ትራምፕ ከፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ. ኬኔዲ ግድያ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይፋ አደረጉ

ትራምፕ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ. ኬኔዲ ግድያ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይፋ አደረጉ። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ1963ቱ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ.ኬኔዲ (ጄኤፍኬ) ግድያ ጋር የተያያዙ ሰነዶች ከትናንት በስቲያ በመልቀቅ በታሪክ በተፈጸመው አስደንጋጭ ክስተት ላይ ግልጽነት እንዲኖር በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገቡትን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚፈልጉ አሳይተዋል።

በብሔራዊ ቤተመዘክር ድረ ገጽ የወጡት የመጀመሪያዎቹ የኤሌክትሪክ ቅጅዎችና ሌሎች 80ሺህ ኮፒዎች በፍትህ ዲፓርትመንት የሕግ ባለሙያዎች ከተገመገሙ በኋላ ይታተማሉ ተብሏል። ሚስጥራዊ ሰነዶችን ጭምር የያዙት ዲጂታል ሰነዶች ወደ ኑክሌር ጦርነት ሊያመራ ጫፍ ደርሶ ከነበረው የኩባ የሚሳይል ቀውስ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በአሜሪካና በያኔዋ ሶቭየት ህብረት በአሁኗ ሩሲያ ግንኙነት ዙሪያ ፍርሃት ነግሶ እንደነበር ያሳያሉ።

አብዛኞቹ ሰነዶች የሚያወሱት ገዳዩ ሀርቬይ ኦስዋልድ በሶቭየት ያሳለፈውን ጊዜና እኤአ በ1963 በዳላስ ኬኔዲ እስከተገደሉበት ድረስ ባሉ ወራት ያደረገውን እንቅስቃሴ ለማወቅ ያደረጉትን ምርመራ ነው። በሰነዱ ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ምርመራ በብዙዎች ዘንድ ይሆናል ተብሎ ከሚታመነው ያፈነገጠ አይደለም። የትራምፕ የጤና እና የሰው አገልግሎት ጸሃፊ ሮበርት ኤፍ.ኬኔዲ ጄአር. በአጎቱ ግድያ ላይ የአሜሪካ ሴንትራል ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ(ሲአይኤ) እጁ አለበት ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።

የጄኤፍኬ የልጅ ልጅ የሆነችው ጃክ ስችሎስበርግ በኤክስ ገጹ የትራምፕ አስተዳደር መረጃውን ሊለቅ መሆኑን ለማንኛውም የኬኔዲ ቤተሰብ አላወቀውም ብሏል። በጄኤፍ ኬ ላይ መጽሀፍ የጻፉት የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ፍሬድሪክ ሎግቫል የሰነዶቹ መለቀቅ የጎደሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ሊረዳ እንደሚችል ገልጸዋል።

“ምንም ሳይቀናነሱ ሙሉ ሰነዶችን ማግኘት አስፈላጊ ነው። ነገርግን ስለግድያው ከዚህ በፊት ያወቅነውን የሚያስቀይር የተለየ ውጤት ይገኛል ብዬ አላስብም” አንድ ሚስጥር የሚል ሰነድ የተጻፈበት ሰነድ የዋረን ኮሚሽን ሲአይኤና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሶቭየትዋ ሴትና ግድያ ፈጽሟል በተባለው አሜሪካዊ ኦስዋልድ መካከል ስላለው የጋብቻ ግንኙነት የሰጡት መረጃ ስላለው ልዩነት የሲአይኤ ሠራተኛን ሊ ዊግሬን ጠይቆ በእጅ ጽሁፍ ያሰፈረበት ነው። በርካታ አሜሪካውያን ጄኤፍኬ በሴራ ተገድለዋል ብለው ያምናሉ።

ትራምፕ ባለፈው ጥር ወደ ኃይትሀውስ ከገቡ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ነበር ሰነዶቹ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ያስተላለፉት። ይህን ተከትሎ የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ ከዳላሱ የኬኔዲ ግድያ ጋር የተያያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰነጆች ለመፈለግ ተገደዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ የጥቁር መብት ተሟጋች የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄአር. ግድያ የተመለከቱ ሰነዶችንም ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ሲል የዘገበው አል ዐይን ነው።

አዲስ ዘመን መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You