የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ፣ በዓለም፣ በአህጉራችን አፍሪካ፣ እንዲሁም በአገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ ስጋት የደቀነ ወረርሽኝ ነው። በአሁኑ ወቅት ይህን ወረርሽኝ መግታት እና መከላከል ትልቅ አገራዊ የትኩረት አጀንዳ ነው። የዜጎችን ህይወት እና ጤና፤ የአገርን ህልውና እና ደህንነት አደጋ ላይ የጣለውን የዚህን ወረርሽኝ ስርጭት ለመመከት የሁላችንም ጥረት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው። እስካሁን በተለያዩ አገራት የተከሰተውን የወረርሽኙን ስርጭት፣ እንዲሁም የዓለም ጤና ድርጅት እና የአገራችን የጤና ባለሙያዎች እና ተቋማት የሚያቀርቧቸውን ሙያዊ መረጃዎች እና ምክሮች ከግምት በማስገባት መንግሥት ወረርሽኙን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወቃል። ህዝቡ ስለበሽታው መረጃ ኖሮት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲችል ስለወረርሽኙ ባህሪያት እና መተላለፊያ መንገዶች በየጊዜው ከሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች በየደረጃው እንዲወሰዱ መንግሥት ውሳኔ ማስተላለፉ እና መመሪያዎች መሰጠታቸው ይታወሳል።
መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች ኃላፊነት ካለው አካል የሚጠበቁና ሊበረታቱ የሚገባቸው ናቸው። ምክንያቱም ችግሩ እየከፋ ሄዶ ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ እንኳንስ በድሃ አገር አቅም አላቸው በተባሉ ትልልቅ አገራት ጭምር የፈጠረው ችግር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እየተመለከትን ነውና። ባለፉት 18 ቀናት በአገራችን የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 23 መድረሱ መንግሥት ወቅታዊውን አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እየተከታተለ ዕለት በዕለት የሚወስዳቸው እርምጃዎች ከዚህም በላይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው ያመላክታል።
ይሁንና ከዚህ እጅግ አሳሳቢ አደጋ ህዝብንና አገርን ለመታደግ መንግሥት እያወጣቸው ያሉ መመሪያዎች በራሳቸው ከችግሩ አያድኑም። ይልቁኑ ውጤታማ መሆን አለመሆኑ ኅብረተሰቡ መመሪያዎችን ተቀብሎ በመተግበር ረገድ በሚያሳየው ቁርጠኝነት ይወሰናል። ሀዝባችን ከመንግሥት እና ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ መመሪያዎችን በጥብቅ ዲስፕሊን ከፈጸማቸው ችግሩ ጉልህ ጉዳት ሳያስከትል የሚያልፍበት ዕድል እንዳለ ሁሉ መመሪያዎችን በመተግበር በኩል ቸልተኝነት ከታየ ለአሳዛኝ ጉዳት ልንዳረግ የምንችልበት ዕድልም ከፍተኛ ነው።
ብልህ ከጎረቤቱ ይማራል እንዲሉ ቀደም ሲል በቻይናና ጣሊያን ከተከሰተው ነገር እንደ ህዝብ ብዙ መማር ይቻላል። በቻይና ከመንግሥትና ከጤና ባለሙያዎች የተላለፈውን ጥብቅ መመሪያ በመከተልና በመተግበር አደጋው ሊያደርስ የነበረውን ታላቅ ጉዳት መቀነስ የተቻለ ሲሆን በጣሊያን በታየው ቸልተኝነት ይሄው አሁን ድረስ ትልቅ ዋጋ በመክፈል ላይ ይገኛል። ከሰሞኑ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መልዕክት የሚያስተላልፉ የሃይማኖት አባቶች በአጽንኦት እንደገለጹትም መላው ኅብረተሰብ ከመንግሥት የሚተላለፉ መመሪያዎችን በጽናት በመተግበር ራሱን ቤተሰቡንና አገሩን ከአደጋ ሊጠብቅ ይገባል።
ከዚህ አንጸር እስካሁን ያለውን ሁኔታ ስንገመግም መላው ኅብረተሰብ የችግሩን አስከፊነት በሚገባ ተረድቶ በሚፈለገው መጠን ራሱን ቤተሰቡን አገሩን እየጠበቀ ነው ለማለት አያስደፍርም። የቫይረሱ ዋነኛ መተላለፊያ መንገድ ንክኪ መሆኑን በመግለጽ ብዙ ህዝብ ከሚሰባሰብባቸው ቦታዎች ራሰን ማራቅ፣ አካላዊ ፈቀቅታን መጠበቅ እንደሚገባ ተደጋግሞ ምክር ቢሰጥምና ብዙ ሰራተኛ በቤቱ ሆኖ እንዲሰራና ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ መንግሥት እርምጃ ቢወስድም አሁንም ብዙ ሰዎች ይህን በሚገባ ሲጠቀሙበት አይስተዋልም። ትምህርት ቤት እንዲዘጋ የተደረገው ልጆች ከአላስፈላጊ ቅርርብ ርቀው ከበሽታው እንዲጠበቁ ቢሆንም ብዙ ህጻናት ሰፈር ውስጥ ተሰባስበውና ተቀራርበው ሲጫወቱ ይስተዋላል። ይህ ደግሞ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል በኃላፊነት መንፈስ ትኩረት ሰጥቶ ሊያስተካክለው የሚገባ መሆን አለበት።
በአጠቃላይ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ከደቀነብን ትልቅ አደጋ መትረፍ የሚቻለው በመደማመጥ፣ ምክርን በመስማትና የሚተላለፉ የመንግሥትና የህክምና ባለሙያዎችን መመሪያዎች በጥብቅ ዲስፕሊን በመፈጸም ብቻ በመሆኑ ከመንግሥት እየተላለፉ ያሉ መመሪያዎች በጥብቅ ዲስፕሊን ሊተገበሩ ይገባል እንላለን።
አዲስ ዘመን መጋቢት 22/2012
ኮሮናን ለመከላከል በመንግሥት የተሰጡ መመሪያዎች በጥብቅ ዲስፕሊን ይተግበሩ!