የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከል የተገኘው ድጋፍ ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ

እየሄደበት ከሚገኘው የስርጭት መጠን አንጻር ይህ እጅግ ዝቅተኛ ነው” ብለዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጄን ካሴያ በበኩላቸው አንድ ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶችን በድጋፍ መልክ ለማግኘት የአፍሪካ ሲዲሲ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ስፔን ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል ሲሆኑ ሌሎች ክትባት አምራቾች እና ሀገራት ተጨማሪ ድጋፎችን እንዲያደርጉ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡ የአውሮፓ ኅብረትና የኔዘርላንዱ የክትባት አምራች ባቫሪያን ኖርዲክ ለአፍሪካ የክትባት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

በጦርነት እየታመሰች ከምትገኘው ከዴሞክራሲያዊት ኮንጎ ተነስቶ ሌሎች የአሕጉሪቷን ሀገራት እያዳረሰ የሚገኝው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዓለም ጤና ድርጅት ማኅበረሰባዊ የጤና ስጋት ስለመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ ታውጇል፡፡

አፍሪካ በአሁኑ ወቅት ስርጭቱ በሚገኝበት ደረጃ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት እንደሚያስፈልጋት ያስነበበው ሮይተርስ የክትባቱ ዋጋ ውድነት ፈተና መደቀኑን ዘግቧል፡፡ የክትባቱ አምራቾች በአሁኑ ወቅት የአንድ ዶዝ ክትባት ዋጋ 100 ዶላር ተምነው በመሸጥ ላይ ናቸው፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን  ነሐሴ 24/ 2016 ዓ.ም

Recommended For You