ኧሯ! እንዴት ሆኖ እንዴት ሆኖ እኛንማ አይደፍርም! ብለን ነበር ደፈረን። በሩቅ ሆኖ የሰማነው ዜና ገስግሶ መጥቶ አጠገባችን ከደረሰ የወራት እድሜን አስቆጠረ።
በሰው ሀገር ሲነገር፤ ሲወራ እኛ ዘንድ የማይደርስ መስሎን ተዘናግተንማል። እኛ ሀገር አይገባም ፤ ጥቁሮችን አይነካም በማለት እራሳችንን በማይሆን ተስፋ እያታለልን ቆይተናል። ቁርጡ ቀን ደርሶ በሀገራችን የቫይረሱን መገኘት እውነታ ሲነገር ሰምተን ላለማመን ያመነታነው ስንቶቻችን እንሆን? ታዲያ አስፈሪ ዝናውን አስቀድሞ በርካቶቻችንን ኮርኩሮ ሃሳብ በማሰንዘር ፤ ከሃሳባችን መደምደሚያ ሳንደርስ ከች ብሎ ጉድ ያደረገን እሱም አይደል ወይ ኮሮና። ስለ ቫይረሱ ያለን እውቀት እንደ ግንዛቤ የሚለያይ ነው።
አንዳንዱ ህይወቱ ግድ ሰጥቶ ለራሱ ኖሮ ሌላውን ለማትረፍ የሚጥረው ነው። ሌላው ደግሞ ለራሱም ሆነ ለሌላው ግድ የሌለው ቢነገረው ቢዘከር ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶ እንዳላየ የሚሆን ነው። ራሱን በመኖርና ባለመኖር መካከል ከቶ በደመነፍስ እንደሚኖር ሰው ቫይረሱ ምንም እንደሚያመጣ የሚናገርም ዛሬ ድረስ አልጠፋም። ሰውን ለማዳን ራሱን ያልሰሰተውን ተመልክተን እሰየው በርታልን ጓድ እንዳላልን ሁላ ፤ በግዴለሽነት የሚኖረውን ደግሞ በትዝብት እያየን ከማለፍ ለመምከር የሞከርን እንኖራለን።
የሚጠነቀቀውም ሆነ ግዴለሹ፤ የአንዱ ጤንነት የሌላው መኖር ዋስትና ነው ። የሰው ልጅ በምድር ላይ የሚኖረው ለራሱ ብቻ አይደለም፤ ለሌሎችም ነው። አንዱ ከሌለ የሌላው መኖር ትርጉም አልባ ነውና ። ህይወት ጣዕም የሚኖራት በመኖር ነው። መኖር ትርጉሟ ሙሉ የሚሆነው አንዳችን ለአንዳችን በሚኖረን አብሮነት ፤ መረዳዳትና መደጋገፍ ነው። ለዚህ ዋንኛው ደግም የኔ ጤንነት ሲጠበቅ የጎረቤት፤ የአካባቢዬ ፤ የሀገር፤ የሁሉም ጤና መሆን ግድ ይላል ።
ታዲያ አለመታዘዛችን ከምን የመነጨ ይሆን? ለመኖር ራሳችን ከመጠበቅ ሌላው አማራጭ ይኖር ይሆን። ታላላቆቻችን፤ አባቶቻችን ማድመጥ፤ መደማመጣችንን እሴቶቻችንን ማን ነጠቀን? ለምን ረሳነው? በራሳችን ፈርደን በሌሎችም የመጨከን አባዜን ከየት አመጣነው? የሰውን ልጅ ሳይመርጥ ከምድረ ገጽ እያጠፋ ያለው ይህ ጨካኝ ቫይረስን እንዴት ልባችንን ሊያደነድን ቻለ። ሰው የሚችለውን ነውና የሚታዘዘው እራሳችንን እንመርምር ለመለወጥ መትጋት አለብን።
የማንችለውን ትተን የምንችለውን መምረጥ ፤ ዛሬን መኖር ለነገ ተስፋ ነው። የእኛ ጥንቃቄ ለወገን መሆኑ ማመን አለብን። ነጭ፤ ጥቁር፤ ዘመድ፤ ባዕድ እያልን ራሳችንን ሳንከፋፈል ከስጋት ራስን ጠብቆ በማስመለጥ አብሮ ማምለጥ ይቻላልና ነው። ካለበለዚያ ግን “ከኑግ ጋር ያለህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” ከሆነ ጉዳይ የታሪክ ተወቃሽ መሆናችን አይቀርም። መቼም ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ማግስት ጀምሮ ብዙ ለውጦችን፣ አዳዲስ ነገሮችን ታዝበናል።
ለመከላከል የሚረዱን እጅን በሳሙና ቶሎ ቶሎ በደንብ መታጠብን ፤ ፊት በእጅ አለመንካት፤ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በዋናነት ከህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክሮች ተግባራዊ ለማድረግ ተሞክሯል። ለራሱ ያለ ራሱ ተጠንቅቆ ሌላውን ለማዳን እየጣረ እየተጋ ታይቷል። ይገርማችኋል! ለዛሬ ትዝብቴ መነሻ የሆኑት ይህንን የሰሙ የማይመስሉ የሰፈሬ ወጣቶች ናቸው። በከተማችን የሚገኙ በርካታ ወጣቶች በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ከወገናቸው ጎን የቆሙበትን አይተናል፤ ሰምተናልም። የነገ የሀገሪቱ ተስፋዎች መሆናቸውንም አስመስክረዋል። የኔ ሰፈር ወጣቶች ግን ቫይረስ መኖሩን አልሰሙም!! በአንድ ላይ በጋራ በመሆን መጠጥ ይጠጣሉ ፤ ጫት ይቅማሉ፤ መንገድ ዳር ተዛዝለው በሚባል ሁኔታ ሆነው ያወጋሉ።
የቫይረሱ የተከሰተ ሰሞን አልነበሩም፤ ጠፍተው ነበር ። እሰየው አልኩኝ፤ ራሳቸውን ለመከላከል ወስነው ቤት ለመቀመጥ የከተሙ መስሎኝ። አልሰሜን ግባ በለው አሉ። ለካ የቦታ ለውጥ በማድረግ ከሰው አይን ዞር ብለው ነበር። ታዲያ እኔም የግዴታዬን ለመወጣት ወደእነሱ አመራሁ። በእግዜር ስላምታ ተቀላቀልኳቸው። ስለቫይረሱ አስከፊነት የነሱ መጠንቀቅ ለሚወዷቸው ሁሉ ፤ ለወላጆቻቸው፤ ለሰፈራችን ሁሉም እንደሆነ አስረዳኋቸው። ለማዳመጥ ፈቃደኛ ባልሆነ ጆሮ ሰሙኝ ።
መልስ አልሰጡኝም። አንደኛው እሺ አለኝ ቀልድ በተሞላበት ፌዝ ። በእውነት አመመኝ። ለምን አትተሳሰቡም እርስ በርሳችሁ እንኳን አትዋደዱም አልኳቸው። እሺ ሌላው ቢቀርስ ለምን አትታዘዙም አልኩት? አቀርቀረው ስልካቸውን መጎርጎር ተያያዙት ። ትቻቸው ስሄድ መታዘዝ ከመሰዋዕትነት ይበልጣል አልኩ ሰምተውኛል፤ ግን ዝምታን መርጠዋል። ለብቻዬ እንዳስብበት የቤት ስራ የሰጡኝ ወጣቶች ዞር ብዬ በማየት ጉዞዬን በሃሳብ ቀጠልኩ። “ለምን ይሆን የተከለከለ ነገር የሚያምረን?” አልኩኝ ለራሴ ። ወደ አፈጣጣራችን ተመለስኩ ለካ አዳምን ከገነት ያስባረረው አታድርግ የተባለው በማድረጉ ነው።
እኛም ዛሬ ለመቅጽበት ለሚያልፍ ቀን ብለን አታደርጉ የተባልነውን በማድረግ በጎ ተግባር እንደፈጸመ ጀግና በየአደባባዩ እንታያለን። ማንንም መስማት አንፈልገም፤ እራሳችንን ብቻ ካልሆነ በስተቀር ፤ ራሳችንን በቅጡ አውቀን ብናዳምጥ ጥሩ ነው። በዓለም ያሉ ሀገራት እንደኛ አይነት ተው ተብለው የማይሰሙ ዜጎች በመያዛቸው ነው። ዛሬ ለመስማት የሚቀፍ ዜና እየሰማን የምንገኘው። እነሱ ቢጸጸቱም ወደ ኋላ ሊመልሱት የማይችሉት ነገር ሆኖባቸዋል። ለኛ ትምህርት መሆን አለባቸው።
እኛ ላይ በቅድሚያ ያልተፈጸመብን መሆኑን እያመሰገን ከሰማነው፣ ካየነው ቀድሞ መገኘት የግድ ይለናል። ጊዜው ፈጣን ነው ፤ ዛሬ ላይ እንኳን ቆመን ነገን ለማየት በተሰጠን መልካም እድል መጠቀም አለብን። ያለመታዘዛችን ዋጋ እንዳያስከፍል መበርታት ያስፈልገናል። ለዚህም ቀኑ ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም። የቤት ስራን ከወዲሁ በመፈጸም ለወገን አለኝታነታችን በመግለጽ እራስን ሆኖ መገኘት፤ ታዝዞ መታዘብ ማስተማር ፤ቀዳሚ ሆኖ ለሌሎች አርአያ በመሆን መስመሩን በመጥረግ ከመስመሩ ያፈነገጡትን መመለስ ይገባል።
የዛሬ ሁላችንም አብሮነትና ትብብርን አንዱ ለአንዱ መኖር ግድ ይሆናል። ታላላቆቻችንን በማስቀደም እነሱን አድምጠን ከዚህ አስከፊ አደጋ ማምለጥ ይኖርብናል። አብረን ስንሆን፣ ስንተባበር፣ ስንደማምጥ፤ ስንረዳዳ ያምርብናል። ባህሩን አቋርጠን መሻገር እንችላለን። የሰው ልጆችን እየጠረገ ያለውን አስከፊ ወረርሽን ለመከላከል ወኔ አቅም ጉልበት ይኖረናልና ። መጪው ጊዜ መልካም ዜና የምንሰማበት ጊዜ ይሁንልን ።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2012
ወርቅነሽ ደምሰው
ለራስ ሲባል ሌላውን …