10 መማር ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች አንዱ ማመዛዘን መቻል ነው። እውነታውም ቢሆን የተማረ ሰው በቀላሉ የመኖርና ህይወቱን የመምራት ብልሃት ይኖረዋል። ለሕጎች ተገዥ መሆንን ጭምር ያካትታል። ለመንግሥት አስተዳደር በጥቅሉ ለሕጎች ተገዥ ከመሆን በላይ ለመንግሥት ጠቃሚ ሀሳብ በማቅረብ ሀገርን ይረዳል። ነገር ግን በእኛ ሀገር ይህን እየተመለከትን አይደለም።
ኮቪድ -19 የዓለም ሥጋት ከሆነ ሰንበትበት ቢልም የኛ ሀገር ሰው ግን ድንግጥም ያለ አይመስልም። የመንግሥትን መመሪያና የህክምና ባለሙያዎችን መልዕክት ባለመስማት ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ የሚውለው በአብዛኛው የተማረው የሕብረተሰብ ክፍል ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። የተማረው ላልተማረው አርአያ ከመሆን ይልቅ ቸልተኝነትን የሚያስተምሩ ይበዛሉ።
ሁሉም ሰው ሳይዘናጋ ከኮቪድ -19 ለመከላከል ከሦስት አካላቶች መጠንቀቅ አለበትት። መጀመሪያ እራሳቸውን ከሚያታልላቸው ከራሳቸው ህሊና መጠንቀቅ ከቀሪ ሁለት አዘናጊ አካላት በመጠንቀቅ ሕይወታቸውን መታደግ ይችላሉ። አማኝ ነኝ የሚለው ሰው የእምነት አባቶችን መልዕክት አልሰማም ብሎ በግድ በሽታው ካልያዘኝ ማለት እብደት ነው። ከዚህ በፊት በርካታ ጊዜ ወረርሽኝ ተነስቶ በሚሊየንና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ ሞቱ መረጃዎች ያስረዳሉ። እና ያኔ ፈጣሪ የለም? አማኝስ? መልሱ አያከራክርም።
ነገር ግን ከጥንቃቄ ማነስ የተነሳ ክቡር ህይወታቸውን አጥተዋል ማለት ነው። ህሊናችን በሃይማኖት እያሳበበ ተዘናግተን እንድንሞት እንዳያደርገን እንጠንቀቅ። እንደውም እኮ ጠንካራ እምነት ያለው ሰው በቀላሉ የመሪውንና የባለሙያዎችን ትዕዛዝ መቀበል ነበረበት። ሁሉም የዕምነት ተቋሞች ለመሪዎቻችንና ለታላላቆቻችን መታዘዝ እንዳለብን ያስተምራሉ። ታዲያ አሁን አድርጉ የተባልነውን ዘንግተን ከኮሮና ጋር መፋጠጣችን ትዕዛዝ አለማክበር አይሆንም? በፈጣሪ ከሚያምን ሰው ይህ ይጠበቃል? ነፍሳችንስ ተጠያቂ አናደርጋትም? ህሊናችንን በውሸት እየሸነገልን ነው።
አሁን በሀገራችን እየተስተዋለ ያለው በተማረውና ባልተማረው ሰው የአስተሳሰብ ልዩነት መጥፋቱ ነው። እንዴት ሰው በአንድ ህይወቱ ይቀልዳል? ‹‹ሐበሻ ሞት አይፈራም›› ሲባል ትኩረት ሰጥቼው አላውቅም ነበር ነገር ግን ሰሞኑን የምናየው ነገር የዚህን አባባል እውነታነት የሚያረጋግጥ ነው። ግን እንደሚገባኝ ሐበሻ ሞት አይፈራም ሲባል በሀገሩ ጉዳይ፣ በሚስቱና በእናቱ ጉዳይ ነው። ለጠቀስናቸው ሲሉ መሞት የጀግና ሞት ነው። ነገር ግን በጥንቃቄ ጉድለት በወረርሽኝ መሞት ጀግናውን የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር የማይመጥን ሞት በመሆን ልንጠነቀቅ ግድ ይላል። ‹‹ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም›› እያልን የራሳችን ህሊና ለኮሮና አሳልፎ እንዳንሰጥ እፈራለሁ። ይህ የሀገራችን ቢሂል ለኮሮና ወረርኝ አይሰራም።
እርግጥ ነው አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ይረዳ ይሆናል። ከዚህ ይልቅ በአሁኑ ወቅት የሚጠቅመን ‹‹ፈሪ ለእናቱ ጀግና ነው›› የሚለውን የፈሪ ማበረታቻ ሥነ ቃላችን ነው። አንዳንድ ሰዎች ቤት ውስጥ መዋል ለወንድ ልጅ አይመጥንም ቢሉም ክፉ ቀንን ተደብቆ ነፍስን ማትረፍ ጀግንነት የሚሆንበት ቀን እሩቅ አይሆንም። እምነት ካለን ሊያታልለን የሚሞክረውን የገዛ ህሊናችንን ባለመስማት ህይወታችንን እናትርፍ። ፈጣሪም እኮ በመጨረሻው ዘመን ፈተናዎች ይበዛሉ ብሏል። ይህ ማለት እኮ ችግሮች ሲከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ማለት ነው። አንዳንድ ሰዎች መጠንቀቅን ፈጣሪ የለም እንደማለት አድርጎ በመቁጠር እየተዘናጉ ነው። ሁሉም ሰው በሁለተኛ ደረጃ እራሱን ከአንዳንድ ፖለቲከኞች መጠበቅ አለበት። የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ብለው የመንግሥትን መመሪያን ካለማክበርም በላይ ኮሮና መንግሥት በሚለው ልክ አስጊ አይደለም እያሉ ህዝብ እንዳይጠነቀቅ የሚያደርጉ ብዙዎች ናቸው። እንደ መንግሥት መግለጫ ቢሆንማ ኑሮ እስካሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ያልቅ ነበር ሲሉ ይደመጣሉ። መንግሥት ምርጫ እንዳይካሄድ እየተጠቀመበት ነው በማለት ይመርጠናል የሚሉትን ህዝብ እየተሳለቁበት ነው። ህይወቱን እንዲነጠቅ ጉልበትና ድፍረት እያደሉት ይገኛሉ።
መንግሥት ደጋፊዎቼን አሰረብኝ፤ እንዳይሰበሰቡ እያደረገብኝ ነው ብሎ ኮሮናን መወንጀል ቀላል ስላልሆነ መጠንቀቁ ይበጃል ባይ ነኝ። ፖለቲከኞች ስልጣን ለመያዝ ህዝብ እንደሚያስፈልግ የተገነዘቡት አይመስልም። ሀገርን መምራት ማለት ምድሩን አይደለም የሰውን ልጅ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ በበሽታ እንዳያልቅ ቀድሞ ማሰብ የብልሆች መንገድ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ። ተሳስቼ ከሆነ ግን ሞግቱኝ ካጠፋሁ እማራለሁ። አሁን ጊዜው ተማሩ እንማር የሚባልበት እንጂ ዘራፍ የሚዘፈንበት አይደለም።
ሕይወቱን የሚወድ ሰው በሦስተኛ ደረጃ የሀሰተኛ ነቢያቶችን የማዘናጊያ መልዕክት መስማት ዋጋ እንደሚያስከፍለው ማወቅ አለበት። ሀሳቡን ከመፅሔት ላይ ያገኘሁት ሲሆን እንዲህ ይላል፤ ‹‹ከነገ ጀምሮ ኮሮና የሚባል በሽታ ከምድር ላይ እንዲጠፋ አዘዝኩ›› እያለ የሚጮህ ሀሰተኛ ነቢያት ሞልተዋል። ዙሪያውን የከበበው ህዝብ እሱን ተከትሎ ‹‹አሜን›› እያለ ይጮሀል። ከገረመኝ ነገር ግን በዚህ ጭንቅ ወቅት እንኳን ‹‹ነብዮች›› በቴሌቪዥን ቻናል የዘነጠ ፎቷቸውን አስቀድመው ‹‹ኮሮና ከኢትዮጵያ መቼ እንደሚጠፋ ፈጣሪ የነገራቸውን ነቢይ ነገ ለህዝብ ስለሚያስተላልፉ ይጠብቁ›› የሚል ማስታወቂያ ማስነገራቸውን አለማቆማቸው ነው።
በቤቱ ተቀምጦ እልልታውን እያስተጋባ ከጥንቃቄ የሚርቅ በርካታ ምዕመናን እንደሚኖሩ አልጠራጠርም። እንዲህ ብሎ ህዝብ እንዳይጠነቀቅ ማድረግ በፈጣሪ ያስጠይቃል። ህዝቡም ራሱን ከነዚህ አዘናጊዎች መጠበቅ አለበት። እኔን የሚገርመኝ መጪውን መከራ መተንበይ ቀርቶ መገመት ያልቻለ ‹‹ነቢይ›› በመከራው ሰዓት እጁን ለፈውስ በድፍረት ዘርግቶ መቆሙ ነው።
በዚህ የከፋ ዘመን እንዲህ እያወጁ ይሄ የዋህ ህዝብ ራሱን እንዳይጠብቅ ማዘናጋት ምን ይሉታል? ፈጣሪስ ይወደዋል? ህዝቡ በወረርሽኝ ላለመያዝ የሚያደርጉትን እንቅስቃቄ ከፈጣሪው ጋር እየተጣላ እንዲመስለው የሚያደርጉ ሀሰተኛ ነቢያቶች ለመዋሸትም ህዝብ እንደሚያስፈልግ አስበው ከማደናገርና ከማዘናጋት ሊቆጠቡ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በመከራ ወቅት ብትላላ ኃይልህ ትንሽ ስለሆነ ነው።›› የሚል ቃል አለ። ህሊና ላለው ሰው ይህ ቃል በቀላሉ በመከራ ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቁማል። ሳይጠነቀቁ ቀርቶ መሞት ምን የሚሉት ሞት ነው? ይሄ ለኔ የእምነት ሳይሆን በተለይ ደግሞ ክብርን ለሚወደው የሀገሬ ህዝብ የውርደት ሞት ነው።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2012
ሞገስ ፀጋዬ
አታዘናጉን !