅ 11 ይመልከቱ፡፡
መላኩ ኤሮሴ