አዲስ አበባ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዲፕሎማቶችና ሚሲዮኖች ጋር በቀጣዩ ሳምንት ይወያያሉ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአንድ ሳምንት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሥራዎች መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመጪው ሰኞ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥራ ኃላፊዎች፣ በውጭ አገራትና በዋና መስሪያ ቤት ከሚገኙ የሚሲዮን መሪዎች እና ዲፕሎማቶች ጋር ይወያያሉ፡፡ ውይይቱ የሚደረገው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተተገበረ ስለሚገኘው ለውጥ፣ ባለፉት 10 ወራት ውስጥ የተገኙ የዲፕሎማሲ ውጤቶች እና ቀጣይ የውጭ ጉዳይ ተልዕኮ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡
በዚህ ወቅት ባለው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ይበልጥ ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ በተለይ ኢትዮጵያዊነት በዓለም ጎልቶ እንዲወጣ፣ ከዳያስፖራው ጋር ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአገራቸው አምባሳደር ሆነው እንዲንቀሳቀሱ፣ የዜጎች ክብር የሚረጋገጥበት፣ ብሔራዊ ደህንነት የሚጠበቅበት፣ ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ የሚጎለብትበት ሁኔታዎች ላይ እንደሚመከርም አቶ መለስ ዓለም ገልጸዋል፡፡ በውይይቱ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮችን ጨምሮ 60 ሚሲዮን መሪዎችና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ወደ አገር እየገቡ ሲሆን፤ ከውይይቱ በኋላ በቀጣይ ቀናቶች ሚሲዮንና የውጭ ጉዳይ ሥራ ዘርፎች የተናጠል ውይይቶችና የክንውን ሪፖርት ግምገማ ያደርጋሉ፡፡
አቶ መለስ እንዳስታወቁት፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የሚያስጀምሩት ወቅታዊ፣ አገራዊ፣ አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ የፓናል ውይይት ይደረጋል፡፡ የፓናል ውይይቱ ላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን እና ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበት ይሆናል፡፡ ሌላኛው መርሐ ግብር ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2011 ዓ.ም ‹‹የኢትዮጵያ ባህል ቀን›› የሚል ስያሜ የተሰጠው በአዲስ አበባ ተቀማጭ ለሆኑ አገራት አምባሳደሮችና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነሮች የሚጋበዙበት በዓይነቱ የተለየ ፕሮግራም ነው፡፡
ፕሮግራሙ የተዘጋጀው አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ዲፕሎማቶች ከተማዋን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ፕሮግራሙ የእንጦጦ ተራራን በመውጣት አፄ ምኒሊክ ቤተ መንግሥትንና ሙዚየም መገብኘት፣ የሱሉልታ ያያ መንደርን በማቅናት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ የሚያሳይ ሙዚየም ይጎበኛል፡፡ ይህ ፕሮግራም በውጭ ጉዳይ አስተባባሪነት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት ኦፕሬተሮች ማህበር፣ የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ይሳተፉበታል፡፡
በተያያዘ ዜናም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ነብያት ጌታቸውን በቃል አቀባይነት ሾሟል፡፡ አቶ ነብያት ጌታቸው የመጀመሪ ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና እንግሊዝ አገር ከሚገኘው ሊድስ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ኮሚኒኬሽን ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው፡፡ አቶ ነብያት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰሜንና ደቡብ አሜሪካ እና ካሪቢያን ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በሚኒስትር ካቢኔ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ጀነራል፣ የኢፌዴሪ አፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ዳይሬክተር፣ በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር እና በተለያዩ የፖለቲካ ዲፓርትመንት በዴስክ ኦፊሰርነት ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ አገልግለዋል፡፡
አዲስ ዘመን ጥር 4/2011
ሰላማዊት ንጉሴ
I always look forward to reading your posts, they never fail to brighten my day and educate me in some way Thank you!
Your blog has quickly become one of my favorites I always look forward to your new posts and the insights they offer
Taraftarium24, ücretsiz ve HD kalitede canlı maç yayınları sunan popüler bir online spor platformudur.
Justin TV maç yayınlarına kolay erişim sağlayarak favori takımlarınızın maçlarını canlı izleyebilirsiniz.
justin tv
From the bottom of my heart, thank you for being a source of positivity and light in this sometimes dark and overwhelming world