ቀለም የለኝ ሽታ
በሰማይ ምሰየም በነጭ የምነጣ
በጥቁር ምጠቁር
በቢጫ ምበጭጭ
በቀይ የምቀላ
ምሞቅ ምቀዘቅዝ በሳት የምፈላ፤
ውሃ ነኝ ውሃ ነኝ
የትም እፈሳለሁ
የትም እደርሳለሁ
ያገኘሁትን ቅርጽ መስዬ እለቃለሁ
ውሃ ነኝ አውቃለሁ።
የሚያቁረኝ የለ ገድቦ ሚያስቆመኝ
አቅም ጉልበት ኖሮት ይዞ የሚያስቀረኝ
ደራሼን ሚረታ ወጀቤን ሚቋቋም
ፍጥረት ካለ አላውቅም።
ብቻ ግን ውሃ ነኝ
በፈለኩት ምድር ምፈነጭ ምጋልብ
መርከብ የማናጋ ጀልባ የማሰጥም
ውስጤ ፍጥረት ያለ ትንሽም ትልቅም
ካሳ ጋር ነው ምኖር ይህንን አልክድም።
ንፁህ አዲስ
2015 ዓ.ም
አዲስ ዘመን ዓርብ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም