የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ቀናት ባደረገው የክትትል ስራ ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ የነበሩ እና ዓመታዊ ገቢያቸው በሚሊየን የሚቆጠር ብር የሆነ ተቋማትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም በተቋማቱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እና ተግባሩ የወንጀል ድርጊትም በመሆኑ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን እና 35 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።
በዚህም መሰረት፦
1. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ/
2. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ አጎና አካባቢ ቅርንጫፍ
3. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ ጎተራ አካባቢ ቅርንጫፍ
4. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ ደንበል ቀርንጫፍ
5. ቬልቬት የውበትና ጽዳት ሃ/የተ/የግ/ማ/
6. ባዝራ ፈረስ ሌዘር ላኪ ሃ/የተ/የግ/ማ/
7. ቢኤምኤች አጠቃላይ ንግድ
8. በላክ ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
9. ድናሪም ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
10. አፍደል ሃ/የተ/የግ/ማ/
11. ደሚር ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
12. ሞጀግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
13. ፋሙ ኤሌክትሪካል ዎርክስ
14. አስተኑ ጄኔራል ትሬዲንግ
15. ዕድላዊት ስቴሽነሪ
16. ጆቢራ ካፌ ሃ/የተ/የግ/ማ/
17. ኪው ቲ ትሬዲንግ
18. አሰብ ሆቴል በክክትሉ የተገኙ ተቋማት ናቸው።