አዲስ አበባ፡- (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ፣ ኤርት ራና ሶማሊያ መሪዎች ከዚህ ቀደም የፈረሙትን የሦስትዮሽ ስምምነት ለማስፈጸም ቁርጠኛ መሆና ቸውን አረጋገጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፣ ከኤር ትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከሶማሊ ያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር በአስመራ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም መስከረም 2011 ዓ.ም የፈረ ሙትን የሦስትዮሽ ስምምነት ለማስፈጸም ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ማረጋገጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
የስምምነቱን አፈጻጸም ከመገምገም ባለፈም ለ2012 እና ቀጣይ ዓመታት የጋራ የሽብር ስጋቶችን ለመቀልበስ፣ የሕገ-ወጥ የሰዎች፣ የመሣሪያ እንዲሁም የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውርን ለመግታት የሚሆን የትግበራ ዕቅድ አውጥተዋል። በተጨማሪም፣ ሦስቱ መሪዎች ሀገራቱ ያሏቸውን የሰው እና የተፈጥሮ ሀብቶች በጥቅም ላይ በማዋል፣ የጋራ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ተስማምተዋል።
ሀገሮቹ የሦስትዮሽ ትስስራቸውን የሚያጎለብት የትብብር ስምምነት በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም በኤርትራ መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዲላሂ ተፈራርመውታል። ስምምነቱ ሦስቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች በትብብር እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑም በወቅቱ ተገልጿል።
አዲስ ዘመን ጥር 19/2012