ሥልጠናው የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የሃሳብና የተግባር አንድነት ለመገንባት የሚያስችል ነው

አዲስ አበባ፡- ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ሥልጠና በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የሃሳብና የተግባር አንድነትን ለመገንባት የሚያስችል ነው ሲሉ አፈጉባኤ ታገስ ጫፎ ተናገሩ፡፡

ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ‹‹የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት ›› በሚል መሪ ሃሳብ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጣቸው ነው፡፡ ሥልጠናውም ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ተጠቅሷል፡፡

የሥልጠናው መርሃ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፤ ሥልጠናው በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሃሳብና የተግባር አንድነትን ለመገንባት የሚያስችል ነው፡፡

ሥልጠናው ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ሁለተናዊ ስኬት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠልና በእድገት ጉዞ የሚገጥሙ ፈተናዎች ለመፍታት የሃሳብና የተግባር አንድነትን ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል

የአቅም ግንባታ ሥልጠናው በሀገሪቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል፤ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችሉ ግብዓቶችን የያዘና ተጨማሪ ሃሳቦች ከሠልጣኞች ለመጨመር እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

ሥልጠናው በአንድ የአስተሳስብ መንፈስ በመሥራት የተገኘውን እድገት ለማስቀጠልና በሁሉም ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ የሚረዳ መሆኑን ጠቅመው፤ መወያየት፣ መመካከር፣ መነጋገርና መሠልጠን፣ የተወያዩበትን ሃሳብ ተግባራዊ ማድረግ የሀገርን እድገት ለማስቀጠል ይረዳል ብለዋል፡፡

የአቅም ግንባታ ሥልጠናው የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላትን ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን አውቀው የሀገሪቱን ስኬት እንዲያስቀጥሉ የሚያግዝ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋየ በልጅጌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የአቅም ግንባታ ሥልጠናው ኢትዮጵያ የደረሰችበትን ሁለተናዊ ስኬት ለማስቀጠልና በስኬቶቿ የሚገጥማትን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚያስችል አቅም ለመገንባት፤ የሃሳብና የተግባር አንድነት ለማምጣት የሚረዳ ነው፡፡

የሕዝብ ተወካይና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን እንዲያውቁ፤ የሀገርን ስኬት እንዲያስቀጥሉ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

የአመራርነት አቅም የመገንባት ሥራ ላለፉት አራት ዓመታት እየተሠራበት እንደሆነ አስታውሰው፤ አሁንም የሚሰጠው ሥልጠና ተጨማሪ አቅምን ለማጎልበት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ሥልጠናው የሀገሪቱ ስኬቶች ምንድን ናቸው? ተግዳሮቶችስ? የሚለውን በመለየት ስኬቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ ፈተናዎችንም ፈትቶና ተሻግሮ የታሰበውን ብልፅግና እውን ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ አለው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የሃሳብና የተግባር አንድነትን ለማጠናከር፤ በጋራ ግብ በጋራ በመቆም ስኬትን ለማስመዝገብ ሥልጠናው ትልቅ ጠቀሜታ አለው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ሥልጠናው የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት፤ ትርክት ከታሪካዊ ስብራት ለሀገር እምርታ፤ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት፤ የውጭ ግንኙነት፣ የደህንነትና ፀጥታ፣ ተቋማዊ፣ ሥነ-ምግባር፣ የአመራር እምርታዎችን የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የያዘ መሆኑን ገልጸው፤ ሠልጣኞች ሥልጠናውን ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉና ስኬቶችን ለማስቀጠል ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል ተጨማሪ ግብዓት እንዲሰጡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ታደሠ ብናልፈው

አዲስ ዘመን ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You