የሰው ልጅ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ቀጣይነት ያለው የአዲስ ሃሳብ ፈጠራ ጠቃሚ እንደሆነ ከገባው ብዙ ዘመናትን አስቆጥሯል:: በዚህም የሰው ልጅ አዳዲስ ሃሳቦችን ማፍለቅና መፍጠር ጠቃሚነቱ ሰፊ መሆኑን ተረድቷል:: ልዩ ነገር የማሰብ፣ አዲስ ሃሳብ የማፍለቅና የመፍጠር ችሎታ የሰው ልጅ ልዩ ባህሪያት ናቸው::
ልዩና አዳዲስ ሃሳቦች ከተለዩ ሰዎችና አጋጣሚዎች ይፈልቃሉ ተብሎ ይታሰባል:: ሃሳብ ከጅምሩ የብዙ ሰዎችን ቀልብ አይገዛም:: ሃሳብ የሰዎችን የተሳሰተ አተያይ የሚያቃናና መስመር የሚያስይዝ ሊሆን ይገባል::
አንዳንድ ሰዎች ሃሳብ የሚያፈልቁ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው ብለው ያስባሉ:: የሰው ልጅ አዳዲስና የተለዩ ሃሳቦችን ማፍለቅ የሚያስችል አቅም አለው:: ለዚህም ትዕግስተኛና ቁርጠኛ ሆነን አዳዲስ ሃሳቦችን መጠበቅ አለብን:: አዳዲስ ሃሳቦችን ማስተናገድ የሚያስችል አውድ መፍጠርና ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል:: የሃሳብ ፈጠራ ከፍ ባለ ደረጃ እንዲያድግ ብዙ ሥራዎች ሊሠሩ ይገባል:: አስቻይ አውድ ሊኖር ይገባል:: ማህበረሰቡም ከለመደው አስተሳሰብ የተለዩ ሃሳቦችን ሊያበረታታና ሊያቅፍ ይገባል::
ሃሳቦች በግለሰብ ደረጃ ነው የሚፈልቁት:: አንዳንድ ሰዎች ሃሳ ባቸውን ለጓደኞች፣ የሥራ ባለደረቦችና ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ፈጥነው ያጋራሉ:: ሌሎች ደግሞ ሃሳባቸውን ያዝ አድርገው ሳያጋሩ ረዘም ያለ ጊዜ ይቆያሉ:: ሃሳቦች ቅቡልነት እንዲያገኙ ለሰፊው ማህ በረሰብ ቀርበው መሞገት አለባቸው:: አንዳንድ ሃሳቦች ተወዳዳሪ ባለመሆናቸው ተግባራዊነትና ተቀባይነት ሳይኖራቸው ሲቀሩ ብዙ ሃሳቦች ግን ያለበቂ ምክንያት ቅቡልነት ሳይ ኖራቸው ይቀራል:: ይሁን እንጂ በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች ሃሳቦች ለመመርመር ብዙ የመረጃ ምንጮች አሏቸው::
በጣም ብዙ ሰዎች አዲስ ሃሳብን ሲጋፈጡ ምቾት አይሰማቸውም:: የሰው ልጆች ያልተለመደን ነገር ይፈራሉ:: አዲስ ሃሳብ ሲነሳ የተነሳውን ሃሳብና ሃሳቡን ያነሳውን ግለሰብ በጣም ብዙ ሰዎች ያገላሉ:: ከዚህ አልፎም ሃሳቡን ያነሳውን ግለሰብ ባህል፣ አስተሳሰብና የፖለቲካ አቋም ማያያዝ የተለመደ ነው::
በሀገራችን የሃሳብ ዕድገት እንዳይኖር ብዙ መሰናክ ሎች አሉ:: ከእነዚህም ዋነኞቹ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ፖለቲ ካና የማህበረሰብ ንቃተ-ህሊና ናቸው:: አንድ ሃሳብ ሲነሳ ሃሳቡን ከመሞገት ይልቅ ሃሳቡን ከሆነ ነገር ጋር ማያያዝና ማጣጣል የተለመደ ነው:: ተገቢና ጠንካራ ሃሳቦች አንደ መርዝ ተወስደው እንዲፈሩ ተደርጓል:: አዲስ ሃሳብም ውግዘት እንዲገጥመው ብዙ ተሠርቷል::
አዲስ ሃሳብን ማውገዝ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተለ መደ ነው:: በባለፉት 100 ዓመታት አንድ የመንግስት ሥርዓት በሌላኛው ሥርዓት በኃይል ሲፈነገልና በባሰ አምባገነን ሲተካ ቆይቷል:: አዲሱ ሥርዓት የማህበረ ሰብ የሕይወት አካል ሆኖ የተለየ ሥርዓት እንዳይፈጠ ርና ሌላ ሥርዓት እንደማያስፈልግ እንዲታሰብ በሰፊው ተሠርቷል::
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መድበለ- ፓርቲ ሥርዓትን ቢፈቅድም መሬት ላይ ያለው ዕውነታ ግን ሌላ ነበር:: ባለፉት 18 ወራት አበረታች ያሉት አበረ ታች ሁኔታዎች የሃሳብ ብዝሃነት እንዲለመልምና እንዲያ ድግ አስተዋፅዖ ይኖራቸዋል::
ንቃተ-ህሊና በማደግ ላይ ባለ ማህበረሰብ አዲስ ሃሳብ ማንሳት ብዙ ጣጣዎች አሉት:: እነዚህም ማገለል፣ ስድብ፣ ውግዘትና ተቀባይነትን ማሳጣት ናቸው:: ከዚህም አልፎ ማህበረሰብን አለመቀበልና መናቅ ተደርጎም ይቆ ጠራል::
ለምሳሌ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትዳር መያዝን ከፍተኛ ቦታ ይሰጣል:: ምንም እንኳን ትዳር መያዝ የሰዎች የግል መብት ቢሆንም ትዳር ያልያዙ ሰዎች በማ ህበረሰቡ የሚኖራቸው ተቀባይነት አነስተኛ ቦታ ይሰጣቸ ዋል:: ትዳር ያልያዙ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ትዳር እንዲይዙ ጫና ይደረግባቸዋል:: በእኔ አምነት ይሄ ሰው የራሱን የተለየ ሃሳብ እንዳያራምድ ማደናቀፍ ይመስለ ኛል። በአጠቃላይ አዲስና የተለየ ሃሳብ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን ለማህበራዊና ለፖለቲካዊ ጉዳዮ ችም ከፍተኛ ፋይዳ አለውና የሃሳብ ብዝሃትና ማከበርና አዲስ ሃሳብ ማፍለቅ ይጠናከር እላለሁ::
አዲስ ዘመን መጋቢት 19 / 2012
በላይ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ