ኮፕ29 የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ በአዘርቤጃን ዋና ከተማ ባኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በስብሰባው ላይ የተገኙት የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ዶክተር ሱልጣን አል ጃቢር በአሁኑ ወቅት ግጭቶች እና ክፍፍሎች መኖራቸውን ጠቅሰው በጉዳዩ ላይ ትብብር እና ውይይት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ዶክተር አል ጃቢር በኮፕ28 ስብሰባ ታሪካዊ የተባለው “የዩኤኢ ስምምነት” እንዲደረስ አድርገዋል ያሏቸውን የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት እና ስብሰባውን ያስፈጸሙትን ሠራተኞች አመስግነዋል።
ዶክተር ጃቢር አክለው እንደገለጹት ኮፕ 29 የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ወደተግባር የሚቀየርበት ነው።
በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ መሻሻሎችን ለማምጣት ፋይናንስ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ጃቢር ሁሉይም የመንግሥት እና የግል የፋይንስ ምንጮች እንዲለግሱ ማበረታት ይገባል ብለዋል።
ዶክተር ጃቢር ዓለም የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት አንድ የጋራ ግብ እንዲያስቀምጥ እንደሚፈልጉም ገልጸዋል።
ባለፈው ስብሰባ “በዱባይ ታሪካዊ የሚባል ስምምነት ላይ ደርሰናል። ነገር ግን ታሪክ የሚፈርደን በሠራነው ተጨባጭ ሥራ ነው” ብለዋል ዶክተር ጃቢር።
የተባበሩት ኤምሬትስ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች የተሳተፉበትን የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በስኬት ማስተናገዷ የሚታወስ ነው።
በጋዜጣው ሪፓርተር
አዲስ ዘመን ህዳር 3/2017 ዓ.ም