ነገረ ቲክቶክ

(የመጨረሻ ክፍል)

በክፍል አንድ መጣጥፌ ቲክቶክ በምዕራባውያን የማኅበራዊ ሚዲያና ፖለቲካ ላይ ስላስነሳው አቧራ እና ስለተደቀነበት የሕልውና አደጋ አነሳሳሁ። አሁን ደግሞ እግረ መንገድ ቲክቶክ በልጆች ስነ ልቦና እና አስተዳደግ ላይ ስለደቀነው አሳሳቢ አደጋ ከዚህ ቀደም ወላጆችን ለማሳሰብ ያደረግሁት ጥረት ፍሬያማ ሆኖ ስለ አላገኘሁት ዳግም ልመለስበት ወደድሁ።

በእኔ ትውልድ ወላጆቻችን በሰፈሩ የሚታወቅ ባለጌ ልጅ ካለ ከእሱ ጋር እንዳንገናኝ እንዳንውል ከማስጠንቀቂያ ጋር እንመከርና እንዘከር ነበር። አንድ ቀን አብረን ከታየን ማታ ቁንጥጫና ኩርኩም ይጠብቀናል። ሁለተኛ ከዚህ አሳዳጊ ከበደለው ጋር አይህና፤ ሁለተኛ እየተባልን ጭናችን አጋም እስኪመስል ይመዘለግ ነበር ። አጥፍተን ከተገኘን ደግሞ ከዚያ ስድ ጋር እየዋልህ ድሮስ እንባላለን ።

ከአህያ ጋር የዋለች ላም ፈ* ተምራ ትመጣለች እየተባለ ይተረትብናል። በሰፈሩ በትምህርቱ ጎበዝና ለወላጆች የሚታዘዝ ልጅ ካለ ደግሞ የእሱን ሰብዕናና ባሕሪ እንድንላበስ አጋጣሚ እየተፈለገ ከእነ ወላጆቹ ስሙ ይነሳል። ወላጆቻችን ሥነ ልቦናን አስኳላ ገብተው ባያጠኑም የአቻ ለአቻ ግፊት ወይም ተፅዕኖ በአዎንታም ሆነ በአሉታ በልጆች ሰብዕናና አስተዳደግ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ አበክረውና ጠንቅቀው ያውቃሉ ።

ያደግንባት ከተማ ጠባብ ስለነበረች ስለትምህርት ቤት አዋዋላችንም ከአስተማሪዎቻችን በቀላሉ ወሬ ማግኘት ስለሚችሉ ያም ያህል አይቸገሩም ነበር። አሁን አሁን ግን ከተሞች በመስፋታቸውና የተማሪዎች ቁጥሩም የዛን ያህል በመጨመሩ የወላጅን ክትትል ከባድ አድርጎታል። እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ደግሞ ይብስ ያዳግታል። በእንቅርት ላይ እንዲሉ በአናቱ ላይ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጨምሮበት ልጆችን በሥነ ምግባር ኮትኩቶ ማሳደግ ፈታኝ እየሆነ ነው ።

የሚማሩበትን ትምህርት ቤትና ጓደኞቻቸውን መምረጥ ብንችልም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ ወይም የቨርቹዋል ዓለሙን ጓደኞቻቸውን ግን መምረጥም ሆነ መከታተል ይቸግራለን። አሁን አሁን ልጆች ከእኩዮቻቸው ጋር ጭቃ አቡክቶ ቦርቆ ከመጫወት ይልቅ ቴሌቪዥንና እጅ ስልክ ላይ መጣድን ይመርጣሉ። እኔ በምኖርበት የጋራ መኖሪያ ቤት ቅዳሜና እሁድ ሆነ በአዘቦት ከትምህርት ቤት ሲመለሱ በእረፍታቸው ውጭ ወጥተው ሲጫወቱ አላይም ።

ድንገት መብራት ሲጠፋ ግን ቴሌቪዥን ስለሚቋረጥ፣ ብሮድ ባንዱም ስለማይሠራ ከየቤታቸው መውጣትና ሰፈሩን መቀወጥ ይጀምራሉ ። በዚህ መሐል መብራት ከመጣ ሰፈሩን በጩኸትና በፉጨት ያደበላልቁና ወደየቤታቸው ይመለሱና ሰፈሩ መልሶ ጭር ይላል። ሩጦና ዘሎ ያላደግ ሕጻን አካላዊም አእዕምሯዊ ብቃቱ ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለአፍታ አስቡት።

የእጅ ስልክ ምርኮኛ እየሆኑ ነው። ዘመድ ቤት ሲመጣም ሆነ እናንተ ዘመድ ጥያቄ ስትሔዱ ሁለት ዓመት ያልሞላቸው ሕጻናት ሳይቀሩ ጠጋ ብለው የእጅ ስልክን ተቀብለው ከአንድ አንድ ጌም ፍለጋ ነው የሚገቡት። ሁለት ዓመት ያልሞላት የእህቴ ልጅ ቤት ስትመጣ ስልኬን ለመቀበል ነው የምትሽቀዳደመው። መጣጥፎችን በእጅ ስልኬ ስለምጽፍና ብዙ ዶክመንት ስለሚይዝ ታጠፋብኛለች ብዬ ስለምፈራ ስለማልሰጣት ሁል ጊዜ በመጣች ቁጥር ጸብ ነው። ስታለቅስ ሌላ ስልክ ሰጥተው ያባብሏታል ።

ልጅ ሲያለቅስ በከረሜላ በቼኮላት ሳይሆን የሚደለለው በስልክ ሆኗል። ይህ የስልክ ፍቅር አብሮ ያድግና ከፍ ሲሉ ስልክ ካልተገዛለን ከወላጅ ጋር ጸብ ነው። መቼም ወላጅ የሚኖረው ለልጆቹ ነውና እነሱን ለማስደሰት ቢያጣም ተበድሮና ተለቅቶ ገዝቶ መስጠቱ አይቀርም ። ስልኩን ገዝቶ ይስጥ እንጂ አጠቃቀሙ ላይ ቁጥጥር ስለማያደርግ ልጆቹ በጌምና እንደ ቲክቶክ ባሉ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱስ ይጠመዳሉ። ለከፉ ሌሎች አደጋዎችም ሊጋለጡ ይችላሉ። ሱሱ ያድግና ለተለያዩ የአዕምሮ ሕመሞች ይዳርጋቸዋል ።

ለጭንቀት፣ ለድብርት፣ ራስን ለመጥላትና ራስን ለማጥፋት ይጋለጣሉ። ዛሬ ልጅን አሳድጎ ለወግ ለማዕረግ ማብቃት ፈታኝ እየሆነ ነው። ልጆቻችን ከእጃችን እያመለጡን ነው። ከእድሜያቸው ቀድመው ለተለያዩ እኩይ ተግባራት እየተጋለጡ ነው። ችግሩ ዓለማቀፋዊ ነው። መጠኑ ይለያይ እንጂ ምዕራባውያን በዚህ እየተፈተኑ ነው። ቢቸግራቸው ማኅበራዊ ሚዲያዎች የእድሜ ገደብና የይዘት ክልከላ እንዲያደርጉ ግፊት ቢያደርጉም የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ ስላልሆነ ከእነ አካቴው ይታገዱ እስከማለት ደርሰዋል ።

አሜሪካ ውስጥ ከ2024 ምርጫ፣ ከእስራኤልና ሐማስ ጦርነት፣ ከራሽያና ዩክሬን ጦርነት በመለጠቅ ቲክቶክ ዐቢይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ነው። ለዚህ ነው ብዙኃን መገናኛዎች የዜናዎቻቸው ማሟሻ አድርገውት የባጁት። ፋሪድ ዘካሪያ በ”ዋሽንግተን ፓስት” ጋዜጣ ፣ “Why banning TikTok won’t do any good” ወይም “ቲክቶክን ማገድ ለምን ፋይዳ ቢስ ይሆናል” በሚል ርዕስ በአንድ ወቅት ባስነበበን የግል አስተያየቱ፤ ሰለ ቲክቶክ ባሰብሁ ቁጥር ይበልጥ ያስፈራኛል የሚለው ፋሪድ ዘካሪያ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለተከታታይ ሁለት እሁዶች በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣም ሆነ በCNN/GPS ጽፎ አያውቅም። ባልተለመደና ተከታዮቹን ባስገረመ ሁኔታ ስለ ቲክቶክ ግን ጻፈ ።

ይህ የቻይናው መተግበሪያ አሜሪካንን እንዴት እንዳሳሰባትና እረፍት እንደነሳት ጥሩ ማሳያ ነው። ፋሪድ፣ ባለፈው ሳምንት የቲክቶክን መታገድ ተቃውሜ ሞግቼ ነበር ይለንና። ከተለያዩ ሰዎች ጋር ባደረግሁት ውይይት የተገነዘብሁት ነገር ቢኖር ፤ የአሜሪካውያን ዋና ስጋት ቲክቶክ የቻይናዊ ንብረት መሆኑ ሳይሆን ከየትኛውም ማህበራዊ ሚዲያ በላይ አደገኛ ሱስ አስያዥ መሆኑ ነው ። ይህ ደግሞ ሁላችንን እያሳሰብ ያለጉዳይ ስለሆነ ሳንዘገይ አንድ ነገር ማድረግ አለብን ።

አሜሪካውያን በ2022 ዓም ከሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች በአንደኛ ደረጃነት ቲክቶክን አውርደዋል። ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑ የአሜሪካ ብላቴናዎች ወይም ታዳጊ ልጆች ቲክቶክን ይጠቀማሉ። ከስድስቱ አንዱ ደግሞ በቲክቶክ ሱስ ተለክፈዋል። ከ2018 እስከ 2021 በተደረገ ጥናት የቲክቶክ ተጠቃሚዎች አኃዝ በ67 በመቶ ሲተኮስ፤ የፌስቡክና የዩቲውብ ተጠቃሚዎች በ10 በመቶ ብቻ ነው ከፍ ማለት የቻለው። ቲክቶክ ምን የተለየ ነገር ቢያደርግ ነው አዳሜን እንዲህ በሱስ የሚያብከነክነው ሲል ፋሪድ ይጠይቅና መልሶ ለነገሩ ማንም አያውቅም ይለናል ።

በርሊን በሚገኘው ማክስ ፕላንክ ተቋም ተመራማሪ ሊቅ የሆኑት ፊሊፕ ሎሬንዝ የሚያሳዝነው ስለ ቲክቶክም ሆነ ሊያስከትል ስለሚችለው መዘዝ በክፍል አንድ መጣጥፌ ቲክቶክ በምዕራባውያን የማኅበራዊ ሚዲያና ፖለቲካ ላይ ስላስነሳው አቧራ እና ስለተደቀነበት የሕልውና አደጋ አነሳሳሁ። አሁን ደግሞ እግረ መንገድ ቲክቶክ በልጆች ስነ ልቦና እና አስተዳደግ ላይ ስለደቀነው አሳሳቢ አደጋ ከዚህ ቀደም ወላጆችን ለማሳሰብ ያደረግሁት ጥረት ፍሬያማ ሆኖ ስለ አላገኘሁት ዳግም ልመለስበት ወደድሁ።

በእኔ ትውልድ ወላጆቻችን በሰፈሩ የሚታወቅ ባለጌ ልጅ ካለ ከእሱ ጋር እንዳንገናኝ እንዳንውል ከማስጠንቀቂያ ጋር እንመከርና እንዘከር ነበር። አንድ ቀን አብረን ከታየን ማታ ቁንጥጫና ኩርኩም ይጠብቀናል። ሁለተኛ ከዚህ አሳዳጊ ከበደለው ጋር አይህና፤ ሁለተኛ እየተባልን ጭናችን አጋም እስኪመስል ይመዘለግ ነበር ። አጥፍተን ከተገኘን ደግሞ ከዚያ ስድ ጋር እየዋልህ ድሮስ እንባላለን ።

ከአህያ ጋር የዋለች ላም ፈ* ተምራ ትመጣለች እየተባለ ይተረትብናል። በሰፈሩ በትምህርቱ ጎበዝና ለወላጆች የሚታዘዝ ልጅ ካለ ደግሞ የእሱን ሰብዕናና ባሕሪ እንድንላበስ አጋጣሚ እየተፈለገ ከእነ ወላጆቹ ስሙ ይነሳል። ወላጆቻችን ሥነ ልቦናን አስኳላ ገብተው ባያጠኑም የአቻ ለአቻ ግፊት ወይም ተፅዕኖ በአዎንታም ሆነ በአሉታ በልጆች ሰብዕናና አስተዳደግ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ አበክረውና ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ያደግንባት ከተማ ጠባብ ስለነበረች ስለትምህርት ቤት አዋዋላችንም ከአስተማሪዎቻችን በቀላሉ ወሬ ማግኘት ስለሚችሉ ያም ያህል አይቸገሩም ነበር። አሁን አሁን ግን ከተሞች በመስፋታቸውና የተማሪዎች ቁጥሩም የዛን ያህል በመጨመሩ የወላጅን ክትትል ከባድ አድርጎታል። እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ደግሞ ይብስ ያዳግታል። በእንቅርት ላይ እንዲሉ በአናቱ ላይ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጨምሮበት ልጆችን በሥነ ምግባር ኮትኩቶ ማሳደግ ፈታኝ እየሆነ ነው ።

የሚማሩበትን ትምህርት ቤትና ጓደኞቻቸውን መምረጥ ብንችልም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ ወይም የቨርቹዋል ዓለሙን ጓደኞቻቸውን ግን መምረጥም ሆነ መከታተል ይቸግራለን። አሁን አሁን ልጆች ከእኩዮቻቸው ጋር ጭቃ አቡክቶ ቦርቆ ከመጫወት ይልቅ ቴሌቪዥንና እጅ ስልክ ላይ መጣድን ይመርጣሉ። እኔ በምኖርበት የጋራ መኖሪያ ቤት ቅዳሜና እሁድ ሆነ በአዘቦት ከትምህርት ቤት ሲመለሱ በእረፍታቸው ውጭ ወጥተው ሲጫወቱ አላይም ።

ድንገት መብራት ሲጠፋ ግን ቴሌቪዥን ስለሚቋረጥ፣ ብሮድ ባንዱም ስለማይሠራ ከየቤታቸው መውጣትና ሰፈሩን መቀወጥ ይጀምራሉ ። በዚህ መሐል መብራት ከመጣ ሰፈሩን በጩኸትና በፉጨት ያደበላልቁና ወደየቤታቸው ይመለሱና ሰፈሩ መልሶ ጭር ይላል። ሩጦና ዘሎ ያላደግ ሕጻን አካላዊም አእዕምሯዊ ብቃቱ ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለአፍታ አስቡት።

የእጅ ስልክ ምርኮኛ እየሆኑ ነው። ዘመድ ቤት ሲመጣም ሆነ እናንተ ዘመድ ጥያቄ ስትሔዱ ሁለት ዓመት ያልሞላቸው ሕጻናት ሳይቀሩ ጠጋ ብለው የእጅ ስልክን ተቀብለው ከአንድ አንድ ጌም ፍለጋ ነው የሚገቡት። ሁለት ዓመት ያልሞላት የእህቴ ልጅ ቤት ስትመጣ ስልኬን ለመቀበል ነው የምትሽቀዳደመው። መጣጥፎችን በእጅ ስልኬ ስለምጽፍና ብዙ ዶክመንት ስለሚይዝ ታጠፋብኛለች ብዬ ስለምፈራ ስለማልሰጣት ሁል ጊዜ በመጣች ቁጥር ጸብ ነው። ስታለቅስ ሌላ ስልክ ሰጥተው ያባብሏታል ።

ልጅ ሲያለቅስ በከረሜላ በቼኮላት ሳይሆን የሚደለለው በስልክ ሆኗል። ይህ የስልክ ፍቅር አብሮ ያድግና ከፍ ሲሉ ስልክ ካልተገዛለን ከወላጅ ጋር ጸብ ነው። መቼም ወላጅ የሚኖረው ለልጆቹ ነውና እነሱን ለማስደሰት ቢያጣም ተበድሮና ተለቅቶ ገዝቶ መስጠቱ አይቀርም ። ስልኩን ገዝቶ ይስጥ እንጂ አጠቃቀሙ ላይ ቁጥጥር ስለማያደርግ ልጆቹ በጌምና እንደ ቲክቶክ ባሉ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱስ ይጠመዳሉ። ለከፉ ሌሎች አደጋዎችም ሊጋለጡ ይችላሉ። ሱሱ ያድግና ለተለያዩ የአዕምሮ ሕመሞች ይዳርጋቸዋል ።

ለጭንቀት፣ ለድብርት፣ ራስን ለመጥላትና ራስን ለማጥፋት ይጋለጣሉ። ዛሬ ልጅን አሳድጎ ለወግ ለማዕረግ ማብቃት ፈታኝ እየሆነ ነው። ልጆቻችን ከእጃችን እያመለጡን ነው። ከእድሜያቸው ቀድመው ለተለያዩ እኩይ ተግባራት እየተጋለጡ ነው። ችግሩ ዓለማቀፋዊ ነው። መጠኑ ይለያይ እንጂ ምዕራባውያን በዚህ እየተፈተኑ ነው። ቢቸግራቸው ማኅበራዊ ሚዲያዎች የእድሜ ገደብና የይዘት ክልከላ እንዲያደርጉ ግፊት ቢያደርጉም የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ ስላልሆነ ከእነ አካቴው ይታገዱ እስከማለት ደርሰዋል ።

አሜሪካ ውስጥ ከ2024 ምርጫ፣ ከእስራኤልና ሐማስ ጦርነት፣ ከራሽያና ዩክሬን ጦርነት በመለጠቅ ቲክቶክ ዐቢይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ነው። ለዚህ ነው ብዙኃን መገናኛዎች የዜናዎቻቸው ማሟሻ አድርገውት የባጁት። ፋሪድ ዘካሪያ በ”ዋሽንግተን ፓስት” ጋዜጣ ፣ “Why banning TikTok won’t do any good” ወይም “ቲክቶክን ማገድ ለምን ፋይዳ ቢስ ይሆናል” በሚል ርዕስ በአንድ ወቅት ባስነበበን የግል አስተያየቱ፤ ሰለ ቲክቶክ ባሰብሁ ቁጥር ይበልጥ ያስፈራኛል የሚለው ፋሪድ ዘካሪያ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለተከታታይ ሁለት እሁዶች በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣም ሆነ በCNN/GPS ጽፎ አያውቅም። ባልተለመደና ተከታዮቹን ባስገረመ ሁኔታ ስለ ቲክቶክ ግን ጻፈ ።

ይህ የቻይናው መተግበሪያ አሜሪካንን እንዴት እንዳሳሰባትና እረፍት እንደነሳት ጥሩ ማሳያ ነው። ፋሪድ፣ ባለፈው ሳምንት የቲክቶክን መታገድ ተቃውሜ ሞግቼ ነበር ይለንና። ከተለያዩ ሰዎች ጋር ባደረግሁት ውይይት የተገነዘብሁት ነገር ቢኖር ፤ የአሜሪካውያን ዋና ስጋት ቲክቶክ የቻይናዊ ንብረት መሆኑ ሳይሆን ከየትኛውም ማኅበራዊ ሚዲያ በላይ አደገኛ ሱስ አስያዥ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ሁላችንን እያሳሰብ ያለጉዳይ ስለሆነ ሳንዘገይ አንድ ነገር ማድረግ አለብን ።

አሜሪካውያን በ2022 ዓ.ም ከሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች በአንደኛ ደረጃነት ቲክቶክን አውርደዋል። ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑ የአሜሪካ ብላቴናዎች ወይም ታዳጊ ልጆች ቲክቶክን ይጠቀማሉ። ከስድስቱ አንዱ ደግሞ በቲክቶክ ሱስ ተለክፈዋል። ከ2018 እስከ 2021 በተደረገ ጥናት የቲክቶክ ተጠቃሚዎች አኃዝ በ67 በመቶ ሲተኮስ፤ የፌስቡክና የዩቲውብ ተጠቃሚዎች በ10 በመቶ ብቻ ነው ከፍ ማለት የቻለው። ቲክቶክ ምን የተለየ ነገር ቢያደርግ ነው አዳሜን እንዲህ በሱስ የሚያብከነክነው ሲል ፋሪድ ይጠይቅና መልሶ ለነገሩ ማንም አያውቅም ይለናል ።

በርሊን በሚገኘው ማክስ ፕላንክ ተቋም ተመራማሪ ሊቅ የሆኑት ፊሊፕ ሎሬንዝ የሚያሳዝነው ስለ ቲክቶክም ሆነ ሊያስከትል ስለሚችለው መዘዝ ብዙ የምናውቀው ነገር የለም ይሉናል። ፋሪድ ዘካሪያ ስለቲክቶክ ያለን ግንዛቤ ዝቅተኛ የሆነው ምን አልባት ማኅበራዊ ሚዲያውን ዘግይቶ ስለተቀላቀለና የተጠቃሚ ማጥመጃ ስልቱ ወይም አልጎሪዝም እጅግ የተራቀቀ ስለሆነ ይሆን ሲል ይመረምራል ።

ሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ጓደኛህ የወደደውን ወይም ያጋራውን ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ፎቶና መልዕክት ሲያደርሱ ፤ ቲክቶክ ግን ፍላጎትህንና የምትወደውን ነገር እየገመተ አጫጭር ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ወይም ቪዲዎችን በአናት በአናቱ ያዥጎደጉድልኃል። አንዱ ያስወደደው ነገር ይህ ነው። በርካታ የሥነ ልቦና ጠበብት ቲክቶክን የሰው አዕምሮ ምግብ፣ አደንዛዥ እጽና ወሲብ ሲፈልግ ከሚያመነጨው ከዶፓሚን ወይም dopamine ንጥረ ነገር ጋር ያነጻጽሩታል። ሌላው ከሰዎች ጋር የሚያገናኘን፣ የሚያቀራርበንና ቤተሰብ የሚያደርገን ነገር ስናገኝ ደስተኛ መሆናችን ለእነ ቲክቶክ ሱስ አጋልጦናል የሚሉም አልታጡም ።

ማኅበራዊ ሚዲያ ምን ያህል አዕምሮአችንን እየተቆጣጠረው እንደ ሆነ ለመረዳት የሥነ ልቦና ሊቁን ስኪነር ንድፈ ሀሳብ ማንሳት ተገቢ ነው። “operant conditioning” በሚለው በዚህ ግኝቱ ሰዎች ጥሩ ሲሠሩ የምትሸልማቸው ከሆነ ያን ጥሩ ሥራ ደጋግመው ያከናውኑታል። ማኅበራዊ ሚዲያው በእሱ መመዘኛ ጥሩ ተሳታፊ የሆኑ ተከታዮችን ገንዘብን ጨምሮ በላይክ፣ በሼርና በኮሜንት ያበረታታል። የሚዲያው ተጠቃሚ ዩቲውበር ከሆነ ባገኘው ሰብስክሪፕሽን፣ ቪውና ላይክ መጠን ስለሚከፈለው ዩቲውበሩ የተሻለ ክፍያ እንዲያመጣለት ይጥራል። አንድ ዩቲውብር ቀድሞ የሚመለከተው ትላንት የጫነው ቪዲዮ ምን ያህል ሰብስክሪፕሽን፣ ቪውና ላይክ እንዳገኘና የተሰጠውን አስተያየት ነው ።

የቲክቶክ፣ የፌስ ቡክ፣ የቲዊተር፣ የኢንስታግራም፣ የቴሌግራምና የሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ይሄን ነው በየዕለቱና ሰዓቱ የሚያደርጉት። ብዙ ጊዜያቸውን እያጠፉበት በሄዱ ቁጥር ሱስ እየሆነባቸው ይሄዳል። እንስሳትን ሰርከስን ጨምሮ ለተለያየ ዓላማ የሚያሠለጥኑ ባለሙያዎች የሚጠቀሙት የስኪነርን ስልት ነው። የሚሠለጥነው ውሻ የታዘዘውን ሳያዛንፍ ሲፈጽም አጥንት ሲሰጠው እንደሚበረታታው ሁሉ ማኅበራዊ ሚዲያውም እነ ላይክንና ቪውን እንደ ዶፓሚን በመጠቀም በሱስ ያጠምዳል ።

በማኅበራዊ ሚዲያ ሐያሲነቱ የሚታወቁትና በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ጆናታን ሄይት ከማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የአዕምሮ ሕሙማን ብላቴናዎች ቁጥር በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ ነው ይሉናል። ከ2012 ዓም ወዲህ ከዓመት ዓመት በአዕምሮ ሕመም የሚሰቃዩ ሕጻናት ቁጥር በአስፈሪ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የስሜት መዋዠቅ ፣ በጭንቀት፣ በድብርትና ራስን በማጥፋት ሙከራ የተነሳ ሆስፒታል የሚገቡ ልጆች ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ እያደገ ነው ።

በተለይ ሴት ልጆች ከወንዶች በባሰ በማኅበራዊ ሚዲያ የተነሳ ለተስፋ መቁረጥ፣ ለጭንቀትና ራስን ለማጥፋት በሚዳርግ የአዕምሮ ሕመም እየተሰቃዩ ነው ይሉናል ጆናታን። በ2010ዎቹ ልጆች የእጅ ስልካቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ በታጨቁ ዘመናይ ስማርት ስልኮች መተካት የጀመሩበት ክፉ ዘመን ነው። በ2009 ዓ.ም ፌስቡክ “Like”ን ቲዊተር ደግሞ “retweet”ን በማስተዋወቅ በአጥንት እንደሚደለለው ሠልጣኝ ውሻ ሰዎችን በተለይ ልጆችን ማጃጃል ጀመሩ። ፌስቡክ በ2012 ዓም ኢንስታግራምን ሲጠቀልል ልጅ እግር ተጠቃሚዎችን በብዛት የሚያጠምድበት ተጨማሪ መረብ አገኘ ።

ጆናታን ሔይት የልጆች ማኅበራዊ ሚዲያን የመጠቀም መብት ከ13 ወደ 16 ከፍ ሊል ይገባል ሲሉ፤ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱም 16 ዓመት የሚል ረቂቅ ይዞ ብቅ ብሏል። ማኅበራዊ ሚዲያው ሙሉ በሙሉ የሰው ሠራሽ አስተውሎትን መጠቀም ሲጀምር ደግሞ ልጅ አዋቂ ሳይል አዳሜን የሱሱ ምርኮኛ ያደርጋል ሲሉ ጆናታን ፍርሀታቸውን አበክረው ይገልጻሉ ።

በሳንዲያጎ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ፕሮፌሰር የሆኑት ጄን ትዌንጌ ሰሞኑን በተወዳጁ የTIME መጽሔት ላይ እንደገለጹት። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠር ማዕከልን ወይም CDCን ጠቅሰው እንዳስታወቁት በ2021 ዓም ከሦስት አንድ የ2ኛ ደረጃ ሴት ተማሪ ራስን ስለማጥፋት ታስባለች። ከ2011 ጋር ሲነጻጸር ደግሞ ራስን የማጥፋት ሀሳቧ በ60 በመቶ አሻቅቧል ።

በርካታ ልጃገረዶች ደስተኛ እንዳልሆኑና ተስፋ ቢስነት እንደሚሰማቸው የተለያዩ ጥናቶች እያስታወቁ ነው ። ከ2012 ዓም ወዲህ የአዕምሮ ሕሙማን ብላቴናዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ከ2010 እስከ 2019 በድብርት የሚሰቃዩ ልጆች ቁጥር በእጥፍ አድጓል። ከድባቴ ጋር የተያያዙ እንደ ራስን መጉዳት፣ ራስን የማጥፋት ሙከራና ሌሎች የአዕምሮ በሽታዎች ከወንዶች ይልቅ በልጃገረዶች ዘንድ ይከፋሉ ።

ከ2009 እስከ 2015 ዓም ራስን በመጉዳት በድንገተኛ አደጋ ሆስፒታል ከገቡት መካከል እድሜያቸው ከ10 እስከ 14 የሆኑ ሴት ልጆች ብዛት በሦስት እጥፍ ተመንድጓል። ይሁንና ይላሉ ፕሮፌር ጄን በአሜሪካ የብላቴና አዕምሮ ሕሙማን ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን እኔና ባልደረቦቼ ስናስጠነቅቅ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ የሙያ አቻዎቻችን ይሳለቁብን ነበር ብለው ያስታውሱናል። ዛሬ ስናናንቀውና ስንክደው የኖርነው በሽታ ዋጋ እያስከፈለን ነው። ላለፉት አምስት ዓመታት የአዕምሮ ሕሙማን ልጆች ቁጥር የጤና ቀውስ ሆኗል።

ፕሮፌሰር ለመሆኑ የአዕምሮ ሕሙማን ቁጥር ከዓመት ዓመት ለምን እየጨመረ መጣ ብለው ይጠይቃሉ ። በ2009 ዓ.ም ይላሉ ፕሮፌሰር አንዲት ብላቴና አብዛኛውን ጊዜዋን የምታሳልፈው ከጓደኞቿ ጋር በመጫወትና የተወሰነ ጊዜዋን ደግሞ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነበር። በ2016 ዓም ነገርዬው የተገላቢጦሽ ሆነ። ማኅበራዊ ሚዲያ መጠቀም ግዴታ መሰለ። 90 በመቶ የሚሆኑ ሴት ልጆች በየቀኑ ማኅበራዊ ሚዲያ መጠቀም ጀመሩ። ከጓደኞቻቸውና ከአብሮ አደጎቻቸው ጋር ወጥቶ መጫወት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ይህ ደግሞ ለአዕምሮ ጤና አደገኛ ነው ።

ከጓደኛና ከአብሮ አደግ ጋር በአካል ተገናኝቶ መጫወት ቀረና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጥዶ መዋል የሕይወት ዘይቤ ሆነ ይላሉ ፕሮፌሰር ጄን። ይህ ደግሞ አደጋ ይዞ ይመጣል። ሴት ልጆችን ለወሲብ ብዝበዛ፣ ከአካል ክፍሎች ጋር ለተያያዘ ነውር፣ ለስድብና ለማሸማቀቅ አጋለጠ። ይሄን ተከትሎ የአዕምሮ ሕመም እንደ እንጉዳይ ፈሉ። በሳንዲያጎ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ፕሮፌሰር የሆኑት ጄን ትዌንጌ፤ ወላጆች ሆይ ልጆቻችሁ 16 ዓመት እስኪሞላቸው ወይም ከዚያ በላይ እስኪሆናቸው ከማኅበራዊ ሚዲያ አርቋቸው። ካልተቻለ ደግሞ በሚመለከቱት ነገር ላይ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር አድርጉ። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ወስኑ ሲሉ ይመክራሉ ።

ይህን አሳሳቢ ችግር ለወላጆች ብቻ በመተው መፍትሔ ማምጣት አይቻልም። ማኅበራዊ ሚዲያዎች የልጆችን ማኅበራዊ ሚዲያ የመጠቀሚያ የዕድሜ ጣራ ከፍ ሊያደርጉ ይገባል። መንግሥትም ይህን የሚወስን ሕግ ሊያወጣ ይገባል ይላሉ ፕሮፌሰር። አሁን አሁን ዴሞክራቶችም ሆኑ ሪፐብሊካኖች የችግሩን ስፋትና ጥልቀት የተረዱ ይመስላል። የልጆችን ማኅበራዊ ሚዲያ የመጠቀሚያ ዕድሜ ወደ 16 የሚያሳድግና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ደግሞ ዕድሜን የሚያጣራ አሠራር እንዲያስቀምጥ የሚያስገድድ ፤

እንዲሁም ልጆች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጥደው እንዲውሉ የሚያግባቡና የሚያባብሉ ስልቶችን እንዳይጠቀሙ የሚያስገድድ ሕግ ረቅቆ ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ቀርቧል ይሉናል ፕሮፌሰር። ቲክቶክ ከ15 እስከ 60 ሰከንድ የሚወስዱ አጫጭር ቪዲዮዎችን ማጋሪያ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ሲሆን በመላው ዓለም ሁለት ቢሊዮን ጊዜ ወርዷል ብሎኛል በሰው ሠራሽ አስተውሎት ታግዞ መረጃ የሚያፋልገውና እንደ ሰው የሚያወጋው ChatGPT ።

ሻሎም ! አሜን ።

ቁምላቸው አበበ ይማም(ሞሼ ዳያን) fenote1971@gmail.com

አዲስ ዘመን ሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You