የቀድሞ የፖሊስ አባል 40 ዓመት ተፈረደበት

በአሜሪካ ሚሲሲፒ ግዛት የፖሊስ አባል የነበረው ግለሰብ ከሌሎች አምስት ባልደረቦቹ ጋር ሆኖ ሁለት ጥቁር አሜሪካውያንን በቤት ውስጥ በማሰቃየቱ የ40 ዓመት እስር ተበይኖበታል።
ክርስቲያን ዴድሞን የተባለው የቀድሞ የፖሊስ መኮንን ከባልደረቦቹ ጋር ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ለፈጸመው ወንጀል ነው ቅጣት የተጣለበት።

ሌሎች ሦስት የፖሊሰ መኮንኖች ደግሞ በድምሩ የ54 ዓመታት እስር ተፈርዶባቸዋል።
ማይክል ጄንኪንስ እና ኤዲ ፓርከር የተባሉት ጥቁር አሜሪካውያን በፖሊስ መኮንኖቹ በመሳሪያ ሰደፍ የተደበደቡ ሲሆን ወሲባዊ ጥቃትም ደርሶባቸዋል።

አንደኛው ተጠቂ ጄንክሰን ችሎት ላይ በጠበቃው አማካኝነት ባስነበበው ጽሁፍ 40 ዓመት የተፈረደበት የቀድሞ መኮንን ከፍተኛውን ስቃይ ያደረሰበት እንደሆነ ገልጿል።

“ዴድሞን በአሜሪካ ውስጥ የመጥፎ ፖሊስ መኮንኖች ምሳሌ ነው” ሲለም አክሏል።
የቀድሞው የፖሊስ መኮንን ተበዳዩ ላይ ከመግደል መለስ ያሉ ጥቃቶች ሲያደርስ አፉ አካባቢ ላይ ተኩሶበታል። በዚህም ምክንያት ጄንክስን እስካሁን ለመናገር ይቸገራል።

በአንዲት ነጭ ቤት ውስጥ ጥቁር አሜሪካዊ በመቆየቱ እና በነበሩ አጠራጣሪ ድርጊቶች የአካባቢው ነዋሪዎች ጉዳዩን ለፖሊስ አሳውቀዋል። ፖሊሶቹ ጥቃቱን እየፈጸሙም በስልክ ይነጋገሩ ነበር።
ለአንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ያህል ጄንኪንስ እና ፓርከር እጃቸው ታስሮ ሲደበደቡ እና የዘረኝነት ጥቃት ሲደርሰባቸው እንደነበር ተመላክቷል።

የአሜሪካ የአውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛው ቶም ሊ ዲድሞን ሁለት ጥቁሮች እና ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ደግሞ አንድ ነጭ አሜሪካዊ ላይ “እጅግ አስደንጋጭ፣ አሰቃቂ እና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት” ፈጽሟል ብለዋል።
ዴድሞን 40 ዓመት እንደተፈረደበት ከመታወቁ አስቀድሞ ሌላኛው ባልደረባው ኦፕዴክ 17 ዓመት ከ 6 ወር ተበይኖበታል።
ብሬት ማክአልፒን እና ጆሸዋ ሃርትፊልድ የተባሉት የቀድሞ የፖሊስ መኮንኖችም በተመሳሳይ የብይን ውሳኔ ይተላለፍባቸዋል።

በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ዓርብ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You