ኢትዮጵያ ሀገራችን በተለያየ ዘመን በርካታ ክፉ ክፉ ነገሮች ገጥመዋታል። በቀኝ አገዛዝ ለመግዛት የሞከሩትን ወራሪዎች አሳፍራና አሸማቃ መልሳለች። አስከፊ ጦርነት ገጥሟትም በልጆቿ መሰዋዕትነት በድል አድራጊት አሸናፊነቷን አሳይታለች። የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮችም ገጥመዋታል። እንዲሁም በተለያየ ጊዜ አስከፊ ወረርሽኞችን አስተናገዳለች። ሁሉንም በዘዴና በጥበብ ተወጥታቸዋለች። በአንድነት ስሜት በመነሳሳት፣ በመረዳዳትና በመተጋገዝም ሁሉንም አስከፊ ዘመናትን አሳልፋ ዛሬ ለደረስንበት ደርሳለች።
ዛሬ ደግሞ የዓለም የስልጣኔ ማማ ያልበገረው፣ ሳይንቲስቶችና አዋቂዎችን የፈተነ፣ የህክምና ባለሙያና ጠቢባንን ያስጨነቀ፣ የሀብትና ንብረት ብዛት ያልበረገው፣ ለባለስልጣን ያልተንበረከከ መላውን አለም ያርበደበደ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አጋጥሟታል። የኮሮና ቫይረስ በመላው ዓለም መሰራጨቱ ከተሰማ ወራቶች ቢቆጠሩም በሀገራችን ግን አንድ ወር አልደፈነም። አስካሁን ባለው መረጃ 35 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል። በሀገራችን ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ ሞት ባይከሰትም የህሙማኑ ቁጥር በየጊዜው መጨመር ግን አሁንም አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል። ይሄንን ወረርሽኝ ለመከላከልም በመንግስት በኩል እየተወሰዱ ያሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች አሉ። ይሄ የሚያስመሰግን ነው። ከዚሁ ጎን ለጎንም በጎ አድራጊ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከመንግስት ጎን በመቆም ገንዘብ በማዋጣት፣ መኪናቸውን ለአገልግሎት እንዲውል በመስጠት፣ ህንፃዎቻቸውን፣ ሆቴላቸውን እና መኖሪያ ቤታቸውን ሳይቀር ለህክምና አገልግሎት እንዲሁም ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል በማድረግ፤ ከንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ጀምሮ እስከ ምግብ ድረስ በዓይነት በመደገፍ አንቱ የተባለ ስራ የሚሰሩ የክፉ ቀን ደጋጎች ታይተዋል። እነዚህ ሰዎች የጥንቃቄ አልባሳት፣ የህክምና ቁሳቁስ ባልተሟላበት ሁኔታ ህይወታቸውን ሰውተው አገልግሎት ከሚሰጡ የህክምና ባለሙያዎች ያልተናነሰ መልካም ስራ እየሰሩ ናቸውና ሊመሰገኑና ሊከበሩ ይገባል።
ሀገራችን ሁልጊዜም ቢሆን ሰርተው የሚያሰሩና በችግር ጊዜ አጋርነታቸውን የሚያስመሰክሩ ታሪካዊ ጀግኖችን አጥታ አታውቅም። በየስርዓቱ በችግር ወቅቱ ህዝቧንና ሀገራቸውን የሚጠብቁና የሚያስጠብቁ ጀግኖች ይነሱላታል። አሁን እያየን ያለውም ይሄንኑ ነው። የክፉ ቀን ክፉዎችን በተመለከትንበት ዓይን የክፉ ቀን ደጋጎች ከያሉበት ብቅ ብቅ ብለው ለወገን ያላቸውን ወገናዊነት እያሳዩ ናቸው። በዚህም ከመንግስት ለተደረገላቸው ጥሪ በቀናት ውስጥ ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል፤ ይሄ ስራቸው ይበል የሚያሰኝ እና ደግመን ደጋግመን እንድናመሰግናቸው ያስገድደናል።
የክፉ ቀን ደጋጎች በጎነትን በማስተማር በበጎ ተግባራቸው አርአያ በመሆን እንደሚያስደስቱን ሁሉ የክፉ ቀን ክፉዎች ደግሞ በመጥፎ ስራቸው ይወገዛሉ፤ ይወቀሳሉ። እነዚሀ አካላት በኮሮና ቫይረስ ጭንቅ ውስጥ ያለን ህዝብ ከማረጋጋት ይልቅ በአቋራጭ ለመክበር በወገን ላይ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ላይ ታች ሲል ይስተዋላሉ።
ሰሞኑን ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው በአቋራጭ ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት ሕገወጥ በሆነ አካሄድ ምርት የደበቁ፣ ዋጋ እያናሩ ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሱ ያሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ርምጃ ተወስዷል። አሁን ባለው ሂደትም 15 ሺህ 58 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድና 424 የንግድ ድርጅት ባለቤቶችም በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ይሄ በመረጃና በማስረጃ የተደረሰበት ሲሆን በድብቅ ከዚህም በላይ አሻጥር የሚሰሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም። ይሄ በጣም የሚያሳፍርና የሚያሳዝን ተግባር ነው። ይልቅስ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው ታርመው ከደጋግ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በጎነትን ተምረው መልካም ስራ በመስራት የክፉ ቀን ደጋጎች በመሆን ታሪካዊ አሻራቸውን ሊያሳርፉና በሰማይም በምድርም ወረታ ያለውን ሥራ ሊሰሩ ይገባል።
አዲስ ዘመን መጋቢት27/2012
ታላቅ ምስጋና ! ለክፉ ቀን ደጋጎች!