በማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚናፈሱ የወሬ ማዕበሎች መካከል ከሠሞኑ ሁለት ጉዳዮች ቀልባችንን ስበውታል፡፡ የመጀመሪያው ችግርና መከራ ያሳደዳችሁ፣ ራሳችሁንና በእናንተ እጅ የሚኖሩ ቤተሰቦቻችሁን ይዛችሁ ለጥገኝነት የተዳረጋችሁ ሕዝብ አገልጋይ ሠራተኞች ሆይ ኑ ተሰብሰቡልኝ፡፡ የእናንተንም ሆነ የቀያችሁን ሰላም አስጠብቃለሁ የሚለው የካማሺ ዞን ጥሪ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ክቡር የሆነውን የሰው ህይወትና በእጁ የሚገኝ ሀብትን ሲያወድም የከረመው የሥሌት ብጥብጥ የዜጎች ጥሪት ባለአደራ የሆኑት የአገሪቱ ባንኮች የተደራጀው ማፍያ አይን ማረፊያ እና የወረራ ማዕከል መሆናቸው ነው፡፡ ትኩረታችንን በሰናዩ ተግባር ላይ አደረግን፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙት ዞኖች አንዱ የሆነው የካማሺ ዞን በሥሩ በሚገኙ አምስት የሚጠጉ ወረዳዎች የአገልግሎት መስጫ የመንግሥት ተቋማት ጭር ካሉ ቆይተዋል፡፡ ድክድክ ከሚሉ ሕጻናት እስከ አፍላ ወጣት ተማሪዎች የሚቦርቁባቸው እነዚያ የቀለም ቤቶች ወና ከሆኑ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡ ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም በራቸውን ከርችመዋል፡፡ በእነዚህ መስሪያ ቤቶች ሕዝብን አገልግሎት በመስጠት እንጀራቸውን የሚያገኙ፣ ጎጆ የቀለሱ እና ልጆች ያፈሩ ባለሥራዎችም ሥራ ከፈቱም ወራቶች አልፈዋል፡፡
አቶ ደሳለኝ ኩምሳ እንደገለጸልን፣ በያሶ ወረዳ አስተዳደር ዘርፍ ፀረ ሙስና መከታተል ክፍል ባለሙያ ነበር፡፡ በወረዳው ለስድስት ዓመታት ጥቂት ወራት የቀሩት አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ተፈናቅለው ከሸሹት መካከል ነው፡፡ በዋናነት ብጥብጡ እየከፋ የመጣው ባልታወቁ ታጣቂ አካላት አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚያ በፊት በነበሩት ሁለት ወራት ችግር ሊፈጠር እንደሚችል አመላካች ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ በተለይም ከፖለቲካዊ የለውጥ ጅምሩ ጋር ተያይዞ በሚወርዱ የመወያያ ሰነዶችና አቅጣጫዎች ላይ ተነጋግሮ አለመግባባት ይስተዋል ነበር፡፡ በመደመር ፍልስፍና፣ በቁቤ ትምህርት አሰጣጥ ሂደት እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ በሚነሱ ሃሳቦች አረዳድ ላይ አለመግባባቶች ተስተውለዋል፡፡
የግጭቱ እየከረረ መምጣት ያሳደረው ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ቀላል አለመሆኑን የተናገረው አቶ ደሳለኝ ኩምሳ፤ አስቀድሞ መፍታት እንዲቻል ዕድል የሰጠ እንደነበር ገልጿል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው ደህንነት እስከ ቤተሰቡ ለችግር እየተጋለጠ መጣ፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመስከረም አስራ ስድስት ጀምሮ ከአካባቢው መሸሽ ጀመረ፡፡
የደመወዝ ክፍያ ካየሁኝ አራት ወራት ሆኖኛል ያለው አቶ ደሳለኝ፤ ሠራተኛው ወደ ሥራ ገበታው እንዲመለስ አመራሩ ከጀመረው ውይይት ጋር ተያይዞ ምን ሃሣብ እንዳለው ጠይቀነው ነበር፡፡ በአጭር ጊዜ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር አንድነት የሚፈጥርና የሚያግባባ ሥራ መስራት የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ እስከ አሁን ባለኝ መረጃ ወደ አካባቢው የተመለሱ ነጋዴዎች መኖራቸውን ሰምቻለሁ ብሏል፡፡
የያሶ ወረዳ መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህሩ አቡዬ ባዘዘው እንደተናገረው፣ ትምህርት ቤቶች ከጥቅምት ጀምሮ ተዘግተዋል፡፡ ከአካባቢው ሸሽቶ የወጣው ህዳር አምስት ሲሆን በከባድ ሥቃይ ውስጥ ሕይወቱን ማትረፉን ተናግሯል፡፡ የትራንስፖርት ግንኙነቱ ተቋርጧል፡፡ ከፍተኛ ተኩስ በመኖሩ አማራጭ አልነበረንም፡፡ ድፍን ሁለት ቀን በእግር ተጉዘናል፡፡ ሰላሳ ሦስት ሰዎች ነበርን ለመንገድ መሪ ሃያ ሺ ብር ከፍለናል፡፡ ከዚያም አባይን በታንኳ ለሚያሻግሩ ሰዎች በአንድ ሰው አምስት መቶ ብር ከፍለናል ሲል የገጠመውን ዘርፈ ብዙ ፈተና አንስቷል፡፡
ጥቃቱ ያነጣጠረው የክልሉ ተወላጅ አይደላችሁም በሚሏቸው ኦሮሞዎች ላይ ሲሆን፣ ቀጥሎም አማራና ሌሎች ብሔሮችም ጭምር ለጥቃት መዳረጋቸውን አንስቷል፡፡ ደመወዝ ከቆጠረ ሁለት ወራት እንዳለፉት የገለጸው መምህር አቡዬ ባዘዘው፤ አሁንም የአካባቢው የሰላም ሁኔታ ወደ ቀድሞው መረጋጋት መመለሱን ይጠራጠራል፡፡ አሁንም ከአካባቢው በተለይ እያሶ ወረዳ ገጠር የሚገኙ አርሶ አደር ተፈናቃይ ሰዎች መኖራቸው እና መንገድ እንዳልተከፈተ መረጃ አለኝ ብሏል፡፡
የከማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገርቢ ሎልንሳ በበኩላቸው፣ ከመስከረም አስራ ስድስት ጀምሮ መደበኛ የመንግሥት የሥራ እንቅስቃሴ መቋረጡን አስታውሰዋል፡፡ የፀጥታ ችግር ተከስቶባቸው በነበሩ ከአምስት በላይ ወረዳዎች አሁን አንጻራዊ ሰላም ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ከሥራ ገበታቸው ለተፈናቀሉ የመንግሥት ሠራተኞች ከዞኑ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጋር በመነጋገር ጥሪ ተላልፏል፡፡ በዚህ መሰረትም 200 ሠራተኞች ተገኝተው ጥር ሁለት ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመው ጥሪውን ሰምተው ከተገኙ የመንግሥት ሠራተኞች የተነሱት አንኳር ነጥቦችም የመንገዱ ሁኔታ በተገቢው ይከፈት፣ በዘላቂነት ከሥጋት ነጻ የሆነ የሥራ አካባቢ ይፈጠርልን፣ የተዘረፉና የወደሙ ንብረቶቻችን ጉዳይ እንዴት ይሁን? እና የተቋረጠው ደመወዝ ይከፈለን የሚሉት ጥቂቶቹ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ከመቼ ጀምሮ ደመወዛቸው እንደተቋረጠ በውል ይታወቃል ወይ? በሚል ላነሳንላቸው ሃሳብ፤ የተወሰኑ ሠራተኞች የባንክ አካውንት ለመጠቀም ምቹ ያልሆኑ ወረዳዎች በመኖራቸው ደመወዝ የተቋረጠባቸው አሉ፡፡ ለአብነት ሰዳል፣ አጋሎ ሜጢ፣ ያሶ ወረዳዎች እንዲሁም በለው ወረዳ በከፊል ለሁለት ወር ያህል ደመወዝ ያልተከፈላቸው ይኖራሉ፡፡ ሌሎቹ አልተቋረጠባቸውም ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡
አጠቃላይ በዞኑ አምስት ወረዳዎች 1 ሺ 300 የመንግሥት ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ የሉም፡፡ ዋናው ምክንያት የፀጥታ ችግሩ ቢሆንም ዓመት በዓልን ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ የሄደ የመንግሥት ሠራተኛ ቁጥሩ ቀላል አይደለም ብለዋል፡፡
አሁን አስተማማኝ ሰላም እንዲፈጠር በፌዴራል ደረጃ ከተዋቀረው ኮማንድ ፖስት ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ያሉት አቶ ገርቢ፤ ችግር የነበረበትና ተቋርጦ የቆየው የአዲስ አበባው መንገድ መሆኑን ገልጸው፣ አሁን ሥራ መጀመሩን አመልክተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከዞኑ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው በአጎራባች ወረዳዎች ተጠልለው የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችም ሆኑ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸው ተመልሰው መደበኛ ሥራቸውን እንዲጀምሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
የተገኙትን የመንግሥት ሠራተኞች በጥር ሁለት ባወያዩበት መድረክ፤ከመንገድ መከፈትና ካለው አስተማማኝ የፀጥታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ በኢንዶክትሬሽንና ህዝብ ግንኙነቱ በኩል ደጀንነቱን መግለጹ ይታወሳል፡፡
አዲስ ዘመን ጥር 9/2011
በሙሀመድ ሁሴን
camera xuyên thấu vô cùng hấp dẫn và lôi cuốn, cùng khám phá ngay.
Double Wall Corrugated (DWC) Pipes in Iraq: Elite Pipe Factory in Iraq is a leading producer of Double Wall Corrugated (DWC) Pipes, known for their superior strength and lightweight design. These pipes feature an innovative double-wall structure that provides enhanced resistance to impact and external pressure, making them ideal for a variety of applications, including sewage systems and drainage projects. The advanced production techniques at Elite Pipe Factory ensure that our DWC pipes meet rigorous quality standards, delivering exceptional performance and longevity. As one of the best and most reliable factories in Iraq, we are dedicated to providing high-quality products that our clients can depend on. For more details about our Double Wall Corrugated Pipes, visit elitepipeiraq.com.