በ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ የሚቀርበው የዓለማችን ውድና ቅንጡ መኪና

አዲሱ የሬድቡል ቅንጡ መኪና በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል፡፡ 3 ዓመታት 15 “RB17 ሃይፐርካር” መኪናዎች ብቻ የሚመረቱ ሲሆን ሁሉም ከወዲሁ ተሽጠዋል፡፡

ሬድቡል “RB17 ሃይፐርካር” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የዓለማችን ውድ፣ ቅንጡና ፈጣን መኪና ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።

የፎርሙላ ዋን የመኪና ውድድር የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ሬድቡል ከ7.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ የተቆረጠለት “RB17 ሃይፐርካር” መኪናውን ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው “ጉድውዱ የፍጥነት ፌስቲቫል” ላይ ይፋ ማድረጉም ተነግሯል።

አዲሱ የሬድቡል “RB17 ሃይፐርካር” መኪና በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።

የፈረንሳዩ ቡጋቲ ኩባንያ በሰዓት 445 ኪሎ ሜትር የምትጓዝ መኪና ሠራ “RB17 ሃይፐርካር” መኪና ውስን ምርት ብቻ ተመርቶ ለገበያ እንደሚቀርብ ያስታወቀው ሬድቡል፤ በቀጣይ 3 ዓመትት ውስጥ ለመደበኛ የመንገድ ላይ ጉዞ ብቻ የሚያገለግሉ 15 መኪናዎች ይመረታሉ ብሏል።

በቀጣይ 3 ዓመታት ውስጥ ለማምረት እቅድ የተያዘባቸው 15 “RB17 ሃይፐርካር” መኪናዎች ከወዲሁ እያንዳንዳቸው በ7.77 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተሽጠው ማለቃቸውንም ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

አዲሱ የሬድ ቡል መኪና ከ900 ኪሎ ግራም በታች ክብደት የሚኖረው ሲሆን፤ 1000 የፈረስ ጉብልት ያለው “V10 ኮስዎርዝ” ሞተር ከተጨማሪ ከ200 የፈረስ ጉልበት የኤሌክትሪክ ሞተር የሚገጠምለት ነው ተብሏል።

በሁሉም “RB17 ሃይፐርካር” መኪና ላይ የሬድ ቡል የላቀ ቴክኖሎጂዎች በጠቅላላው የግንባታ ሂደት እንደሚተገበሩም ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

በዓለማችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት በጣም ውድ የሆኑ ፈጣን እና ቅንጡ መኪናዎች ይፋ የሚደረጉ ሲሆን፤ የፈረንሳዩ ቡጋቲ በቅርቡ በሰዓት 445 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ መኪና መሥራቱ ይታወሳል።

አዲሱ የቡጋቲ መኪና 1 ሺህ 800 የፈረስ ጉልበት ያለው ሲሆን በሰዓትም 445 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል በወቅቱ መገለጹ አይዘነጋም።

አዲሱ የቡጋቲ መኪና 4 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ የወጣለት ሲሆን የተወሰኑ የሙከራ ሥራዎች ከተደረጉ በኋላ 250 ምርቶች ለገበያ ይቀርባሉ ተብሏል።

የቡጋ ተሽከርካሪ ሦስት የኤሌክትሪክ ሞተር እንዲሁም 1 ሺህ ፈረስ ጉልበት ያለው አንድ የነዳጅ ሞተርም እንዳለው ተገልጿል።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You