ጥንታዊቷና ዘመናዊቷ ቻይና
በአፍላ የወጣትነት ዘመኔ በትምህርት ቤት ስለ ዓለም ታሪክ ስማር በመሬት ስፋት ከሩሲያ ቀጥላ ስለምትታወቀው ቻይና፤ የአራት ሺህ ዓመት የሥነ ጽሑፍ ሀብትና ታሪክ ያላትና የጥንት ሥልጣኔ ባለቤት የሆነች ሀገር መሆኗን ተረድቼ ነበር፡፡ ስለሆነም ቻይና በዓለም ቀዳሚ ጀማሪ ስለሆነችባቸው አንዳንድ የፈጠራ ሥራዎች፤ ስለ ፈላስፋው ኮንፊሺየስ—ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ በተጨማሪም በተለይ በዘመነ አብዮትና በዘመነ ኢሕአፓ ጊዜ ስለ አብዮተኛው ማኦ ዜዱንግና (ሴቱንግ) ሥራዎቹ፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስለነበረው ስለአብዮተኛው ቹኤን ላይ ፤ ስለ ቀዩ መጽሐፍ፤ ከገጠር ወደ ከተማ ስለተካሄደው ስለ ቻይና የባህል አብዮት…በስፋት የማንበብ እድሉ ነበረኝ።
ቻይና
በቀድሞዋ ሶቭየት ሩሲያ፤ በቫሮኔዥ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜም ስለ ዓለም የኮሙኒስት ፓርቲዎች ታሪክ ስንማር መምህሮቼ የማኦን ስም በክፉ በማንሣትና የቻይናን አብዮት ሲያጣጥሉና ሰውየው የማርክሲዝም-ሌኒኒዝም በራዥ ነው ሲሉ እሰማ ነበር፡፡ በፈተና ጊዜም ለውጤት ስንል የማኦን የአይዲዮሎጂ ግድፈት ተንትነን ማስረዳት፤ መጻፍ ስለነበረብን ቻይናን የምመለከታት የጎሪጥ ነበር፡፡ የሀገራችን ሕዝብም እአአ ከ1978 ዓመት በፊት ቻይና የነበራት ዓመታዊ ገቢዋ ከእኛ ሀገር ጋር ተመሳሳይና ድሀም ስለነበረች የሚያውቃት በድሮ ታሪኳ ነው፡፡
በቅርቡም በኢትዮጵያ የሕዝባዊት ቻይና የኢኮኖሚና የኮመርሻል ኮንሱላር የሆኑት እመት ልዩ ዩ በሒልተን ሆቴል ወደ ቻይና ሄደን ለተመለስን ሰዎች የራት ግብዣ በአደረጉበት ምሽት እንደተናገሩት ከዐርባ ዓመታት በፊት በቻይና ምግብ፤ ስኳር፤ ልብስ… ሁሉም ነገር በኩፖን እየተገዛ ለሕዝቡ ይዳርስ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ታክሎበት የሀገራችን ሕዝብ ስለቻይናና ስለቻይናውያን ያለው ግምት ዝቅተኛ ነበር፡፡ የሀገራችን ሰው ቻይናን እንደ ቀልድ እያደረገና እንደማትረባም እየገመተ፤ እያጣጣለ ይናገራል፡፡ ትንሽ አፍንጫው (አፍንጫዋ) አነስ ያለ፤ ያለች ልጅ ከወለደ ቻይና ብሎ ይጠራል፡፡ በቻይናውያን ላይም ብዙ ተረት ይተርታል፡፡ ይኸ ሁሉ ግን ዛሬ ቻይና የደረሰችበትን ካለማየትና ከግንዛቤ እጥረት የመጣ ነው፡፡
ብሔር ብሔረሰቦች
በቻይና 56 ብሔር ብሔረሰቦች ሰምና ወርቅ ሆነውና ኅብር ፈጥረው፤ ተዋድደው በሰላም ይኖራሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሆን ተብሎ የሚታወቀውና ቻይንኛን የአፍ መፍቻ ያደረገው የቻይና ሕዝብ 91ነጥብ5 ቢሊዮን ሲሆን፤ ቀሪው የአናሳ ብሔረሰቦች ስብስብ ነው፡፡ በአጠቃላይ የቻይና ሕዝብ ቁጥር 1ነጥብ 4 ቢሊዮን ሲሆን፤ ይኸውም ቁጥር ከፍ ሊል የቻለው እያንዳንዷ የቻይና ሴት (ከአናሳ ብሔረሰቦች ) በስተቀር ቀደም ሲል በተቀመጠው የወሊድ ቁጥጥር ሕግ ገደብ መሠረት አንድ ብቻ እንድትወልድ ተጥሎባት የነበረው ማዕቀብ በአሁኑ ጊዜ ሁለት ሁለት እንድትወልድ በመፈቀዱ ነው፡፡
ይህም የሕዝብ ቁጥር ከአፍሪካ የሕዝብ ቁጥር ጋር የሚተካከል ነው፡፡ በቁጥር አነስተኛ የሆኑት ብሔረሰቦች 4 የራስ አገዝ ክፍለ ሀገር ሲኖራቸው፤ የከተማ፤ የንዑስ ከተማና የቀበሌ አስተዳደርም አላቸው፡፡ ሁሉንም የቻይና ዜጎች ከከተማ እስከ ገጠር፤ ከጠረፍ እስከ ጠረፍ የሚያግባባቸው፤ ማስታወቂያዎችና ታፔላዎች የሚጻፉት ማንዳሪን ተብሎ በሚታወቀው የሀገሪቱ ቋንቋ ቻይንኛ ነው፡፡ እነዚህ አናሳ ብሔረሰቦች በሕዝባዊት ቻይና ምክር ቤት የ13ነጥብ6 በመቶ የውክልና ድምጽ አላቸው፡፡ ሕዝባዊት ቻይናን ለማየት የቻልኩት በቅርቡ ነው፡፡ ምስጋና ይግባቸውና ክቡር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀደም ሲል የኪነ ጥበብ ሰዎችን በቤተ መንግሥት ጠርተው ስለ ጥበብና ጠቢባን ጠቀሜታ ገለጻ ባደረጉበት ወቅትና ከዚሁ በመነሣት 50 የኪነ ጥበብ ሰዎች ወደ ቻይና ሄደው ጎብኝተውና ልምድ ቀስመው እንደሚመለሱ በተናገሩት መሠረት እኔም ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር በኩል እድሉ ስለተሰጠኝ ቻይናን አይቼና ጎብኝቼ ተመልሻለሁ፡፡
ሥራ ወዳድነትና የሕዝብ አንድነት
ሁላችንም እንደምንገነዘበው እኛ ኢትዮጵያውያን ሥራ ወዳዶችና የሥራ ጊዜን አክባሪዎች አይደለንም፡፡ ይልቁንም ሥራ የሚሠራ ይናቃል፤ ሳይሠራ ሠርቆ፣ አጭበርብሮ የሚበላ ይከበራል፡፡ እንደጀግናም ሊቆጠር ይችላል፡፡ ከነተረቱ «እገሌ ጌታ ነው፤ ሥራ ሳይሠራ ቁጭ ብሎ ይበላል» ይባላል፡፡ሥራ የማይሠራ ዘመናይ ሰው ሲፎክርም «ወንዱ የዱባ ቀንዱ፤ ቁጭ ብሎ እሚውል በጥሩው ሥራ፤ ታጥቦ ቀራቢ እንደ ሙሽራ» ይላል፡፡ «ሥራ ለሠሪው፤ እሾህ ላጣሪው» የሚለው ተረትና ምሳሌም የሚያሳየን ሥራ መሥራት ያለበት የተወሰነ ሰው ብቻ መሆኑን ነው፡፡ የቻይና ሕዝብ ሥራ ወዳድ መሆኑ በሀገራችንም፤ በመላው ዓለምና በራሳቸው በቻይናውያንም የታወቀ ነው፡፡ በቻይና ውስጥ ሁሉ ነገር ፈጣን ነው፡፡ ጊዜው፣ ልማቱ፣ ሕዝቡ፣ ሕንፃው፣ሌቱ፣ ቀኑ፣ የድራጎን መልክና ቅርጽ ያለው ባቡሩም ቢሆን ፈጣን ነው፡፡
56 ብሔር ብሔረሰቦችና አናሳ ቁጥር ያላቸው ጎሳዎች ኅብር ፈጥረውና ሰምና ወርቅ ሆነው በፍቅርና በመተሳሰብ በሚኖርባት ሕዝባዊት ቻይና የሕዝቡ አንድነት፤ የሀገር ፍቅር ስሜቱ፤ የሰንደቅ ዓለማው አለኝታነቱና አክባሪነቱ፤ የሕግና የሥርዓት ተገዥነቱ፤ በመንግሥት ላይ ያለው እምነቱና ታማኝነቱ፤ ሥራ ወዳድነቱ፤ ከሌብነትና ከአጭበርባሪነት የራቀ መሆኑ፤ እርስ በርስ የመከባበርና የመግባባት ስሜቱ፤ ቅንነቱ፤ የተፈጥሮ ሀብት ተንከባካቢነቱ፤ አንድነቱ ከብረት የጠነከረና የሚያስቀናም ነው፡፡
ሕዝቡ ለታላቂቱ ሀገር ለቻይና ኃያልነት፤ ለመንግሥቱና ለፓርቲው ገናናነት ሁልጊዜ በትጋት
ይሠራል፡፡ የኮሙኒስት ፓርቲውን ዓርማ እንደ ዓይኑ ብሌን፤ እንደ ህልውናው አድርጎ በመላ አገሪቱ በክብር ያውለበልበዋል፡፡ በሥራ ቀን ሥራ የፈታ ቦዘኔ በመንገድ ላይ አይታይም፡፡ ጠዋትና ማታ ሕዝቡ ለሥራ ሲጣደፍ ይስተዋላል፡፡
እንግዳ አክባሪነትና ትሕትና
ሁላችንም እንደምንገነዘበው እኛ ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባዮችና አክባሪዎች ነን እንላለን፡፡ ይህ ግን ከቻይና ሕዝብ መስንግዶ ጋር ሲነጻጸር የእኛ የለበጣ ይመስላል፡፡ ቻይናውያን እንግዶቻቸውን የሚቀበሉትና የሚጋብዙት በፍጹም ትሕትና ፍቅር ቆመው፤ አደግድገውና ታላቅ ክብር ሰጥተው ነው፡፡የቻይና ሕዝቦች እርስ በርስ ከመግባባትና ከመከባበር አልፈው ለውጭ አገር ዜጋ የሚሰጡት ክብር እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡
ቻይናውያን የትም ቦታ «ሺሸ» ፤ የትም ስፍራ «ኛኦ» በማለት በፈገግታና በፍቅር ስሜት ሆነው ለውጭ አገር ዜጎች አክብሮታቸውን ይገልጻሉ፡፡ እንግዳው የሚፈልገው ነገር በፍጥነት ይቀርብለታል፡፡መንገድ ቢጠፋበት ቻይናውያን እስከሚፈልገው ቦታ ድረስ በገዛ ገንዘባቸው በታክሲ አሳፍረው ያደርሱታል፡፡ የማንደሪን ቋንቋ ካለማወቅ የተነሣ ግንኙነት ለመፍጠር በጥቅሻና በምልክት ቋንቋ ጭምር ተጠቅመው ያስተናግዳሉ፡፡ ቻይናውያን አንተ ነጭ ነህ፤ አንተ ደግሞ ጥቁር፤ ቢጫ ነህ በሚል አድልዎ አያደርጉም፡፡
የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ
ቻይናውያን ከከተማ እስከ ገጠር የተፈጥሮ ሀብታቸውን ጠብቀው ይኖራሉ፡፡ በዚህም በቻይና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፤ እንክብካቤ አያያዝ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ይታያል፡፡ የቻይና ተራራ በደን ፤ ሜዳና ረባዳው በአዝርዕት፤ በአትክልትና በፍራፍሬ የተሸፈነ በመሆኑ ሁልጊዜ አረንጓዴ ነው፡፡በአብዛኛው የቻይና ሜዳ ውኃ ገብ በመሆኑ በሩዝ ሰብልና በየአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ተጨናንቆ ይታያል፡፡
በቻይና ያፈጠጠና ያገጠጠ ተራራ፤ ጦም ያደረ፤ የተራቆተ መሬት አይታይም፡፡ በልምላሜ የተዋቡ ተራሮችና ዳገታማ አካባቢዎች በፀሐይ ቃጠሎ እንዳይጠወልጉ፤ ዐፈራቸው በዝናብ፤ በነፋስ፤ በጎርፍና በማዕበል እንዳይጠራረግ ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህም የተነሣ፤ የተናደና የተንሸራተተ
መሬት፤ ያፈጠጠና ያገጠጠ ተራራ፤ የተንሸራተተ ዳገትና በወራጅ ውኃ የተፈጠረ ዐፈረ ገደልና ቁልቁለት…አይታይም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ ለም ዐፈር እንዳይጠረግ ጋራውና ሸንተረሩ፤ ተራራው፤ ሜዳውና ረባዳው በእርከን ሥራ፤ በሽቦና በብረት ሰንሰለት እንደ እሥረኛ ተተብትቦና ተያይዞ አሸዋ ግርፍ ተገርፏል፡፡
ከላይና ከሥር ደግሞ ሐረግና አበባ ተተክሎበት ፤ በላዩም ላይ እንደ ሐረግ ዘምቶበት የተለየ ውበት ፈጥሮ ይታያል፡፡ የለመለመውን ሣር፤ የተለያየ ኅብረ ቀለም ያለውን አበባ በየዛፉና በየመንገዱ ዳር ግራና ቀኝ ያስተዋለ ሰው ወደ ማያውቃትና ልዩ ፕላኔት ወደ ሆነች ምድራዊት ገነት የገባ ያህል ስለሚቆጥረው የተለየ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ማንም ሕዝብ የሥነ ኑረትን ( ኢኮሎጂ) ሕግና ሥርዓት አክብሮ ያለ ስንፍናና ያለ ሌብነት፤ ያለ ኻኬት በቅንነት ከሠራ ዓለምን በቀላሉ ሊለውጣት እንደሚችል በ40 ዓመት ውስጥ ተምዘግዝጋ ያደገችው ቻይና እንደ ምሳሌ ልትሆነው ትችላለች፡፡
በአሁኑ ጊዜ በቻይና የገበያ ማዕከላት አስተማማኝ የምግብ ፍጆታና የሸቀጥ ምርት፤ በየሆቴሉና ሬስቶራንቱ የተትረፈረፈ ምግብ ሊገኝ የቻለው ሕዝቡ የተፈጥሮ ሀብቱን በአግባቡ ስለሚጠብቅና ስለሚንከባከብም ጭምር ነው፡፡ የቻይና መሬት እንዲህ እንደ ሕፃን ልጅ በእንክብካቤ የተያዘና በሰብልና በደን የተሸፈነ ነው
እምነት
ከቻይና ሕዝብ 65 ከመቶው በእግዚአብሔር የማያምንና እምነት አልባ ስለሆነ «ዛሬ ዓመታዊ የማርያም፣ የገብርኤል፣ የሚካኤል፣ የጊዮርጊስ ንግሥ ነው፤ ወርኃዊ ቅዳሴ፤ በዓል አለብኝ፤ ሥራ አልነካም ዛሬ አቡየ ናቸው» ብሎ የሚጨነቅ አይደለም፡፡ «የቻይና ሕዝብ ዛሬ የእገሌ ቀብር፣ ዐርባ፣ ሰማኒያ፣ ሙት ዓመት፣ ክርስትና፣ ልደት፣ የቆብ ተዝካር፣ -ቁርባን…ነው፤ ነገ የገና፣ የፋሲካ፣ የትንሣኤ በዓል ነው» ብሎ ሥራ የሚያቆምበት መንገድ የለውም፡፡ ካልሠራ እንደማይኖር ስለሚያውቀው ሁልጊዜ በሥራ የተጠመደ (ጽሙድ) ነው፡፡
በሌላ መንገድ የቡድሂዝም፤ የታኦኢዝም፤ የእስልምናና የክርስትና (ካቶሊክና ፕሮቴስታንት) እምነት ያላቸው ሰዎች ሲኖሩ የማምለኪያ ቦታዎቹ እንደልብ በየቦታው አይታዩም፡፡ ቤጂንግ ለ23 ቀናት ስዘዋወር
አንድ መስጊድ፤ አንድ የካቶሊክ፤ አንድ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን፤ እንደዚሁም በጉይጆ ክፍለ ሀገር የሑዋንግሁዋሾው ፏፏቴ ባለበት አንድ የካቶሊክ ቸርች ከማየት ውጭ ሌላ የማየት እድል አልገጠመኝም፡፡ ቻይናውያን ሲሞቱ በአካባቢያቸው በሚገኝ ዳገታማ ቦታ ላይ ይቀበራሉ፡፡መቃብራቸው ላይ ትናንሽ ሐውልቶችና የደንጋይ ካቦች ፤ ልዩ ልዩ የአበባ ዓይነትና ዛፍ ይታያል፡፡
ትራንስፖርት
በቻይና መንገድ በእጅጉ ለምቶና ተስፋፍቶ ይገኛል፡፡ ሁሉም እንደፈለገ በፈጣን መንገድ በባሕር በየብስ፤ በአየር የግንኙነት መስመሮች ማለት በአውቶቡስ፤ በታክሲ፤ በትራሌቡስ፤ በትራንቫይ፤ በትላልቅና በመለስተኛ ሐይገር፤ በቤት መኪና፤ በሜትሮ፤ በአውሮፕላን በመርከብ በመጓዝ ከፈለገበት ቦታ ይደርሳል፡፡ አገር አቋራጭ ባቡሮችና አውቶቡሶች፤ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች ተደራራቢና ረጃጅም የድልድይ መንገዶችን፤ አንዳንዴ ከአንድ ኪሎ ሜትር በላይ የሚደርሱ የተራራና የጋራ ውስጥ ዋሻ መሥመሮችን ተምዘግዝገው እያለፉ በየቦታው ይደርሳሉ፡፡ የአስፓልት መንገዶች ከከተማ እስከገጠር የየአርሶ አደር መንደሮችና የእርሻ ማሳዎች እስከ አሉባቸው ጣቢያዎች ድረስ ስለተዘረጉ በቻይና መንገድና የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ብዙ አሳሳቢና መሠረታዊም አይመስልም፡፡
መንገዶች ሰፋፊዎች ስለሆኑ በትራፊክ ፍሰት አይጨናነቁም፡፡ በየጊዜው አስፋልቱ በውኃ ስለሚታጠብ አቧራ ፈጽሞ የለም፡፡ አንዲት የወረቀት፣ የፌስታልና የተረፈ ምግብ… ቆሻሻ በቻይናዎች መሬት ላይ አትታይም፡፡ አየሩ በከተማም ሆነ በገጠር ለጤና ተስማሚ ነው፡፡ የትራፊክ አደጋ አብዛኛውን ጊዜ አይታይም፡፡ ሾፌሮች በተረጋጋ ሁኔታ ያሽከረክራሉ፡፡ ለእግረኞች ብርቱ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡የሠከረና ራሱን የጣለ ሰው ፈጽሞ በቻይና አይስተዋልም፡፡
መዝናኛና ፋሽን
የቻይና ሕዝብ ከእምነትና ከመንፈሳዊ በዓላት ይልቅ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ለባሀላዊ የድራጎን ፌስቲቫሎችና ለብሔራዊ በዓላት ነው፡፡ ሕዝቡ ራሱን ለማዝናናትና ለማጽናናት በዓመታዊ ፌስቲቫልና በአዲስ ዓመት ክብረ በዓል የባህልና ዘመን አመጣሽ (የፋሺን) ልብሱን እየለበሰ የድራጎን ዘመን፤ የአንበሳ ዘመን፤ የዝንጀሮ ዘመን፤ እያለ በኅብረት በመዝፈንና በመፈንጠዝ አዲስ ዓመቱን ያከብራል።
የአዝመራና የፀደይ ወቅት በዓላትንም እንዲሁ የስፖርት ትርእይት በመሥራት፤ የብስክሌት ውድድር በማድረግ፤ በመዋኘት የቴኒስ፤ የጠረጴዛ ቴኒስ፤ በመጫወት፤ የባድሜንተንና የውሾ ጨዋታን በማሳየት፤ ታሪካዊ ቦታዎችንና የቱሪስት መስህብ የሆኑ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በመደነስና በመዘመር በተለይ ወጣት ልጃገረዶች ዘመኑን የዋጀ የፋሽን አልባሳትን ለብሰውና ተውበው በየቦታው በመታየትጊዜያቸውን ያሳልፋል። ቻይናውያን በዕረፍት ሰዓታቸው ከሚጎበኙዋቸው ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ የተከለከለው ከተማና ታላቁ ግንብ የቻይና ሕዝብ ትልቁ ጸጋው ለተፈጥሮ ጽኑዕ ፍቅር ያለው መሆኑ ነው፡፡ ቻይናውያን የተሻለ የትምህርት ደረጃ፤ ቋሚ ሥራ፤ ብዙ ገቢ፤ ታላቅና አስተማማኝ የሆነ ማኅበራዊ ደኅንነት፤ የተሻለ የሕክምና አገልግሎትና ጤና፤ የመኖሪያ ቤትና ሰላማዊ የሆነ የመኖሪያ ስፍራ እንዲኖረው ስለሚፈልግ ሁል ጊዜም በትጋት ሕግንና ሥርዓትን፤ ማኅበራዊ ኑሮንም አክብሮ ይሠራል፡፡
አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2011
ታደለ ገድሌ ጸጋየ ዶ/ር
médicaments à prix abordable en Italie Biofarma Biel/Bienne médicaments sans ordonnance en Belgique
до чого сняться зради знак зодіаку після риби
скачати молитви миколи чудотворця безкоштовно міфи про місяць
і сонце урок 6 клас
If some one wants to be updated with latest technologies after that he
must be pay a visit this web page and be up
to date daily.
жаңа әлемдегі жаңа қазақстан тәрбие сағаты,
қазақстанның қасиетті рухани құндылықтары
тәрбие сағаты dns karaganda, technodom балалардағы асқазан
ішек жолдарынан қан кету, іштен қан кету идея
басни мартышка и очки
traceroute cisco, какие могут быть причины
неудачного завершения ping и tracert бабалар сөзі даналық көзі 11 сынып, бабалар сөзі даналық
көзі эссе сөз табы деген не, сөз таптары дегеніміз
не 3 сынып этил спирті химиялық қасиеті,
спирттердің жіктелуі және химиялық қасиеттері
дмитрий колдун ничего чего слушать покраска волос лунный
календарь декабрь, лунный календарь стрижек на
декабрь 2023 сонник тапочки одевать
тест на эмоциональное выгорание quiz,
тест на эмоциональное выгорание
маслач приснилось что переспала с парнем своей подруги
статья 147 ук рк судоводительское удостоверение, школа водного транспорта работа
в корее на заводе, работа в корее
шымкент қазақ қызы катя, тарас шевченконың қазақстан тақырыбына
арналған суреттерінің саны
prijs van medicijnen met voorschrift in Brussel Heumann Le
Rœulx Beste Online-Quellen für Medikamente ohne ärztliche Verschreibung in Zürich
как заработать много и без вложений работа из дома
как не сойти с ума варианты подработки на дому дом
горького режим работы
работа в логистическом центре дому подработка в доставке еды москва дом
сон работа выходной фриланс картинки для презентации