ጨንቻ፡- ሰብዓዊነትና ሰብዓዊ ክብር መስጠትን ከጨንቻ ማረሚያ ተቋም መማራቸውን የህግ ታራሚዎች ገለጹ።
በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በጋሞ ዞን ጨንቻ ወረዳ ጨንቻ ከተማ የሚገኘው የጨንቻ ማረሚያ ተቋም ታራሚዎች ለአዲስ ዘመን ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት፣ተቋሙ በታራሚዎች ሰብዓዊ አያያዝና ክብር አስመስጋኝ ሥራ እየሰራ ነው።
ወደ ማረሚያ ተቋሙ ከገባች ሦስት ዓመታትን ማስቆጠሯን የምትናገረው የህግ ታራሚ መምህርት አማረች ዱሬ ተቋሙ በታራሚዎች አያያዝና እንክብ ካቤ በኩል የሚሰራውን ሥራ “እንደ ቤቴ ነው” ስትል ገልጻዋለች። አመራሩና የፖሊስ ጥበቃ አባ ላቱ የሚያደርጉላቸው እንክብካቤ የሚያስመሰግንና ቤተሰባዊነትን የተላበሰ እንደሆነ የገለፀችው የህግ ታራሚዋ የሰብዓዊነትን ትምህርት ያገኘችበት ቦታ እንደሆነ አመልክታለች።
ሌላው ታራሚ በልሁ ቆሎባ ከአንድ ዓመት በላይ በማረሚያ ተቋሙ ማስቆጠሩን ገልፆ፣ በሚደረግላቸው እንክብካቤና ሰብዓዊ አያያዝ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል። ‘’ተቋሙን እንደቤታችን እንድንመለከተው የሚያደርጉ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ይከናወናሉ፤ በገቢ ማስገኛ ሥራዎችም ተጠቃሚ ሆነናል’’ ያለው የህግ ታራሚ በልሁ፤ህጉ በሚያዘው መሰረትም መብታቸው ተጠብቆ እየታነፁ መሆኑን አስረድቷል።
ከአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት በዝውውር ወደ ጨንቻ ማረሚያ ተቋም ከመጣ 9 ወራትን ያስቆጠረው የህግ ታራሚ መኮንን አየለ፤ የጨንቻ ማረሚያ ተቋም በታራሚዎች አያያዝ የተሻለና ምቹ መሆኑን ተናግሮ፣ መብታቸው ተጠብቆ ወንጀልን እንዲጠየፉና እንዲታነፁ እየተደረገ መሆኑን ተናግሯል።ይህ በፊት ከነበረበት ቦታ የተለየ መሆኑን ጠቅሷል።
ታራሚ ወጣት መኮንን የወንጀልን አስከፊነትና የሚያደርሰውን ጉዳት በማረሚያ ቤቱ የተማረ ስለሆነ ታንፆ ከወጣ በኋላ በመልካም የዜግነት መንፈስ ያስከፋውን ማህበረሰብና ሀገሩን ለመካስ መዘጋጀቱን ገልጿል።
የማረሚያ ተቋሙ ኃላፊ ኮማንደር አጥናፉ አሰፋ ማረሚያ ተቋሙ ታራሚዎችን ከማነፅና ከማረም በተጨማሪ በተለያዩ የቀለምና የሙያ ትምህርት መስኮች አብቅቶ አንድም የእውቀት ሌላም የጥበብ አቅማቸው እንዲያድግ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኮማንደር አጥናፉ፤ በተቋሙ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ያስከፋውን ማህበረሰብና ሀገሩን ለመካስ መዘጋጀቱን ገልጿል።
የማረሚያ ተቋሙ ኃላፊ ኮማንደር አጥናፉ አሰፋ ማረሚያ ተቋሙ ታራሚዎችን ከማነፅና ከማረም በተጨማሪ በተለያዩ የቀለምና የሙያ ትምህርት መስኮች አብቅቶ አንድም የእውቀት ሌላም የጥበብ አቅማቸው እንዲያድግ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኮማንደር አጥናፉ፤ በተቋሙ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት በመደበኛ ትምህርት ከ1-8ኛ ክፍል ድረስ እና በሽመና፣ ብረታብረት ፣ እንጨት ሥራ፣ በጓሮ አትክልት ልማት፣ ከብት እርባታ እና ብሎኬት ማምረት ሥራዎች ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
እንደ ኮማንደር አጥናፉ ገለጻ ፤ተቋሙ በሁሉን አቀፍ የማረምና የማነፅ ተግባራት፣ በህግ ታራሚዎች አያያዝ፣ በሰብዓዊ መብት አከባበር እና መሰል የተሻሉ አፈፃፀሞች በማስመዝገቡ በ2008 ዓ.ም የምስክር ወረቀትና ትንሹ የቪዲዮ ካሜራ፣ በ2009 ዓ.ም
የምስክር ወረቀቶች፣ በ2010 ዓ.ም የምስክር ወረቀቶች ዋንጫና ሁለት ባለ 43 ኢንች ቴሌቪዥኖች፣ በ2011 ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣ የምስክር ወረቀት፣ ዋንጫ፣ 80 ሺህ ብር እና ስምንት ኮምፒዩተሮች፣ በ2012 ዓ.ም ደግሞ አንድ ሞተር ብስክሌት እና የዋንጫ ሽልማት እንዲሁም የ50 ሺህ ብር ስጦታ ተበርክቶለታል።
በ1945 ዓ.ም የተመሰረተው የጨንቻ ማረሚያ ተቋም በአሁኑ ወቅት 410 ወንድ እና 24 ሴት በድምሩ 434 የህግ ታራሚዎችን እያስተናገደ ይገኛል።
አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2012
ድልነሳ ምንውየለት