መግቢያ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከጤና አንጻር በእኛም ሀገር ሆነ በሌሎች በርካታ ሀገራት ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ እርምጃዎች የሰዎችን፣ የምርትን እና የንግድን እንቅስቃሴ የሚገድብ በመሆኑ ወረርሽኙ ከጤናም ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጽእኖ እያደረሰ ይገኛል፡፡
ከዚህ አንጻር መንግሥት በኢኮኖሚው ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያስችሉ የፖሊሲ እርምጃዎችን ለመውሰድ በርካታ ዝግጅቶችን በማድረግ የፖሊሲ ፓኬጆችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
እነዚህም መንግሥት ወረርሽኙ በኢኮኖሚው ላይ እያደረሰ ያሉትን ተጽእኖዎች ለመቋቋም ተግባራዊ ያደረጋቸው የፖሊሲ እርምጃዎች እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የፖሊሲ ምላሾች ዝርዝር
ወረርሽኙ በዜጎች ላይ የሚያሳርፈውን ማህበራዊ መናጋት እና በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመቋቋም መንግሥት ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በየዘርፎቹ ቫይረሱ የሚያሳርፋቸውን ተጽዕኖዎች በመለየት አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን በጤና፣ በምግብና ኒውትሪሽን (ከተለመደው 15 ሚሊዮን ተረጂ ተጨማሪ ተረጂዎች እንደሚኖሩና ጠቅላላ ቁጥሩ 30 ሚሊዮን እንደሚደርስ ተገምቷል)፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በመጠለያና ምግብ ነክ ባልሆኑ ቁሳቁሶች ፍላጎት፣ በውሃና ንጽህና፣ በሎጂስቲክስ እንዲሁም በስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ዘርፎች የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራትና የፋይናንስ ፍላጎቶችን የያዘ እቅድ ተዘጋጅቷል።ይህንንም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ 1.64 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገምቷል፡፡
በሀገሪቱ አሁን ያለው አጠቃላይ የምግብ ክምችት እና ተጨማሪ የሚያስፈልገውም ተለይቷል፣ የምግብ ስርጭቱንም ለማሳለጥ በየአካባቢው በተለዩ ቦታዎች የምግብ ባንኮች እንዲቋቋሙ ተደርጓል፣ በሀብት ማፈላለጉ የሚሠራውም ሥራ ከዚህ ጋር እንዲቀናጅ ተደርጓል፣ እንዲሁም የጂኦ ስፓሺያል ኤጀንሲና የተለያዩ የአ.አ.ዩ. ምሁራንን በማሳተፍ የማፒንግ ሥራ በአዲስ አበባ ተጠናቋል፣ በክልሎችም ሥራው ተጀምሯል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ የኢኮኖሚ ተጽዕኖ ትንተናና የመቋቋሚያ ምላሽ ዕቅድ ተዘጋጅቷል።ይህም ወረርሽኙ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳርፈውን ተጽዕኖ በዝርዝር የሚተነትን ሲሆን፣ የዜጎችን ደህንነትና ዋስትና ከከፋ ጉዳት ለመከላከል እና ባለፉት ዓመታት ሀገራችን በድህነት ቅነሳ ያሳካቻቸውን ዋና ዋና ስኬቶች እንዳይሸረሸሩ፣ በተቀናጀ የመንግሥት የልማት ጥረት ከድህነት የተላቀቁ ዜጎች ተመልሰው ወደ ድህነት እንዳይገቡ፣ በቫይረሱ በጤና ምክንያት ዜጎች ሕይወታቸውን ከማጣት አልፈው በምግብ ዕጦት በርሀብ የሚሞቱ ዜጎች እንዳይኖሩ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ይዟል፡፡
በተጨማሪም በወረርሽኙ ምክንያት የሥራ ዕጦት እንዳይስፋፋ እና ቀጣሪዎች ሠራተኞቻቸውን እንዳያሰናብቱ መንግሥት ሊያደርጋቸው የሚገቡ የተለያዩ ድጋፎችን ይዟል።እንዲሁም የግሉ ዘርፍ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ጨምሮ በቫይረሱ የሚደርስባቸውን ተጽእኖ ለመቋቋም እንዲችሉና ቫይረሱ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በፍጥነት ወደሥራ መመለስ የሚችሉበትን አቅም ማጎልበት እንዲችሉ አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን በዕቅዱ በዝርዝር ቀርቧል።በመንግሥት ገቢ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ ግምትም ተዘጋጅቷል፡፡
በነዚህም ላይ በመመሥረት መንግሥት የፖሊሲ እርምጃ ፓኬጆችን በመወሰን ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ዋና ዋና የተከናወኑ ተግባራት፡-
ወረርሽኙን ለመከላከል ለሚያስፈልጉ ወጪዎች ቅድሚያ ለመስጠትና ፋይናንስ ለማድረግ ያስችል ዘንድ የ15 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸው ፕሮጀክቶች ወደ ቀጣዩ በጀት ዓመት እንዲተላለፉ የመለየት ሥራ ተሠርቷል፤
በአጠቃላይ ዕቅዱን ለማስፈፀም የሚያስፈልገውን ከፍተኛ የሆነ የውጭ ሀብት ለማሰባሰብ በተደረገው እንቅስቃሴ ከተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማትና የልማት አጋሮች ሀብት የማፈላለግ ተግባር እየተከናወን ይገኛል።እስካሁንም ከዓለም ገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ከአውሮፓ ሕብረት፣ ከፈረንሳይና ከእንግሊዝ መንግሥታት እስከ 2.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የወረርሽኙን ተጽእኖ ለመቋቋም የተዘጋጁትን ዕቅዶቹ ማስፈጸሚያ ድጋፍ እንዲውል ለማስቻል ሀብት ለማሰባሰብ የተለያየ የድርድር ደረጃዎችና ሂደቶች ላይ ይገኛሉ።ከዚህም ውስጥ ከዓለም ገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ የሚገኘው ከፍተኛ ድርሻን ይይዛሉ።ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሚጠበቀው 411 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍም በድርጅቱ ቦርድ ጸድቋል፡፡
ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የገቢ ዕቃዎች እና ግብአቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ በመደረግ ላይ ይገኛሉ፤
የፋይናንስ ዘርፉን ጤንነት አስጠብቆ ለመቀጠል እና ባንኮች በወረርሽኙ ተጽእኖ እንቅስቃሴያቸው ለተጎዱ ደንበኞቻቸው ጊዜያዊ የብድር እፎይታ እና ተጨማሪ ብድር ለመስጠት እንዲያስችላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊዮን ብር የሉኩዲቲ ኢንጀክሽን አድርጓል፤
የውጪ ምንዛሬ የሚያስፈልጋቸው እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ ዕቃዎችን እና ግብአቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስገቡ አስመጪዎች ባንኮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲያስተናግዱ በመደረግ
ላይ ነው፤
ኩባንያዎች የተሻለ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖራቸው ለማስቻል የተፋጠነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ እንዲኖር የሚያስችል አሠራር ተግባራዊ ተደርጓል፤
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጭ ገበያ በሚቀርብ አበባ ላይ የጣለው ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ገደብ ለጊዜው እንዲነሳ ተደርጓል፡፡
በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፣ ኮንስትራክሽን ዘርፍ እና ጅምላ ንግድ ኩባንያዎች እንዲሁም፣ የፋይናንስ ዘርፍ የሚፈለገውን የታክስ ዕዳ ጫና በመቀነስ እነዚህ ድርጅቶች በሥራቸው መቀጠል እንዲችሉ ለማገዝ ከታክስ ዕዳ በምህረት እስከ ክፍያ ጊዜ መስጠት፣ የሚደርስ ድጋፍ እንዲደረግ መንግሥት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የዜጎችን የወጪ ጫና ለመጋራት፣ ለመኖሪያና ለትምህርት (ከፍተኛ ትምህርትን ጨምሮ) እንዲሁም ለአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች አገልግሎት ከሚውሉ ቤቶች ኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ የሚከፈለው ግብር እንዲነሳ፣ እንዲሁም ያለሥራ ደመወዝ ከሚከፈላቸው ሠራተኞች የሚጠየቀውን የደመወዝ ገቢ ግብር ለአሰሪዎች ገቢ እንዲቀርላቸው የሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፣
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት ያለባቸውን የገንዘብ ችግር ለማቃለል በተፋጠነ መልኩ ለሥራቸው ማስፈፀሚያ የሚሆን ብድር እንዲያመቻች ተወስኗል፣
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ለህብረት ሥራ ማህበራት በብድር የሚሰጡት ተጨማሪ ገንዘብ በብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያመቻች አመራር ተሰጥቷል፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የተርንኦቨር ታክስ መክፈያ ጊዜን ማራዘም፣ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገው ዕርዳታ ከግብር ተቀናሽ እንዲሆን መፍቀድ፣ ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ለሚያቀርቡ አምራች ድርጅቶች፣ ምርታቸውን ለተወሰኑ ወራት በአገር ውስጥ
ገበያ መሸጥ እንዲችሉ መፍቀድ እና በቀላሉ ገቢ ማመንጨት በሚያስችሉ ሌሎች የምርት ሥራዎች፣ በተለይም ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የሕክምና አቅርቦቶችን በማምረት ላይ እንዲሰማሩ በሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ድጋፍ እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል፣
በኤክስፖርት ሥራ ላይ የተሠማሩ ድርጅቶች በቫውቸር ሥርዓት ተጠቅመው ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ወደአገር ባስገቡት ጥሬ ዕቃ ያመረቱትን ምርት ወደ ውጭ አገር መላካቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ለማቅረብ ባለመቻላቸው በእንጥልጥል ላይ የሚገኝ የጉምሩክ ዕዳ፣ የኢንቨስትመንት ቦርድ ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ ወደ አገር እንዲገባ በፈቀደው ተሽከርካሪ እና ጥሬ ዕቃ ላይ የሚፈለግ በኦዲት የተረጋገጠ የጉምሩክ ዕዳ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቀረጥና ታክስ ለመክፈል ግዴታ ገብተው ወደ አገር ባስገቡት ዕቃ ላይ የሚፈለግ የጉምሩክ ዕዳዎች እና በጉምሩክ ኮሚሽን በተሰብሳቢነት ተመዝግበው የሚገኙ ዕዳዎች በጉምሩክ ኮሚሽን በዝርዝር ተጣርተው ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲቀርቡና እና የገንዘብ ሚኒስቴር የዕዳውን መሠረዝ አግባብነት መርምሮ ውሣኔ እንዲሰጥ የሚኒስትሮች ም/ቤት ውክልና ለገንዘብ ሚኒስቴር ሰጥቷል፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሽያጭ ወደግል ባለቤትነት በሚዘዋወሩበት ጊዜ ገዥዎች ከሽያጩ ዋጋ ውስጥ የተወሰነውን ከፍለው ቀሪውን በ5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንዲከፍሉ የተደረገውን ስምምነት በተባለው ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ያላደረጉ እና በእንጥልጥል ላይ የሚገኘውን ዕዳ በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመነጋገር ቅጣትና ወለድ ተነስቶላቸው ዋናውን ዕዳ ሚኒስትሩ በሚወሰን ጊዜ ውስጥ እንዲከፍሉ እንዲደረግ ተወስኗል፣
በመጋቢት፣ በሚያዝያና ግንቦት የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የተርንኦቨር ታክስ ወለድና ቅጣት ሳይከፍሉ በሰኔ መክፈል እንደሚችሉ የመክፈያ ጊዜ ተራዝሟል፣
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገው ዕርዳታ እስከ 20 በመቶው ከግብር ተቀናሽ እንዲሆን ተፈቅዷል፣
ግብር ከፋዮች በ2012 የበጀት ዓመት ያጋጠማቸውን ኪሣራ ወደ ሚቀጥለው የግብር ዓመት ማሸጋገር እንዲችሉ ተፈቅዷል፣
በንግድ ሥራ የተሠማሩ የግል ድርጅቶች በመጋቢት፣ በሚያዝያ እና በግንቦት 2012 የሰበሰቡትን የጡረታ መዋጮ ወለድና ቅጣት ሳይኖርበት በሰኔ ወር 2012 ገቢ ማድረግ እንዲችሉ ተፈቅዷል፣
የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የሸቀጦች እጥረት እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በአጠቃላይ እስከ አሁን የተደረገው ዝግጅት እና እየተወሰደ ያለው እርምጃ ወረርሽኙ በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የተወሰደ ሲሆን፣ በዘርፍ ደረጃ ወረርሽኙ በተለየ ሁኔታ ችግር እያደረሰባቸው ያሉትን የመለየት እና የፖሊሲ ድጋፍ እርምጃ መውሰድ ተገቢ እንደሆነ ታምኖበታል።በመሆኑም በቀጣይ በተለየ መልኩ ጉዳት የደረሰባቸው እንደ ሆቴልና ቱሪዝም ያሉ ዘርፎች ላይ የደረሱ ተጽእኖዎችን በማጥናት መወሰድ ያለባቸው የፖሊሲ ድጋፎች ተለይተው ለመንግሥት ውሳኔ የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
አዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢኮኖሚው ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ ለመቋቋም በመንግሥት የተወሰዱ የፖሊሲ ምላሾች