በጨረታ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው ሙዝ

በአሜሪካዋ ኒውዮርክ ግድግዳ ላይ በፕላስተር የተለጠፈ ሙዝ በጨረታ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር መሸጡ መነጋገሪያ ሆኗል። ግድግዳ ላይ በፕላስተር የተጣበቀው ሙዝ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል። ቻይናዊው የክሪፕቶከረንሲ ባለፀጋ ጀስቲን ሰን ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያፈሰሰበትን ሙዝ እንደሚበላው ተናግሯል።

ማውሪዚዮ ካቴላን የተባለ ጣሊያናዊ ለብዙዎች ስሜት የማይሰጥ የሚመስል ነገር ግን “ኮሜዲያን” የሚል ስያሜ የሰጠው የጥበብ ሥራ ለጨረታ ቀርቧል። የጥበብ ሥራው ምንም የተለየ ነገር የለውም፤ አንድ ሙዝ ግድግዳ ላይ በፕላስተር የተጣበቀበት ነው።

ጣሊያናዊው የቪዡዋል አርቲስት ያቀረበው “የጥበብ ሥራ” ግን ከተጠበቀው በላይ በአራት እጥፍ የላቀ ዋጋ ማውጣቱን ተገልጿል

ማውሪዚዮ ካቴላን የተባለው ጣሊያናዊ የጥበብ ሰው በፕላስተር ከግድግዳ ያጣበቀው ሙዝ ኒውዮርክ ውስጥ በተካሄደ ጨረታ በ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል።

ይህ ዋጋ ግድግዳ ላይ ለተጣበቀው ሙዝ መጀመሪያ ከተሰጠው ግምት በአራት እጥፍ ከፍ የሚል ነው።

አጫራቹ ድርጅት ይፋ እንዳደረገው በክሪፕቶከረንሲ ንግድ የበለፀገው ቻይናዊ ጀስቲን

ሱን የተባለ ግለሰብ ሌሎች ተጫራቾችን አሸንፎ “ኮሜዲያን” የተባለውን የጥበብ ሥራ ረቡዕ ዕለት ሸምቶታል።

ጨረታውን ያሸነፈው ሱን “በሚቀጥሉት ቀናት እኔው ራሴው ሙዙን በመብላት የዚህ ልዩ የጥበብ ማዕድ ተቋዳሽ እሆናለሁ” ማለቱ ተሰምቷል።

በፕላስተር የተጣበቀው ሙዝ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ የተሸጠ ፍራፍሬ ሆኗል። ኒውዮርክ ታይምስ እንደዘገበው በጨረታው የተሸጠው ሙዝ ከጨረታው ቀን በፊት በ0 ነጥብ 35 ዶላር ከገበያ የተገዛ ነው።

“ኮሜዲያን” የተባለው የጥበበ ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ያለው እአአ 2019 ነበር። በወቅቱ ግድግዳ ላይ የተጣበቀው ሙዝ መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ጥበብ ምንድናት? የሚል የበይነ መረብ ክርክር አስነስቶ እንደነበር አይዘነጋም።

ከግድግዳ የተጣበቀው ሙዝ በመላው ዓለም ተዘዋውሮ ለዕይታ ቀርቧል። የተጣበቀው ሙዝ መበስበስ ሲጀምር እንዴት መቀየር እንዳለበት የሚያትት መመሪያም አብሮት ይዞራል።

በፕላስተር የተጣበቀው ሙዝ ከአንድም ሁለት ጊዜ ተበልቷል።

በ2023 ይህ ሙዝ በሴዑል የጥበብ ሙዚየም ተሰቅሎ ሳለ ደቡብ ኮሪያዊው የጥበብ ተማሪ ከግድግዳ አውርዶ እንደበላው ይታወሳል።

ሙዚየሙ በተባለው ፈንታ ሌላ ሙዝ ገዝቶ መቀየሩን የኮሪያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ከአራት

ዓመታት በኋላ ግድግዳ ላይ በፕላስተር የተጣበቀው ሙዝ በአሜሪካዋ የባሕር ዳርቻ ከተማ ማያሚ በ120 ሺህ ዶላር ተሽጧል።

ይህ ከሆነ በኋላ አንድ የጥበብ ሰው ነኝ የሚል ግለሰብ ሙዙን ከግድግዳው ላይ ማንሳቱ ቁጣ ቀስቅሶ

ነበር። ነገር ግን ሙዙ በጥንቃቄ ቦታው ላይ እንዲተካ ተደርጓል።

6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር አውጥቶ በፕላስተር ከግድግዳ የተጣበቀውን ሙዝ የገዛው የክሪፕቶከረንሲ ቱጃር ነው ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ህዳር 14/2017 ዓ.ም

Recommended For You