
አሶሳ፡- የአማራና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልሎች በጸጥታና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሚሠሩበትን ሰነድ ዛሬ እንደሚያጸድቁ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ።
የአማራና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ላይ ለመሳተፍ አሶሳ የገቡት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት፤ የአማራ ተወላጅ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝቦች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች መሪው ፓርቲና መንግሥታቱ በጋራ ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎችን በቅርበት ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ ሁለቱ ክልሎች በተለይም በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የበለጠ ተቀራርበው ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ሰነድ ዛሬ እንደሚያጸድቁ ገልጸዋል።
ተበታትነው የነበሩ ህዝቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋ ገጥ ኢ ህአዴግ እ ንደድርጅት እ ያከናወናቸው ያ ሉ ተግባራት እንዳሉ የጠቀሱት አቶ ተመስገን፤ ኢህአዴግ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ጎን ለጎን በህገመ ንግሥቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት ሊሠራ ይገባልም ብለዋል። የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቅድሚያ የሰው አመለካከት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው፤ የአማራ ተወላጅ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝቦች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት የክልሉ ፓርቲና መንግሥት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሰዋል። ከእነዚህ ተግባራትም መካከል በክልሉ የሚኖሩ ህዝቦች ውክልና እንዲኖራቸው ተደርጓል፤ የበለጠ ውክልና እንዲኖራቸው ለማድረግ ደግሞ በቀጣይ የተጠናከረ ሥራ ይሠራል ብለዋል።
በዕለቱ በተደረገው ውይይቱ የጸጥታ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ የሰላምና የውክልና ጥያቄዎች ተነስተዋል። የጋራ መግባቢያ ሰነዱ የተነሱትን ችግሮች ሊፈታና መፍትሔ ሊሰጥ የሚችል መሆኑም ተጠቁሟል።
አዲስ ዘመን ነሀሴ 12/2011
መላኩ ኤሮሴ