እግር እንይ
አርቀን ማስተዋል ማለት፤ የኛን ስልጣኔ ድልድይ
እግር ማየት ነው ብለዋል፤ እስቲ እንግዲህ እግር እንይ!
ያባቶችህ ያይን ድንበር፤ ከተረከዝ ሎሚ ሳያልፍ
አንተ ግን ጆቢራው – ዘራፍ
ጠረፍ አይወስንህ ጉብል
ጥሎህ በዘመንህ ዕድል
ዓይንህ ባት አልፎ እንዲዋልል፤
ቴህ ወዲያ ጀግንነት የለ፥ ተዚህ የዘረረ ግዳጅ
ባደባባይ የዱር ገደል፥ ስትናደፍ የእግር አዋጅ
ለሊቱን በየሌት- ‘ግለብ’ ቀኑን ጭምር በጠራራ
ሲነጋ እንደ ጠዋት ጆቢራ
በከተማህ ስታቅራራ በዕድሜህ መንከራተት ስራ፥
ካንዱ ቢሮ ሌላው ቢሮ፥ አቦል በረካውን ብለህ
ያገሩን ወሬ ተንትነህ
ተጨቃጭቀህ ተለፋልፈህ አመሳጥረህ፥ የዚያን ጉዳይ ከዚህ ጉዳይ
ዘጋግነህ በቡና ምገህ፥ አምጥተህ ደክመህ ስትለያይ፥
በዚህ ብቻ ሳታስቀረው፥ ደግሞ አዲሱን የአገር ጠባይ
ከልማድህ የቡና ሱስ ጋር፥ የዘመኑን ሳትለያይ
እስቲ ደግሞ አራዳ ወጥተህ፥ በከተማው አደባባይ
ያንዷን ካንዷ ዳሌና ባት፥ እግሯን ከእግር ጋር አስተያየው
ደርቶልህ ያገር ልጅ ቅልጥም
ዳሌው ባቷ እስኪፈረጥም
እየናረ እስኪያስገመግም
አንተ አድፍጠህ ከኃላዋ፥ በአይንህ ሳግ ስታነፈንፍ
ያቺን ልክፍ ያቺን ንድፍ
እያረክ ስታሾል፣ አንዷ ፈርታህ አንዷ ስታፈጥ
ተጠግታ ባቷ ሲያገምጥ
«ዘራፍ» ቀርቶ ቀልብህም «ውይ!»
እያለ ወኔህ እግር ይይ!
«በሰየጠኑትማ ዘንድ
አንዱን የባላንጣ ዘዴ፣ የባዕዳን ስውር መንገድ
ዘመናይ ጦር መሳሪያ ነው፣ ታዳጊ ሃገር ለማንጋደድ
እምነቱን ለማወናበድ
ያንድን ትውልድ የህልም አቅጣጫ
ወደፊት ሳይሆን ወደታች፣ አመንምኖ ማቀጨጫ!»
ቢልህ ፈጥጦ በግልምጫ
ለህሊናህ ማጋለጫ
ናቀው እርግፍ አድርገህ ተወው፣ ቴህ ብጤው ጋር አትንጫጫ።
ሰልጥነን ንቀን አልፈነው፣ የይሉኝታን መቀጣጫ
የኛ ዓይን የእግር ነው እንጂ፣ በቅቶት ህሊና መግለጫ።
አርቀን ማስተዋል ማለት፣ የኛን ስልጣኔ ድልድይ
እግር ማየት ነው ብለናል፣ አሜን በቃን እግር እንይ!
ምንጭ :- ፀጋዬ ገ/መድህን
አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012
እግር እንይ
እግር እንይ
አርቀን ማስተዋል ማለት፤ የኛን ስልጣኔ ድልድይ
እግር ማየት ነው ብለዋል፤ እስቲ እንግዲህ እግር እንይ!
ያባቶችህ ያይን ድንበር፤ ከተረከዝ ሎሚ ሳያልፍ
አንተ ግን ጆቢራው – ዘራፍ
ጠረፍ አይወስንህ ጉብል
ጥሎህ በዘመንህ ዕድል
ዓይንህ ባት አልፎ እንዲዋልል፤
ቴህ ወዲያ ጀግንነት የለ፥ ተዚህ የዘረረ ግዳጅ
ባደባባይ የዱር ገደል፥ ስትናደፍ የእግር አዋጅ
ለሊቱን በየሌት- ‘ግለብ’ ቀኑን ጭምር በጠራራ
ሲነጋ እንደ ጠዋት ጆቢራ
በከተማህ ስታቅራራ በዕድሜህ መንከራተት ስራ፥
ካንዱ ቢሮ ሌላው ቢሮ፥ አቦል በረካውን ብለህ
ያገሩን ወሬ ተንትነህ
ተጨቃጭቀህ ተለፋልፈህ አመሳጥረህ፥ የዚያን ጉዳይ ከዚህ ጉዳይ
ዘጋግነህ በቡና ምገህ፥ አምጥተህ ደክመህ ስትለያይ፥
በዚህ ብቻ ሳታስቀረው፥ ደግሞ አዲሱን የአገር ጠባይ
ከልማድህ የቡና ሱስ ጋር፥ የዘመኑን ሳትለያይ
እስቲ ደግሞ አራዳ ወጥተህ፥ በከተማው አደባባይ
ያንዷን ካንዷ ዳሌና ባት፥ እግሯን ከእግር ጋር አስተያየው
ደርቶልህ ያገር ልጅ ቅልጥም
ዳሌው ባቷ እስኪፈረጥም
እየናረ እስኪያስገመግም
አንተ አድፍጠህ ከኃላዋ፥ በአይንህ ሳግ ስታነፈንፍ
ያቺን ልክፍ ያቺን ንድፍ
እያረክ ስታሾል፣ አንዷ ፈርታህ አንዷ ስታፈጥ
ተጠግታ ባቷ ሲያገምጥ
«ዘራፍ» ቀርቶ ቀልብህም «ውይ!»
እያለ ወኔህ እግር ይይ!
«በሰየጠኑትማ ዘንድ
አንዱን የባላንጣ ዘዴ፣ የባዕዳን ስውር መንገድ
ዘመናይ ጦር መሳሪያ ነው፣ ታዳጊ ሃገር ለማንጋደድ
እምነቱን ለማወናበድ
ያንድን ትውልድ የህልም አቅጣጫ
ወደፊት ሳይሆን ወደታች፣ አመንምኖ ማቀጨጫ!»
ቢልህ ፈጥጦ በግልምጫ
ለህሊናህ ማጋለጫ
ናቀው እርግፍ አድርገህ ተወው፣ ቴህ ብጤው ጋር አትንጫጫ።
ሰልጥነን ንቀን አልፈነው፣ የይሉኝታን መቀጣጫ
የኛ ዓይን የእግር ነው እንጂ፣ በቅቶት ህሊና መግለጫ።
አርቀን ማስተዋል ማለት፣ የኛን ስልጣኔ ድልድይ
እግር ማየት ነው ብለናል፣ አሜን በቃን እግር እንይ!
ምንጭ :- ፀጋዬ ገ/መድህን
አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012