አንዳንድ ሰዎች የተወለድንበት ቀንና ወር ስለ ማንነታችን እና ባህሪያችን ብዙ ይናገራል ብለው ያምናሉ። ማመን አለማመን የየሰው ምርጫ ቢሆንም አብዛኛው የወራት ትርጉም ትክክለኛ ናቸው ብለው የሚከተሉ ሰዎች እንዳሉ መዘንጋት የለበትም። ከእያንዳንዱ ወር ጋር ግንኙነት ያላቸው 12 የዞዲያክ ምልክቶች አሉ። እነዚህም ኤሪስ፣ ታውረስ፣ ጀሚኒ፣ ካንሰር፣ ሊዮ፣ ቪርጎ፣ ሊብራ፣ ስኮርፒዮ፣ ሳጂታሪየስ፣ ካፕሪኮርን፣ አኳሪየስ እና ፒሰስ ይሰኛሉ።
የተወለድንበት ወር ባህሪያቶቻችን፣ አመለካከቶቻችን እና ለህይወት ያለን ስሜቶች እና ሰዎች ለእኛ ያላቸውን አመለካከት ጭምር ለማወቅም ይጠቅማል ይላሉ። የአስትሮሎጂ አጥኚዎች የተወለድንበትን ወር በወሩ ላይ ከሚያርፉ ከዋክብት ጋር በማዛመድ ይህን መሰል ትንታኔ አቅርበዋል። ለዛሬ የተወሰኑትን ቀንጭቤ ላቅርብ።
ጥር
በጥር ወር የተወለዱ ሰዎች መንፈሰ ጠንካራ፣ የማይበገር አመለካከት ያላቸው እና ሰዎች እንዲህ አድርጉ ብለው እንዲመክሯቸው የማይፈልጉ እንደሆኑ ይገለፃል። በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ጎበዝ ነገር ግን ሌሎችን የማይሰሙ አለቃ ይወጣቸዋልም ተብሏል። እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማስተማር ብቃት ያላቸው ሲሆን፤ ጠንካራ የስራ ስነ ምግባርን የተላበሱ ናቸው። የመሰላቸውን ለመናገር ወደኋላ የማይሉ መሆናቸውም ነው የሚነገረው።
የካቲት
የልደት በአላቸውን በየካቲት ወር የሚያከብሩ ሰዎች ደግሞ በውይይት የሚያምኑ፣ አመለካከቱ የወረደ ነው ብለው ከሚገምቱት ሰው ጋር ደግሞ መነጋገር የማይሹ ናቸው ተብሏል። የፈጣሪ አዕምሮ ባለቤቶች፣ በአዳዲስ እና ልዩ የስራ ዘርፎች መሰማራት የሚወዱ፣ ጉብኝት የሚያዘወትሩ፣ ታማኝ እና ሀቀኛ መሆናቸውም ይነገራል።
መጋቢት
በመጋቢት ወር የተወለዱ ሰዎች አዲስ ሃሳብ ለማፍለቅ የተፈጠሩ፣ አይን አፋር እና ጭምት እንደሆኑ ነው መረጃው የሚያመለክተው። የኪነ ጥበብ ስራዎች ራሳቸውን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ሲሆን፤ ለመመሰጥ ጸጥታን እንደሚመርጡም ይነገራል። እነዚህ ሰዎች ለሰዎች ሩህሩህ፣ ቅን እና መልካም አሳቢ ቢሆኑም የራሳቸውን ምስጢር እና ግላዊ ነገር ለመደበቅ የሚሞክሩም ናቸው። በራሳቸው አለም የሚኖሩ፣ ሰላማዊ አውድ የሚፈልጉ እና ብዙ ጊዜ ጫጫታ እና ጭንቅንቅ በሚበዛበት ስፍራ የማይገኙ ናቸውም ተብሏል።
ሚያዚያ
ትዕዛዝን በአግባቡ የማይቀበሉ፣ ነገሮችን በራሳቸው መንገድ የሚመለከቱ እና ሌሎችንም በዚሁ አስተሳሰባቸው ወደራሳቸው ለማምጣት የሚጥሩ ፤ በሚያዚያ ወር ይህቺን አለም የተቀላቀሉ ሰዎች መገለጫ ነው ይላል የናቹራል ሂሊንግ ሜጋዚን ድረ ገፅ ዘገባ። በአቅራቢያቸው ከሚገኝ ማንኛውም አካል ትኩረት እና ፍቅር ይሻሉ፤ በጀብዱ የተሞላ ህይወት ይፈልጋሉ፤ አንዳንድ ጊዜም ጠንከር ባለ ንግግራቸው ይታወቃሉ። በህዝብ ፊት የሚያደርጉት ነገር ግድ የማይሰጣቸውና ቢጸጸቱ እንኳን ከድርጊታቸው በኋላ መሆኑም ይነገራል።
ግንቦት
ለሁኔታዎች የሚቀያየሩ (የገበታ ውሃ)፣ የዛሬ እና ነገ ፍላጎታቸው የተለያየ፣ ብቸኝነት የሚከብዳቸው እና ጠንካራ የማህበራዊ ህይወት ያላቸው ናቸው።
በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ስሜታቸውን በደንብ የመግለጽ ብቃት ያላቸው ሲሆን፤ በተለያዩ የእድሜ ክልል ከሚገኙ ሰዎች ጋርም ማውራት ይወዳሉ። በቀላሉ ለድብርት የሚጋለጡ በመሆኑም የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን ይመለከታሉ ተብሏል።
ሰኔ
በሰኔ ወር ከምቹው የእናታቸው ማህጸን ወደዚህች አለም የተቀላቀሉት ደግሞ ሰዎች የሚወዱት አይን አፋርነት እና ጭምትነትን የተላበሱ ናቸው ይላል ዘገባው። በቀላሉ ስሜታቸው የሚቀያየር እና ለሌሎች ሰዎች ደህንነት አብዝተው የሚጨነቁ መሆናቸውንም መረጃው ያመለክታል። አርቆ የመመልከት እና ሃሳባቸውን ወደ እውን የመቀየር ልዩ ችሎታ እንዳላቸውም ይነገራል።
ሀምሌ
በሀምሌ ወር የተወለዱ ሰዎች በሰኔ ከተወለዱት ጋር ተመሳሳይ ባህሪ እንዳላቸው ነው የሚነገረው። ይሁን እንጂ ወሬ የሚያበዙ፣ ከላይ ከላይ በራስ መተማመን ያላቸው እና ለጋስ መስለው ለመታየት የሚሞክሩ ነገር ግን በውስጣቸው ተንኮል እና ምስጢር የሚይዙ፤ ህመማቸውን ለሌሎች ሰዎች ከመናገር የሚታቀቡ ናቸው። በመዝናኛ ስፍራ የማይጠፉ፣ በሀይል የተሞሉ እና ጨዋታ አዋቂዎች በመሆናቸውም ሰዎች በአቅራቢያቸው አይጠፉም።
በነሃሴ ወር የተወለዱ ሰዎችም፦
– ጥልቅ ሃሳብ እና ትንተና በሚፈልጉ ስራዎች ስኬታማ ናቸው።
– ህይወት በደረጃ እና በምክንያት
የምትራመድ ነች ብለው ያስባሉ።
– ስሜታቸውን ለመግለፅ አይደፍሩም።
– ተፈጥሮ ለመሪነት ያጨቻቸው ናቸው።
– ልበ ሙሉ እና ሃሳባቸውን በድፍረት
ለመናገር ወደኋላ የማይሉ ናቸው።
በመስከረም የተወለዱ ሰዎች፦
– ሰዎች መልካም ነገር እንዲያደርጉላቸው
አብዝተው ይመኛሉ።
– ለኩርፊያም ቅርብ ናቸው።
– ስራቸው ፍፁም ትክክለኛ እንዲሆን
ያስባሉ።
– አዳዲስ ሃሳብ አፍላቂ፣ የተረጋጋ ስብእና
የተላበሱ እና ሰዎችን ለመርዳት የሚታ
ትሩ ናቸው ሲል ድረገፁ አስፍሯል።
ምንጭ፦
www.naturalhealingmagazine.com
አዲስ ዘመን መስከረም 19/2012
መርድ ክፍሉ