• “የኢትዮጵያ እናቶች እናት” በመባል የሚታወቁና የረጅም አመት የማህጸን ሀኪም በመሆን ያገለገሉ ናቸው።
•እ.አ.አ በ1924 ሲድኒ አውስትራሊያ ውስጥ ተወለዱ።
•እ.አ.አ በ1959 ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እቅዳቸው ሦስት ሳምንት የመቆየት ብቻ ቢሆንም በርካታ ሴቶች ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው በመገንዘብ ከመሄድ ይልቅ መቆየትን መረጡ።
•እ.አ.አ በ1974 አዲስ አበባ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነውን የፌስቱላ ሆስፒታል አሰሩ።
•ይህ ሆስፒታል ከ45 ሺ በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከህመም ፈውሶ መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ አድርጓል።
•ዶክተር ካትሪን ሴቶችን የመርዳት ተግባራቸው ሴቶችን በማከም ብቻ የተገደበ አልነበረም። አዋላጅ ነርሶችን የማሰልጠን ሕልማቸውን ለማሳካት በ2000 ዓ.ም የሐምሊን አዋላጅ ነርሶች ማሰልጠኛ ኮሌጅ እንዲቋቋም በማድረግ በርካታ ባለሙያዎች በየገጠሩ እንዲሰማሩ ማድረግ ችለዋል።
•ለ60 አመት በኢትዮጵያ የፌስቱላ ህሙማንን በማከም ሰርተዋል።
•ዶክተር ካትሪን ሃምሊን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያለ እድሜ ጋብቻንና የተራዘመ ምጥን ተከትሎ በሚከሰት ሽንትንና ሰገራን መቆጣጠር ያለመቻል ችግር ይሰቃዩ የነበሩ በርካታ ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ሲታደጉ ኖረዋል።
•ዶክተር ካትሪን የአዲስ አበባውን ጨምሮ በሃገሪቱ ስድስት የሃምሊን ፌስቱላ ሆስፒታሎችን በማቋቋም ሴቶች ከሚገጥማቸው የፌስቱላ በሽታ በነጻ ታክመው እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር ይደርስባቸው ከነበረ የመገለልና የስነ ልቦና ስብራት መታደግ ላይ ሰርተዋል።
• በበጎ ተግባር ላይ ተሰማርተው የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ችግርን የቀረፉት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የኢትዮጵያ የክብር ዜግነትና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።
• ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በዋጋ ለማይተመነው አበርክቷቸው በርካታ ሽልማቶችንና ክብሮችን ተቀዳጅተዋል። ከነዚህም መካከል
• የቀዳማዊ ኃይለስለሴ የሰብአዊነት ሽልማት
• የኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ ሽልማት
• የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ኮሌጅ የክብር ወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት
• የአውስትራሊያ ከፍተኛ ብሄራዊ ሽልማት
• አለም አቀፍ የጤና ምክር ቤት የላቀ አፈፃፀም ሽልማት
• የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ሽልማት
• የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአውስትራሊያ
ማኅበር ሽልማት
• የሮተሪ ኢንተርናሽናል አለም አቀፍ የሰላም ሽልማት
• የእንግሊዝ ህክምና ማህበር ሽልማት
• የሲዲኒ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሽልማት
• የአውስትራሊያና ኒው ዚላንድ ጦር ዘማቾች የሰላም ሽልማት
• የታላቁ የቅድስ ጊዮርጊስ የላቀ የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት
• የዞንታ አለም አቀፍ ሽልማት
• የኤደንብራ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ኮሌጅ የክብር ሽልማት
• የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የህይወት ዘመን ሽልማት
• የ2009 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው።
• ከነዚህ ሽልማቶች በተጨማሪ ካትሪን ሐምሊን እ.አ.አ የ1999ና የ2004 የኖቤል ሽልማት እጩ ሆነው ቀርበው ነበር።
• እ.አ.አ በ2009 ‹‹ተለዋጭ ኖቤል›› በመባል የሚታወቀውና አስቸኳይ ምላሽ ለሚሹ አለም አቀፍ ፈተናዎች ተግባራዊና ተምሳሌታዊ የሆኑ መፍትሔዎችን ላፈለቁ አካላት የሚሰጠው የ‹‹ራይት ላይብሊሁድ ሽልማት ›› ተበርክቶላቸዋል።
• ባለፈው ዓመትም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሀገራችን በተለይም በፊስቱላ የተጠቁ ሴቶችን ከችግራቸው በመፈወስ ለሰሩት ስራ ሽልማት አበርክተውላቸዋል።
• ዶክተር ካትሪን ሀምሊን በ96 አመታቸው መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ስርዓተ ቀብራቸውም በጳውሎስ ወጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም