አዲስ አበባ፡- ከኢትዮጵያ ወደውጭ ሀገራት የሚላኩ አንዳንድ ምርቶች ላይ የሚ ስተዋለው የደረጃ መጓደል በሀገር ገጽታ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ የኮሚ ዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ይስማ ጅሩ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገራት ለሽያጭ የሚቀርቡ አንዳንድ ምርቶች ደረጃቸውን ባለመጠበቃቸው በሀገር ገጽታ ላይ እያሳደረ ያለው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ የእነዚህ ምርቶች የደረጃ መጓደል ምክንያቱ በአንዳንድ ላኪዎች ዘንድ የሚስተዋለው የግንዛቤ ጉድለት ነው። ማንኛውም ምርት ወደ ውጭ ሀገራት ሲላክ የምርቱን ምንነት የሚገልጹ ዝርዝር መረጃ ዎችን ሊያሟላ እንደሚገባ የሚናገሩት አቶ ይስማ በአንዳንድ ላኪዎች ዘንድ ይህ ልማድ ያለመኖሩ ግን ተቀባይ ሀገራቱ ምርቶቹን እን ዳይረከቡና መልሰው እንዲልኩት እያደረገ ነው ብለዋል።
አብዛኞቹ ተቀባይ ሀገራት ምርቶችን ለመቀበል የራሳቸው ቅድመ ሁኔታ አላቸው የሚሉት አቶ ይስማ አንዳንድ የሀገር ውስጥ ላኪዎች ግን ይህን እንደማያሟሉና ተቀባይ ሀገራት ለሚፈልጓቸው መስፈርቶች ትኩረት እንደማይሰጡ ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ወደውጭ ሀገራት ምርቶች ሲላኩ የተቀባይ ሀገራትን የደረጃ ፍላጎት ያገ ናዘበና ከተስማሚነት የምዘና ድርጅት በላቦራ ቶሪ የተረጋገጠ ሰርተፊኬት ሊኖር እንደሚ ገባ የጠቀሱት አቶ ይስማ፣ ከዚሁ ጋር ተያ ይዞም የምርት ይዘቱ፣ የተመረተበት ወቅትና የማጠናቀቂያውን ጊዜ የሚጠቁም በቂ መረጃ መካተት እንደሚኖርበት ጠቁመዋል።
በአንዳንድ ላኪዎች ዘንድ ከሚስተዋ ለው የግንዛቤ ክፍተት በዘለለ በምርቶቹ ላይ ባዕድ ነገሮችን መቀላቀልና ለሚዛን ክብደት ሲባል ውሃ የመንከር ልማድ እንዳለ የተና ገሩት ዳይሬክተሩ ይህ ሆኖ ሲገኝም ተቀባይ ሀገራቱ በምርት ጥራትና የደረጃ መጓደል ምክንያት ወደ ሀገራችን እንደሚመልሱ ተና ግረዋል።
ምርቶቹ ያለምንም ጥቅም እንዲመለሱ መደረጋቸው ለላኪዎቹ ከፍተኛ ኪሳራ ከማስከተል በዘለለ በሌሎች ምርቶች ላይ ጭምር ተአማኒነትን እንደሚያሳጣ የተናገ ሩት አቶ ይስማ ከምንም በላይ ግን በሀገር መልካም ገጽታ ላይ የሚፈጥረው በጎ ያልሆነ ተጽዕኖ የጎላ እንደሆን ጠቁመዋል።
የሀገር ውስጥ ላኪዎች ምርቶቻቸውን ከመሸጣቸው አስቀድሞ የተቀባይ ሀገራትን የደረጃ ፍላጎት በማወቅ ተገቢውን መረጃ መያዝ ይኖርባቸዋል የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ ሀገራችን የዓለም አቀፉ የደረጃዎች ድርጅት (አይኤስኦ) አባል በመሆኗ ላኪዎች ይህንን መስፈርት ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው አስ ታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ወደውጭ ሀገራት ከምትልካ ቸው ምርቶች አብዛኞቹ የግብርና ውጤቶች ሲሆኑ በርካቶቹም የአመራረት፣ የአያያዝና የአጠባባቅ ጉድለት እንደሚስተዋልባቸው
ዳይሬክተሩ ገልጸው፣ ላልተገባ ጥቅም ሲባል በአንዳንድ ላኪዎች ዘንድ የተለመደው ሕገወ ጥነትም በሀገሪቱ የውጭ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝም ተናግረ ዋል።
አቶ ይስማ እንደሚሉትም ለዚህ ችግር ትኩረት በመሰጠቱ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ የጥናትና ምርምር ክፍል ተዋቅሮ በዘርፉ ላይ ጥናት የሚያደርግ ቡድን ተደራጅቷል። አብዛኞቹ ላኪዎች ከተቋሙ ጋር ያላቸው ግንኙነት ያነሰ በመሆኑም ክፍ ተቱን ለመሙላት የሚያስችል ግንዛቤ የመፍ ጠር ተግባር በመከናወን ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ጊዜ እየተገነባ ባለው የሥልጠና አካዳሚ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተሻለ ትስስር ለመፍጠር ጥረቱ ይቀጥላል፣ ያሉት አቶ ይስማ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከደረጃ ተቋማት ጋር በማስተሳሰርም የላኪ ዎችን ግንዛቤ የማሳደግና የሀገርን መልካም ገጽታ የመመለስ ተግባራት እንደሚከናወንም አክለው ገልጸዋል።
አምራች ድርጅቶች አስቀድመው በቂ መረጃዎችን የመጠየቅ፣አደረጃጀቱን የማወ ቅና የምርት ጥራት ፍተሻውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው፣ ያሉት ዳይሬክተሩ በገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘትም ለደረጃ ዎች ጥራት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አሳ ስበዋል።
ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ የቅባት እህሎ ችና የቆዳ ውጤቶችን ወደተለያዩ ዓለማት የምትልክ ሲሆን፣ በመስፋፋት ካለው የኢን ዱስትሪ ፓርኮች ጋር ተያይዞም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ አልባሳትንና መሰል ምርቶችን ለሽያጭ እያቀረበች ትገኛለች።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥቅምት 15/2012
መልካምስራ አፈወርቅ