አዲስ አበባ፡- ሰሞኑን በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት ሐይማኖታዊ ገጽታ እንዲላበስ መደረጉ በሁሉም ሃይማኖቶች ዘንድ ተቀባይነት እንደሌ ለው የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ አስታወቀ።
ጉባዔው ትናንት በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገሪቱ የሚታየው ውጥረት፣ አለመረጋጋትና ግጭት መልክና ሁኔታውን እየቀያየረ ሃይማኖታዊ ገፅታ እንዲላበስ መደረጉ፣ የሃይማኖት ተቋ ማትን በድፍረት የማፍረስ፣ የማራከስና የሃይ ማኖት መሪዎችን እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙ ነት የሌላቸው ንፁሐን ወገኖችን ማጥቃት በሁሉም ሃይማኖቶች ተቀባይነት የሌላቸው ድርጊቶች ከመሆናቸውም በተጨማሪ ወን ጀል በመሆናቸው ሊወገዙ እንደሚገባ አስታው ቋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የታየው አለመረጋጋትና ግጭት ሙሉ በሙሉ ተወግዶ እርቅና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ከዘወትር የፀሎት ተግባራቸው ጎን ለጎን ሁሉንም ወገኖች ሲመክሩና አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦችን ሲያቀርቡ እንደነበር የገለፀው ጉባዔው፤ አገሪቱ ሰላሟና አንድነቷ እንዲጠበቅና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጥረት ፍሬ እንዲያፈራ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ሰላምና ብሔራዊ መግባባት ለማጠናከር እንዲሰሩ ጠይቋል።
ጉባዔው አሁን የሚታየውን አገራዊ ውጥረት ከሃይማኖት ጋር ለማያያዝ የሚደረ ገው ሙከራ የየሃይማኖቶችን መሠረታዊ አስተምህሮ ካለመገንዘብና ከጭፍን ወገንተ ኝነት የመነጨ ስሜት መሆኑን በመረዳትና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ኅብረተሰቡ የአገሩንና የየአካባቢውን ሰላም በጋራ ነቅቶ እንዲጠብቅም አሳስቧል።
‹‹አሁን በአገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና አስጨናቂ እየሆነ ነው›› ያለው ጉባዔው፣ በኢትዮጵያውያን መካከል መጥፎ ጠባሳ እየጣለ ያለው ይህ ያልተለመደ ግጭት ከእምነትም ሆነ ከኢትዮጵያዊ የመከ ባበርና በሰላም አብሮ የመኖር እሴት ጋር የሚቃረን በመሆኑ እንደ አገር እየታየ ያለው አለመረጋጋትና ግጭት ተወግዶ ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታና ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ ሁከትንና ግጭትን ከሚያባብሱ ሃሳቦችና ድርጊቶች መታቀብ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
ግጭት በሚቀሰቅሱ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና የሚመለከተው የፍትህ አካላት አስቸኳይ ማጣራት በማድረግ ወንጀል የፈጸሙትን በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርጉም ጠይቋል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 19/2012
አንተነህ ቸሬ