
አዲስ አበባ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ ለመጡ እንግዶች እንኳን ወደ ቤታችሁ በሰላም መጣችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ሁሉ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣችሁ ትላለች ብለዋል።
በጉባኤው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ተሳታፊዎች ቆይታቸውን አራዝመው የኢትዮጵያን ውብ ታሪክ፣ ልዩ ልዩ ባህሎች እና አስደናቂ መልክዓ ምድር እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
ተሳታፊዎች ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት መሆኗን የሚያረጋግጡ የዳበሩ ታሪኮቿን፣ ልዩ ልዩ ባህሎቿን እና አስደናቂ መልክዓ ምድሮቿን እንዲመለከቱ አበረታታለሁ ሲሉም ገልጸዋል።
እንግዶች ከጉባኤው ባሻገር በቆይታቸው ከጥንታዊ ቅርስ ስፍራዎች እስከ ደማቅ ባህሎችና ወደር የለሽ የተፈጥሮ ውበትን መመልከት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም