የዓለም ትልቁ ስፖርታዊ የውድድር መድረክ ኦሊምፒክን ከሚያደምቁት መካከል አፍሪካውያን ሀገራትይጠቀሳሉ። ከኋላ ቀርነትና ድህነት ጋር የሚያያዘው
ሁለተኛው አህጉር፤ የወጣቶች ቁጥር በእጅጉ ከፍተኛከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከስፖርት ጋር ያለው ቁርኝት ከፍተኛየሚችል ነው። ነገር ግን የስፖርታዊ ውድድሮችቁንጮ ከሆነው ኦሊምፒክየሚመዘዘው የአፍሪካውያንታሪክ የዘገየ ሊባል የሚችል ነው። በዚህና ከተሳታፊሀገራት የተፎካካሪነት አቅም ጋር ተያይዞ ዝቅተኛ ሊባልየሚችል የሜዳሊያ ቁጥር በሰንጠረዡ ተመዝግቦ ይገኛል።
በእርግጥ የአፍሪካና ኦሊምፒክ ቁርኝት ሲነሳጎልቶ የሚታወሰው ጉዳይ የተወዳዳሪነትና የአሸናፊነትታሪክ ሳይሆን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ናቸው። በዛሬውየስፖርት ማህደር እትምም የአፍሪካውያን የኦሊምፒክተሳትፎ፣ የተቃውሞ እና በዘመናዊው ዓለም ትልቅ ስፍራየሚሰጠውን የኦሊምፒክ አዘጋጅነት እንቅስቃሴ በወፍበረር እንዳስሳለን።
በኦሊምፒክ የመጀመሪያው የአፍሪካውያን ተሳትፎበሚል በታሪክ የተሰነደው እአአ 1904 ነው። ሴንትሉዊስ የዘመናዊው ኦሊምፒክ 3ኛ አስተናጋጅ ከተማ ስትሆን፤ በውድድሩ ላይ ሁለት ደቡብ አፍሪካውያንየማራቶን ተካፋይ ነበሩ። እንደሌሎች ስፖርተኞችየታቀደበትና ዝግጅት ባልተደረገበት በዚህ ተሳትፎ፤የቀድሞ ወታደሮች የነበሩና እንግሊዝ ውስጥም በእስርየቆዩት ሌን ቱናያኔ እና ጃን ማሺያኒ እንዲሮጡ በመደረጉአፍሪካ እና ኦሊምፒክቀዳሚዎቹ አፍሪካውያን በሚል ተሰይመዋል።
በወቅቱበአውሮፓውያን ቀኝ ገዢዎች ይተዳደሩ የነበሩ ሀገራትለዚህ ባይታደሉም ደቡብ አፍሪካ ግን በአፓርታይድሰበብ እአአ ከ1964 – 1988 እስክትታገድ ድረስ በመድረኩ
የመሳተፍ እድል ነበራት።እአአ 1904 እስከ 2020ው የቶኪዮ ኦሊምፒክድረስም አፍሪካውያን ሀገራት 126 ወርቅ፣ 146 ብርእና 168 ነሃስ በጥቅሉ 440 ሜዳሊያዎች በመድረኩተመዝግበዋል።
ይህም ከሌሎች ሀገራት አንጻር ዝቅተኛሊባል የሚችል አህጉር አቀፍ ተሳትፎ ነው። በረጅምርቀት አትሌቲክስ ተጽእኖ ፈጣሪዎቹ ኬንያ፣ ኢትዮጵያእና ደቡብ አፍሪካ በውጤታማነት ታሪክ ቀዳሚ ሲሆኑ፤ከአህጉሪቷ አልፎ እንደ አጠቃላይ የኦሊምፒክ ታሪክተዓምር በማሳየት ሁሌም ስማቸው የሚነሱ ወርቃማስፖርተኞች መገኘታቸው ግን ሊዘነጋ አይገባም።
አስቆጪው የአነስተኛ ሜዳሊያዎች ቁጥር ከዘገየውተሳትፎ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም፣ አፍሪካውያን ሀገራትየሚሳተፉባቸው የስፖርት ቁጥሮች ማነስ፣ ዘመኑን የዋጀ
ዘመናዊ ዝግጅት ማድረግ እንዲሁም እንደ ገንዘብ እጥረትያሉ ችግሮችም ለተፎካካሪነትና ውጤታማነት ፈተናሆነዋል።
ቀዳሚውን የደቡብ አፍሪካ ተሳትፎ ተከትሎ ሌሎችአፍሪካውያን ሀገራቅ ቀስ በቀስ መድረኩን ቢቀላቀሉምአብዛኛው ታሪካቸው ግን ዛሬም ድረስ ከሚወሳውተቃውሞ ጋር የሚያያዝ ነው። የአፓርታይዱን እግድጨምሮ ሌሎች ኦሊምፒኮች ላይ ከፖለቲካ ጋር በተያያዙምክንያቶች ሀገራት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ኢትዮጵያን ጨምሮ የአህጉሪቱ ሀገራት ደቡብ
አፍሪካውያን ላይ የሚፈጸመውን በደል ተቃውመውራሳቸውን ያገለሉበት የሞንትሪያል ኦሊምፒክ ከእነዚህመካከል አንዱ ነው።
በዚህ ረገድ ሌላው ዓለም ዝምታን ሲመርጥዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ግን በስታዲየሞችናጂምናዚየሞች በሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች ብቻሳይወሰን ጸረ ፋሺስታዊ አሠራርን በግልጽ በመቃወምአጋርነቱን በማስመስከሩ ሊመሰገን ይገባዋል። የሰውልጆችን ሰላም እና እኩልነት ማጎልበት እንዲሁምሰብዓዊነት የኦሊምፒክ አስኳል ሃሳብ እንደመሆኑኮሚቴው ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት የአፓርታይድናየኦሊምፒክዝም ኮሚሽን አቋቁሞ የደቡብ አፍሪካውያንጭቆና እንዲቆም ያለመታከት መታገሉን ታሪክ ያወሳል።
በሞስኮ፣ ሎስአንጀለስ እና ሴኡል ኦሊምፒኮች ደግሞበዓለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለምን በመደገፍናበመቃወም ሀገራት ጎራ ለይተው ተሳትፎ ያደርጉ ነበር።በዚህ ሂደትም ኢትዮጵያ እና ሌሎች አፍሪካውያን ሀገራትተሳታፊ ነበሩ።በየአራት ዓመቱ የዓለምን ሕዝብ ቀልብ በመያዝተወዳዳሪ የማይገኝለትን ኦሊምፒክ ማዘጋጀት ክብርን
ያጎናጽፋል። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊነባራዊ ሁኔታ በግልጽ በሚንጸባረቅበት በዚህ የውድድርመድረክ ሀገራት ራሳቸውን ከማስተዋወቅ አልፈውታላቅ ብሄራዊ ስሜትን ይገነቡበታል። ከፍተኛ ወጪአውጥተው እጥፉን የሚያተርፉበት እንደመሆኑ አዘጋጅሆኖ ለመመረጥ ከፍተኛ ፉክክርም ይደረግበታል። ከዚህአንጻር አፍሪካውያን ሀገራት ለአዘጋጅነት የሚያቀርቡትጥያቄ አነስተኛ የሚባል ነው። በእርግጥ የዘመናዊውንኦሊምፒክ መጀመር ተከትሎ እንደ ግብጽ እና ደቡብአፍሪካ ያሉ ሀገራት ፍላጎት አሳይተዋል፤ ነገር ግንበወቅቱ የነበሩ አምባገነን የኮሚቴው መሪዎች ፈቃደኞችአልነበሩም። አሁን ላይ ግን ደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫንበብቃት አዘጋጅታ የስፖርት ቤተሰቡን እንዳስደመመችሁሉ ኦሊምፒክን የማስተናገድ ደረጃ ላይ ደርሰናል ያሉየሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ፍላጎታቸውንበማንጸባረቅ ላይ ይገኛሉ።
ብርሃን ፈይሳ
አዲስ ዘመን እሁድ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም