አዲስ አበባ:- የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በዝርዝር ገምግሞ የድርጊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ፡፡
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማጠናቀቁን አስመልክቶ ትናንት ባወጣው መግለጫ ፣ከጥር 07/2011 ዓ.ም ጀምሮ ባደረገው ውይይት የለውጡን ቀጣይነት በማረጋገጥና ተግዳሮቶቹን በመቅረፍ አቢይ አጀንዳ ላይ መምከሩን አስታውቋል። ለውጡ ባስገኛቸው መልካም ውጤቶች፣ ባጋጠሙት ተግዳሮቶችና ወደፊት ሊያጋጥሙ በሚችሉ ሁኔታዎች ላይ በጥልቀት ከመከረ በኋላም የድርጊት አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን አመልክቷል።
ህዝቡ አሁንም ለለውጡ ጠንካራ ድጋፍ እንዳለውና በለውጥ አመራሩ ላይ ትልቅ ተስፋ ማሳደሩን መግለጫው ጠቅሶ፣ሆኖም ግን የደህንነቱን ስጋት የሚጨምሩ ጉዳዮች ስላሉበት የሀገራዊ ሰላም ጉዳይም እንደሚያሳስበው ድርጅቱ መረዳቱን በመግለጫው አስቀምጧል። ስለሆነም ሰላምን በማረጋገጥና የህግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ ሊፈፀሙ የሚገባቸውን አቅጣጫዎች አስቀምጧል።
ሰላምን፣ የህግ የበላይነትንና ፍትህን ማረጋገጥ በተለይም ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ ማድረግ የቀጣይ ቁልፍ ተልዕኮ መሆናቸውን ሥራ አስፈፃሚው አስምሮበታል ያለው መግለጫው፣ ለዚህም በግብርናው በተለይም በመስኖ ልማት ላይ እንዲሁም በኢንዱ ስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የተቀዛቀዘውን ሀገራዊ ኢኮኖሚ ለማነቃቃት መረባረብ ከአስቀመጣቸው አቅጣጫዎች አንዱ ነው።
ማንኛውም ለግጭት እና አለመረጋጋት የሚዳርጉ ሁኔታዎች በግልፅ ተለይተው በአስቸኳይ መታረም እንዳለባቸውና ሁሉም የግንባሩ አባል ድርጅቶች በዝርዝር ተገምግሞ በጋራ በተደረገው ስምምነት መሰረት በተግባር እንዲመሩና መንግሥትም ህግን የማስከበር ቁልፍ ኃላፊነቱን በጥብቅ መወጣት እንደሚገባው አቅጣጫ ማስቀምጡንም በመግለጫው ተመልክ ቷል።
ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ ሌብነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፈፅሞ እንዳይደገሙ በቂ ክትትል ማድረግና ለዚህ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ዝንባሌዎችን በሁሉም የሥራ መስክ እየፈተሹ መጓዝ እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጧል።
በተጨማሪም ኢሕአዴግን እንደ ድርጅት ማጠናከር፣ የሚዲያ፣ የሲቪክ ማህበረሰብና የምሁራንን አቅም መገንባት፣ ሲቪል ሰርቫንቱ በእውቀትና በትጋት ላይ ተመስርቶ እንዲሰራ ማስቻል ዋነኛ ተግባሮች መሆናቸውን በአፅንኦት አስቀምጧል። ከአጋር ድርጅቶች ጋር ያለውን መደጋገፍ ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም በአቅጣ ጫው አስቀምጧል።
ሀገሪቱና ህዝቦቿ ያሏቸውን ሃብቶች በሙሉ በማስተባበርና በማቀናጀት መላ ህዝቡን ወደ ልማት ሥራ ማስገባትም ዋናው ሀገራዊ ዘመቻ መሆን እንዳለበት የጋራ መግባባት መያዙንም መግለጫው ጠቅሶ በዲፕሎማሲው ረገድም የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በአቅጣጫው ላይ ተጠቅሷል።
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የድርጅቱ አባላት፣ አመራርና መላ የሀገሪቱ ህዝቦች የተጀመረውን ለውጥ በማስቀጠል ሀገራችንን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚደረገው ርብርብ የየበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡና ለኮሚቴው አቅጣጫዎች ተፈፃሚነት ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላ ልፏል።
ወጣቶች በለውጡ ያገኙት ነፃነትና ዴሞክራሲ ዘላቂ ባለመሆኑ ገዥው ፓርቲና መንግሥት የወጣቱን መዋቅራዊ ችግሮች የሚፈቱ ጉዳዮች በተለይም በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ መረባረብ እንደሚገባቸው በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ወጣቶችም ሁሉም ችግር በመንግሥት ብቻ የሚፈታ አለመሆኑን ተገንዝበው በየደረጃው በሚቀ ርቡላቸው የሥራ ዕድሎች ላይ በመሳተፍ ለግልና ሀገራዊ ለውጥ መትጋት እንደሚ ኖርባቸው አሳስቧል። ወጣቶች ከኢኮኖሚ ባሻገር ያሉባቸውን የፖለቲካ ተሳትፎ ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻልም እስካሁን በመስኩ የነበሩ ጉድለቶች ሊታረሙ እንደ ሚገባ አመልክቷል።
በትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ፀረ ለውጥ ለሆኑ ቅስቀሳዎች ሰለባ እንዳይሆኑ ይልቁንም የተጀመረውን ለውጥ የማስቀጠል ሚናቸውን እንዲወጡ ለማድረግ የሚመለ ከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት ያለመወ ጣታቸውን ከገመገመ በኋላ ይህን ሁኔታ ለመቀየር የሚያስችሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አሳስቧል፡፡
መገናኛ ብዙሃን የህዝቡን አተያይ በመቅረፅ ረገድ ግን ብዙ እንደሚቀራቸውና በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያው እየተጫወተ ያለው አዎንታዊ ሚና እንደ ተጠበቀ ሆኖ አሉታዊ ሚናው እየጎላ መምጣቱን በመጥቀስ፤ ከለውጡ ጋር በተዛመደ መልኩ የሚታረምበትን አካሄድ መከተል እንደሚገባ አመላክቷል።
ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከለውጡ ተነስተው በሰላማዊ መንገድ መታገል እንደሚቻል አቋም መያዛቸውንና የጋራ ውይይት መጀመራቸውን ያደነቀው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፤ አንዳንድ ፓርቲዎች ፅንፈኝነትን በመስበክ የቆየውን የህዝቦች አንድነት በመሸርሸርና የህግ የበላይነትን ባለማክበር የሚንቀሳቀሱት ከዚህ ተግባራቸው በመቆ ጠብ በውይይት ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ መጎልበት ገንቢ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
አዲስ ዘመን ጥር 11/2011
መርድ ክፍሉ