«ገበሬው ምርቴን የማሳድግበት አቅም አጣሁ፤ ላኪው ጥራት ያለው፣በብዛትና በዓ ይነት የምልከው ምርት አጣሁ፤ ባንኮች ደግሞ የውጪ ምንዛሬ አጣሁ ይላሉ፡፡ ይሄ አብሮ አቅዶ መስራት ላይ ብዙ የሚቀር መሆኑን ያሳያል፡፡ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረገው ለላኪዎች ብቻ እንጂ ለአምራቹ ጭምር አይደለም።ላኪው ምርቱን ከአምራቹ ካላገኘ ምኑን ይልካል?።» ይሄ የተደመጠው የኢትዮ ጵያ ንግድ ባንክ ከወጪ ንግድ ጋር ተያይዞ በሚሰራው ሥራ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች በምን ይስተካከሉ በሚለው ዙሪያ ከላኪዎች ጋር ምክክር በካሄደበት ወቅት ነው፡፡ በምክክሩም የወጪ ንግዱ ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ገበያ ተመሳሳይ አሰራር የሚከተል፣ ተመሳሳይ ችግሮች የሚንፀባረቁበት፣ የአቅም ውስንነት የሚታይበት፣ የምርቶች የጥራት መጓደል እና የተደበላለቁ አሰራሮች የተሸበበ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በውይይቱ ሀሳባቸውን የሰነዘሩት አቶ ፉአድ መሀመድ የቁም እንስሳት ነጋዴ ናቸው፡፡ አገሪቱ ያላትን የእንስሳት ሀብት እንዴት መጠቀምና ትርፋማ መሆን እንዳለበት እየታሰብ አለመሆኑን ይናራሉ፡፡ በእንስሳት ወጪ ንግድ በኩል ምንም ዓይነት የብድር አቅርቦት ማግኘት እንዳልቻሉ ይገልጻሉ፡፡ መንግስት የወጪ ንግዱን ለማሳደግ ያለውን እድል በሙሉ እየተጠቀመ እንዳልሆነና ትኩረት እንዳልተሰጠው ይጠቅሳሉ፡፡
አቶ ፉአድ እንደሚናገሩት፤ የስጋ ምርት ለውጭ የሚያቀርቡ ቄራዎች የቁም እንስሳት የሚረከቡት ከገበሬ ነው፡፡ ቄራዎቹ ስጋውን አዘጋጅቶ ለመላክ አቅም ያላቸው እና ብድ ርና ሌሎች ድጋፎችን የሚያገኙ ናቸው፡ እንስሳቱን የሚያቀርቡት ግን የገንዘብም የማደለብ ስራውንም በብቃት ለመስራት አቅም የላቸውም፡፡ ይሄ በፋይናንስ ተቋማትም ሆነ በመንግስት ያልታየና ያልታሰበበት ትልቅ ክፍተት ነው፡፡ እንስሳት አርቢዎች በገንዘብ እጥረት ምክንያት ለእንስሳቶቹ በቂ መኖ እያቀረቡ በአጭር ጊዜ ደልበው ለገበያ እንዲቀርቡ አያደርጉም፡፡ ይሄ ደግሞ በወጪ ንግዱ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ይፈጥራል።
በውጪ ገበያ የስጋ ምርት በብዛት በሚፈለግበት ወቅት እንስሳት አቅራቢዎች በአጭር ጊዜ ሊያቀርቡት በማይችሉት መጠን እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፡፡በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ለእለት ኑሮ መደጎሚያ፣ ያለዝግጅትና ያለእቅድ እየሰሩ በመሆኑ በቋሚነት መስራት እንደማይችሉ አቶ ፉአድ ይናገራሉ፡፡ የእንስሳቱን ዋጋ የሚተምኑት ቄራዎች በመሆናቸው እንስሳት አርቢዎቹ ለማድለብ ያወጡትን ወጪና ማትረፍ ያለባቸውን ስለማያገኙ ዳግም እንስሳቱን አደልበው ለቄራ የማቅረብ አቅም ያላቸው ጥቂቶቹ ናቸው ።ይሄ አሰራር የሚያበረታታ አይደለም፡፡ ገበሬዎች ወጪ ንግዱን ደጋፊ እስከሆኑ ድረስ በስራው እንዲቆዩ የብድር አቅርቦት ማበረታቻ ሊያገኙ ይገባል፡፡
«የአገሪቱ የወጪ ንግድ እየተዳከመ የመጣው እስካሁን ድረስ ምርት አምርተው በሚያቀርቡት ላይ ባለመሰራቱ ነው»ያሉት ደግሞ የቅባት እህሎች የወጪ ገበያ አቅራቢ አቶ ጣሰው ሀይሉ ናቸው፡፡ አገሪቱ ባላት የማምረት መጠን እንድታመርት፣ የወጪ ንግድ ምርቶች በጥራትም በብዛትም እየተሻሻለ እንዲመጣ፣ በጥናትም፣ በእቅድም ድጋፍ ለማድረግ እየተሞከረ አለመሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ገበሬው ባለው እውቀትና አቅም ኑሮውን ለማሸነፍ ሲል እንደምንም ያመርታል እንጂ ለንግድ ብሎ ትርፉን አስቦ ተበድሮ ስራውን እያሻሻለ ለመሄድ የሚያስችለው እድል እያገኘ እንዳልሆነ ይገልጻሉ፡፡
‹‹የምርት መጠን መጨመር ከምርጥ ዘር እና መካናይዜሽን ግብርና ጋር ብቻ መያያዝ የለበትም›› የሚሉት አቶ ጣሰው፤ አምራቹ የብድር አቅርቦት ቢያገኝ በራሱም፣ በመተጋገዝም እንደየአካባቢውና ሁኔታ መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችለውን ሥራ ይሰራል፡፡
አቶ ጣሰው እንደሚገልጹት፤ የወጪ ንግድ በደፈናው ነው የተጠቃለለው፡፡ ሁሉም የወጪ ገበያ ዘርፍ እኩል አዋጭ አይሆንም፡፡ አይደለምም፡፡ ማበረታቻውንም ብድሩንም ተጠቅሞ ትርፋማ መሆን ያልቻለ ዘርፍ አለ፡፡ እንዲሁም ምርቶቹን ለውጪ ገበያ ለማድረስ የሚወጣው ወጪ እና የሚገኘው የውጪ ምንዛሬም ተመጣጣኝ አይደለም፡፡ በባንኮች በኩል የውጪ ንግድ የብድር አቅርቦታቸው ላይ አገልግሎትና ስራቸውን በማስፋት ችግሩን ለመቅረፍ መስራት አለባቸው፡፡
አቶ ስዩም አለሙ የእብነበረድ ማዕድን ላኪ ናቸው፡፡ የውጪ ንግድ እንደ ማንኛውም ንግድ አይነት በአጭርና አነስተኛ ጊዜ፣ ቦታና ገንዘብ የሚንቀሳቀስ አለመሆኑ ልብ እንዳልተባለ ይሰማቸዋል፡፡ የሌሎች አገራት ገበያ ላይ መሳተፍ በቂ ዝግጅት፣ አቅምና መጠን አስፈላጊ ቢሆንም የኢትዮጵያ ላኪዎች በብዙ ችግሮች ምክንያት ይህንን እያሟሉ አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡
አቶ ስዩም እንደሚናገሩት፤ ለላኪዎች በተቻለ መጠን ድጋፍ ይደረግና አምራቾች ይረሳሉ፡፡ በዚህ ደግሞ ላኪዎችም ይቸገ ራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ላኪዎች ብድርም ማበረታቻም ተጠቅመው የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ አይሆኑም፡፡ ባንኮችም ምርት አቅራቢ አርሶ አደሮችን አስበው ለመደገፍና አብሮ ለማትረፍ አይሰሩም፡፡ለአምራቹም ሆነ ለላኪው ተመሳሳይ ድጋፍ አለመደረጉ በወጪ ንግዱ ላይ የተፈለገውን ያክል ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል።
‹‹ስጋ አምራች ቄራዎች ድጋፍ ያገኛሉ፣ ከብት የሚያቀርቡ ግን ይረሳሉ፡፡ የቅባት እህል ላኪዎች ማበረታቻ ያገኛሉ፣ አምራቾች የልፋታቸውን እንኳን አያገኙም፡፡ ምርቱን ለመላክ መጀመሪያ መመረት እንዳለበት ተረስቷል፡፡ ለላኪዎች የሚያቀርቡትን በብ ድር አግዞ ከአምራቾቹም ጋር ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችሉ ባንኮችም ዘንግተው ታል፡፡» ይላሉ አቶ ስዩም፡፡
ገበሬው ምርቴን የማሳድግበት አቅም አጣሁ፣ ላኪው የምልከው ምርት አነሰ ሲል ባንኮች ደግሞ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ገጠመኝ የሚሉት በተመሳሳይ ጊዜ ነው ይላሉ፡፡ ይሄ ችግሩን ለመፍታት ትርፋማ ለመሆን አብሮ አቅዶ መስራት ላይ ብዙ የሚቀር መሆኑ ያሳያል፡፡
‹‹የእብነበረድ ምርት ለውጭ ለማቅረብ ከአምስት ዓመት በፊት ከተረካቢ ድርጅቶች ጋር በቶን 300 ዶላር ተስማምተን ሥራ ጀመርን፡፡ አሁን ዋጋው ጨምሮ የማቀርበው በ500 ዶላር ነው፡፡ ንግድ ሚኒስቴር ግን በተመሳሳይ መጠን የዋጋ ትመናው አሁንም ድረስ 300 ላይ እንደቆመ ነው›› የሚሉት አቶ ስዩም፤ በተለዋዋጭ የንግድ ዓለም ባረጀ አሰራርና ዋጋ ተመን ተይዞ በገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንደማይቻል ያስረዳሉ፡፡ ይሄንን ተከታትሎ ማስተካከል፤ሲሆንም ለአገር ውስጥ አምራችና ላኪዎች የተሻለ ዋጋ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተ ዋል፡፡
የውጪ ምንዛሪን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻ ልና የኤክስፖርት ዘርፉን ለመደገፍ ብድር ከማቅረብ ባለፈ የዓለም ገበያ እንዴት እየሄደ እንደሆነ ተከታትሎ ያሉትን እድሎች ለመጠቀም ላኪው ይሯሯጣል እንጂ ተቋማት ምንም ዓይት ጥረት እያደረጉ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ስለዚህ በታሰበው ልክ ውጤታማ ለመሆን መንግስትም ባንኮችም ለፍተው በመስራት ለማትረፍ መንቀሳቀስ እንዳለባ ቸው አስገንዝበዋል፡፡
እንደ አቶ ስዩም ገለጻ፤ አገሪቱ አዳዲስ የውጪ ንግድ ምርቶችን መላክ እንድትጀምር እና አዳዲስ ባለሀብቶችን ለማፍራት እየተሰራ አይደለም፡፡ ባንኮችም ያለውን ማስቀጠል እንጂ የንግድ ሀሳቦች ላይ አብረው ሰርተው አብረው ማደግና ማትረፍን እንደ ሥራ የያዙት አይመስልም፡፡ መንግሥትና የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሻሻልና ለመቀየር መልፋት አይፈልጉም፡፡ ፕሮፖዛል ላይ ብቻ ተንጠልጥለው መገምገም እንጂ ያለውን የንግድ ሁኔታ ምን እንደሆነ አጥንቶ የመጣው ሀሳብ ላይ የቢዝነስ አቅማቸውን ማዋል አይጥሩም፡፡ በወጪ ንግዱ ላኪዎች ብቻ እንደማይጠቀሙበት ሁሉ ብቻቸውን ሊለፉም አይገባም።
ሌላው ችግር በማለት አቶ ስዩም የተናገ ሩት ደግሞ«ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ለውጪ ዜጎች እንደሚቀርቡ ታስቦ የነሱን የመግዛት ፍላጎት ከሌሎች ጋር መወዳደር የሚያስችል መንገድ ለመፍጠርና አቅም ለማዳበር እየተሰራ አይደለም» በማለት ይገልጻሉ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጢቆ ላኪዎች ከሰጡት ሀሳብ በአንዳንዱ ላይ ይስማማሉ፡፡ሆኖም ግን በአገሪቱ የውጪ ንግድ ዘርፍ ላይ የባንኮች ሚና ምን መሆን አለበት፣ባንኮች የወጪ ንግዱን እንዴት ያግዛሉ የሚሉ ስራዎች በየጊዜው እንደሚሰሩ ይገልጻሉ፡፡ ባንኮች ላኪዎች ወደ ገበያው እንዲገቡ ብድር በማቅረብ የውጪ ምንዛሬን በማፈላለግ እገዛቸው ከፍ ያለ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
እሳቸው እንደሚሉት ደግሞ ለውጪ ገበያ የሚደረገው ማበረታቻና ድጋፎች እየጨመሩ የመጡ ቢሆንም የወጪ ንግዱ ግን እያሽቆለቆለ ይገኛል፡በተመሳሳይ የምርት መጨመር መኖሩ እየተነገረ ቢሆንም የወጪ ንግድ ግን እየቀነሰ መጥቷል፡፡ የውጪ ንግዱ ከአጠቃላይ የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ያለው ድርሻ እንዲሁ እየወረደ መጥቶ ስምንት በመቶ ያህል ብቻ ሆኗል፡፡
ላለፉት ሰባት ዓመታት የዓለም ገበያ ባለበት እየቀጠለ ሲሄድ፣ ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት መካከል የሚደረገው እየወረደ መጥቶ 2008 ላይ የማገገም አዝማሚያ አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ግን ከነበረበት እየወረደ መጥቷል፡፡ የአገሪቱ የወጪ ንግድ ሁኔታ ከሁሉም ሲወዳደር መቀነስ ብቻ ሳይሆን በአሳሳቢ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይገኛል፡፡
እንደ አቶ ለገሰ ማብራሪያ፤ ባንኮች ላለፉት 20 ዓመታት ለወጪ ንግድ ላኪዎች በአነስተኛ ወለድ በብድርም፣ በውጭ ምንዛሪ አቅርቦትም ቅድሚያ በመስጠት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ከአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት አንስቶ ብትጀምርም፣ መጠን እና የምርት ዓይነቶች እምብዛም ለውጥ አላሳዩም፡፡ እንዲሁም ወደ ዓለም ገበያ ኢትዮጵያ ከተቀላቀለች ረዥም ጊዜ ቢያስቆጥርም፣ በአሰራር ሂደት፣ በእቅድ እና ትርፍ ውጤታማ የሚያስብል አይደለም፡፡ ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች የአቅርቦት እጥረት፣ የጥራት ጉድለት እና አማራጭ የገበያ መዳረሻ ውስንነት እየተፈተነ ይገኛል፡፡
የገበያ ተቀባይ በመሆኗ ለማምረት የሚወጡ ወጪዎች በየደረጃው ያሉ ባለድርሻዎች የሚገባቸውን ዋጋ እያገኙ አይደለም፡፡ በቀጣይ ችግሮቹን ለመፍታት ሁሉም መስራት አለበት፡፡ በላኪዎች ላይ ያተኮረው የባንኮች ድጋፍም አምራቹ ጋር መድረስ አለበት ሁሉም የተስማሙበት ሀሳብ ነው፡፡
አዲስ ዘመን ታህሳስ 20/2011
ሰላማዊት ንጉሴ
Hello! Do you know if they make any plugins to help
with Search Engine Optimization? I’m trying to
get my website to rank for some targeted keywords but I’m not seeing
very good results. If you know of any please share. Thank you!
You can read similar art here: Warm blankets