በደቡብ አፍሪካ በጥቁር የውጭ ዜጎች ላይ የደረሰውን ድብደባ እና ግድያ የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ባለፈው ሳምንት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ብቅ ማለት የጀመሩ ሲሆን፣ በዚህም ናይጄሪያውያን በስሜታዊነት አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ናይጄሪያውያን በደቡብ አፍሪካ ከተሞች ውስጥ እየሰሩ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ኢላማዎች መሆን ጀምረዋል። በዚህ ሁኔታ ወጣት ናይጄሪያውያን በአገራቸው በደቡብ አፍሪካ የተያዙ የንግድ ድርጅቶች ላይ አደጋ ማድረስ ጀመሩ።
የናይጄሪያ መንግሥትም አምባሳደሩን ከደቡብ አፍሪካ ያስወጣ ሲሆን በኬፕታውን ከተማ እየተካሄደ ካለው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባም እራሱን ማግለሉን አስታውቋል። አንዳንድ ናይጄሪያውያን ይህን እርምጃ የተቀበሉ ሲሆን ሌሎቹ ግን በቂ እንዳልሆነ ይናገራሉ።
መንግስታቸውም ዜጎቹን ለማዳን ጣልቃ በመግባት እርምጃ እንዲወስድም ጥሪ አቅርበዋል። በውጭ አገር ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎቻቸውን ለመጠበቅ እና ወደ አገራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ ኃያላን አገሮችም በምሳሌነትም ያነሳሉ። ናይጄሪያ ግን ከእነርሱ አይደለችም ።
በእርግጥ ቀደም ሲል አገሪቱ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስጠበቅ ረገድ በተለያዩ ጊዜያት መስራቷን ቀጥላለች። ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ 1960 ዎቹ ናይጄሪያ በሰሃራ በረሃ ውስጥ የኑክሌር መሳሪያዎችን ፈረንሳይ ልሞክር ባለችበት ወቅት አይሆንም ብላ ፊት ለፊት ተጋፍጣለች። የአቡበከር ታፋዋ ባሌዋ መንግሥት ከፓሪስ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በማፍረስ የፈረንሳዩን አምባሳደር ከማባረር አልፎ በፈረንሳይ ዕቃዎች ላይ ሙሉ ማዕቀብ እስከመጣል ደርሶ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ 1970 ዎቹ እና በ 1980 ዎቹ ዓመታት ናይጄሪያ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የአፓርታይድ አገዛዝን በመቃወም ጫና ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ጥረት አድርጋለች። የናይጄሪያ መንግስት በምዕራባዊ ኃይሎች ላይ የኢኮኖሚ እርምጃን እወስዳለው በሚል ያስፈራራ የነበረ ሲሆን በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በማውጣት የአፍሪካን ብሄራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን ብሄራዊ የነፃነት እንቅስቃሴ ደግፏል።
እ.ኤ.አ. በ 1990 ዎቹ አገሪቱ በወታደራዊ ገዥ በነበረው ሳኒ አባቻ መሪነት ዓለም አቀፍ ማዕቀቦችን በመቃወም የሊቢያ መሪ የነበሩትን ሙአመር ጋዳፊን ጉብኝት በደስታ ተቀበለች። እንዲሁም የናይጄሪያ ወታደሮችን በላይቤሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ላይም እንዲዋጉ ልካለች። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በናይጄሪያ እና በሌሎች አፍሪካውያን ላይ ለሚደርሱ ጥቃቶች አብዛኛዎቹ ምላሾች የአቢቻ-ዓይነት ዲፕሎማሲን የሚናፍቁ ናቸው።
ነገር ግን በቅርብ ጊዜ ከአሜሪካ ጋር ያለው ግንኙነት እንዳሳየው ናይጄሪያ እንደዚህ ዓይነት የዲፕሎማሲ ኃይልን መጠቀም አትችልም። ባለፈው የፈረንጆቹ ወር የናይጄሪያ መንግስት ወደ አገሪቱ ለመግባት ቪዛ የሚያመለክቱትን አሜሪካኖች ክፍያ በተመለከተ ያልተጠበቀ ምላሽ መስጠቷ የሚታወስ ነው።
በተጨማሪም ባለፈው ዓመት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአፍሪካ ሀገሮች ላይ በተሰነዘሩት ያልተገባ ንግግር ብዙ መሪዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ቡሀሪ ዝምታን መርጠዋል። በአሁኑ ወቅት ናይጄሪያ እንደ ደቡብ አፍሪካ ባሉ የአካባቢ ኃይሎች ላይ እንኳን ወታደራዊ ይቅርና የስለላ ችሎታ ወይም የዲፕሎማሲ ብቃት እንደሌላት ግልፅ ነው ።
ከደቡብ አፍሪካ ጋር የተደረገው ይህ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቆም ናይጄሪያ እራሷን “የአፍሪካ ግዙፍ” የሚል ስያሜ ትሰጥ የነበረው የውሸት መሆኑን አሳይቷል። ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያ በሀገሯ እና በአጎራባችዋ ለሚኖሩት የውጭ አገራት ሰዎች የምታደርገውን ድጋፍ ትተች ነበር። ነገር ግን አፓርታይድ ከተገረሰሰ ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ በቀጣናው ተሰሚነቷ እየጨመረ መጣ።
ማዕቀብ እና ዓለም አቀፍ ማግለል ከተነሳ በኋላ ደቡብ አፍሪካ በፍጥነት ከአህጉሪቱ በበለፀጉ አገራት እና በውጭ ባለሀብቶች ተመራጭ ሆነች። ደቡብ አፍሪካ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ትልቁ ድርሻ መያዝ ችላለች። እ.ኤ.አ. 2011 በእንግሊዝ መስራችነት የተጀመረው የኢኮኖሚ ፎረም ውስጥ አባል ለመሆን ጊዜ አልወሰደባትም። በዚህም የምዕራባውን የኢኮኖሚ አካሄድ እንድትከተል አድርጓታል።
ደቡብ አፍሪካ ለናይጄሪያ ወሳኝ የንግድ አጋር በመሆኗ ምክንያት ግንኙነታቸው እንዲቋረጥ አትፈልግል። የደቡብ አፍሪካ ባለሀብቶች በናይጄሪያ ውስጥ ትላልቅ ኢንቨስትመንቶች አሏቸው። ለምሳሌ የ ዲ ኤስ ቲቪ ኬብል አገልግሎት፣ ኤም ቲ ኤን ቴሌኮም ፣ ሾፕሬት ሱፐር ማርኬት እና ሌሎችንም ይጠቀሳሉ።
ናይጄሪያ ከ 3 ነጥብ 83 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ዕቃዎች ፣ በተለይም የዘይት እና የቅባት ምርቶች ከደቡብ አፍሪካ ትቀበላለች። በተቃራኒው ከጠቅላላው የደቡብ አፍሪካ የወጪ ንግድ አንድ በመቶ በታች የሆነውን የደቡብ አፍሪካ ምርቶች ማለትም 514 ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ትልካች።
የሁለቱ አገራት ኢኮኖሚያዊ ንፅፅር ገፅታ የናይጄሪያ ድክመትን እንደገና የሚያጎላ ነው። ናይጄሪያ በሸቀጦች ጥገና ኢኮኖሚ ዙሪያ እየተንከባለለች ሲሆን ደቡብ አፍሪካ እጅግ የላቀ የኢንዱስትሪ መዋቅር ያለው ኢኮኖሚ መስርታለች። በሌላ አገላለጽ ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያን ከምትፈልገው በላይ ናይጄሪያ ለኢኮኖሚዋ እድገት ደቡብ አፍሪካን ትፈልጋለች።
የናይጄሪያ የጂኦፖሊቲካዊ ኃይል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየቀነሰ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ ግን አሁንም ድረስ ዋነኛው የቀጣናው ሀያል ሆናለች። ናይጄሪያ በሰሜናዊ ክልሉ ለአራት ዓመታት ከአማፅያን ጋር ሲታገል የቆየ ሲሆን በነበረው ጦርነትም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሂወታቸውን አጥተዋል። በአጎራባች ናይጄሪያ አካባቢ በፈረንሳይ ተናጋሪዎች የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ (ኢካዋስ) አባል አገራት በክልሉ ውስጥ መረጋጋትን እና ጠብ የሚያስከትሉ እና አካባቢውን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ ይገኛሉ።
የናይጄሪያ መንግሥት እምነት የሚጣልበት አጋር በመሆን በምዕራቡ ዓለም በቂ ተጽዕኖ ሊያሳድር አልቻለም። እ.ኤ.አ. 2014 የኦባማ አስተዳደር ለናይጄሪያ ጦር መሳሪያ ሽያጭ እንዳይካሄድ አግዷል። የትራምፕ አስተዳደርም በውሳኔው የቀጠለ ሲሆን የናይጄሪያ ባለሥልጣናት “ተቀባይነት የላቸውም” ተብሎ ተደምድሟል። ምዕራባዊያን የጦር መሳሪያዎችን ለናይጄሪያ ለመሸጥ ፈቃደኛ አለመሆናቸው በጥቁር ገበያው ላይ የጦር መሳሪያ እንድትፈልግ አስገድዷታል። ደቡብ አፍሪካ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በማሻሻጥ ለናይጄሪያ ተደጋጋሚ ውለታ ሰርታለች።
ከዚህ አንጻር የናይጄሪያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ በዜጎቹ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ጥቂት የዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ እና የደቡብ አፍሪካውያንን ከነጭ ገዥዎቻው ነፃ ለማውጣት የወሰደውን ሚና እንደገና ማምጣት አይችልም። ይህን ቢያደርግ ደቡብ አፍሪካ ከድካምነት አቋም አልወጣችም የሚል አንደምታ ይፈጠራል። በእርግጥ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት የሚጋሯቸው ተመሳሳይ ታሪክ ፣ ዘር እና ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ቢኖሯቸውም ለውጭ ፖሊሲ መሳሪያነት ግን መዋል አይችልም።
አንዳንዴ የአፍሪካ አገራት ሀሳብ በጣም ሩቅ የሚያልም ነው። ተተኪ የናይጄሪያ ምሑራን ይህንን አይነት ሀሳብ በብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ነው ይላሉ። የፓን-አፍሪካዊ ራዕይ ናይጄሪያን በጆግራፊያዊ አቀማመጥ ምክንያት ደካማ አድርጓታል። በዚህም እራሷንና ዜጎቿን ወክላ እንዳትከራከር አግዷታል።
ይህ በጣም ኢኮኖሚውን አለ አግባብ ከመጠቀም ጋር የተያያዘ ነው። ናይጄሪያ ኢኮኖሚዋን ከነዳጅ ሽያጭ ማላቀቅ አለባት። በመቀጠልም ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በመቀነስ እራሷን የሚያስችላት ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት ይጠበቅባታል። ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ እያደገ በመጣበት ዘመን እርሳሶችን የማምረት ሀሳብ ለማጉላት አቅም መጨረስ አያስፈልግም። አገሪቱ ደህንነቷ የተጠበቀና በኢንዱስትሪ የበለፀገች ብትሆን ጠንካራ ኃይል እና ዓለም አቀፋዊ ትብብር መልሳ ማግኘት ትችላለች። በዚህም በአከባቢው ላሉት የቀድሞ ጉልበተኞች መልስ መስጠት ትችላለች።
አዲስ ዘመን መስከረም5/2012
መርድ ክፍሉ