የጡት ካንሰር በዓለማችን በብዛት ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነት ነው። የስርጭቱ መጠንም ከግንባር ቀደም አምስቶቹ የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ነው። የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በዓለማችን ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች መካከል 25% ገደማ የሚሆነው የጡት ካንሰር ነው። በተጨማሪ በጠቅላላ በካንሰር ምክንያት ከሚመጡ ታማሚዎች ውስጥ 14% የሚሆኑት የጡት ካንሰር ታማሚዎች ናቸው። የጡት ካንሰር ሴቶችን በከፍተኛ መጠን ለሞት ከሚያደርጉት የካንሰር ዓይነቶች አንደኛው እና ዋነኛው ነው። ምንም እንኳን የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በብዛት ቢታይም በወንዶች ላይም ሊከሰት ይችላል። የመከሰት ዕድሉ በመቶኛ ሲገለጽ 1% የሚሆነው የጡት ካንሰር በወንዶች ላይ የሚታይ ነው። ብዙ ዓይነት የጡት ካንሰር ያለ ሲሆን እንደ ዓይነቱ የህመሙ ጥንካሬ ይለያል።
የጡት ካንሰር ሴቶችን በከፍተኛ መጠን ለሞት ከሚያደርጉት የካንሰር ዓይነቶች አንደኛው እና ዋነኛው ነው። ምንም እንኳን የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በብዛት ቢታይም በወንዶች ላይም ሊከሰት ይችላል። የመከሰት ዕድሉ በመቶኛ ሲገለጽ 1% የሚሆነው የጡት ካንሰር በወንዶች ላይ የሚታይ ነው። ብዙ ዓይነት የጡት ካንሰር ያለ ሲሆን እንደ ዓይነቱ የህመሙ ጥንካሬ ይለያል።
የጡት ካንሰር ምልክቶች
- በጡት ላይ የሚወጣ እባጭ/ይህ እባጭ ከአካባቢው አካል የተለየ እባጭ ነው።/
- በጡት ላይ የሚከሰት የመጠን፤የቅርፅ፤የቆዳ ቀለም መቀየር
- በጡት ጫፍ ላይ ያሉ ለውጦች/ወደ ውስጥ መግባት (አዲስ የሆነ)/
- በጡት ላይ መላጥ፤መቁሰል፤የተለየ ፈሳሽ ማውጣት
- በጡት ላይ የሚታይ የቀለም ለውጥ/መቅላት፤ የብርቱካን ልጣጭ የሚመስል/
ሌሎች ከበሽታው/ከካንሰሩ መሰራጨት ጋር ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች እንደ ሳል፤በብብት አካባቢ የሚታይ እብጠት፤የሆድ
ማበጥ፤የሳንባ ውሃ መቋጠር ኢንፌክሽን ወ.ዘ.ተ
የጡት ካሰር መምጫ ምክንያቶች
የተለያዩ የምርምር ጥና ቶች እንደሚያሳዩት የጡት ካንሰር በዘር፤ በአኗ ኗር ዘይቤ፤ በሆርሞን መዛ ባት እንደሚከሰት እና ተጋላ ጭነቱም በቀጥታም ሆነ በተዘ ዋዋሪ ከላይ ከተጠቀሱት ጋር እንደሚገናኝ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
እነዚህ መምጫ ወይም አጋላጭ ተብለው ከሚጠቀ ሱት ውስጥ፡-
- ሴት መሆን
- የዕድሜ መጨመር
- በቤተሰብ የነበረ የጡት ህመም ወይም ካንሰር
- ውፍረት
- ዘግይቶ ልጅ መውለድ
- የአልኮሆል እና ሲጋራ መውሰድ
- የሆርሞን ህክምና
- በዘር
- ለጨረር መጋለጥ
- የወር አበባን በለጋ ዕድሜ መጀመር
- የወር አበባን ለረጀም ጊዜ (ዕድሜ) ማየት
ቅድመ ጥንቃቄዎች
- የጡት ካሰር አስቀድመን ሙሉ በሙሉ ልንከላከለው ባንችልም ህመሙን በጊዜ በማግኘት አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ፤የህመሙን ስርጭት እንዲሁም መዘዞቹን ከላከል ይቻላል።
ከእነዚህ ውስጥ፡-
- ገላችንን በምንታጠብበት ጊዜ ሁሉንም የጡታችን ክፍል መፈተሽ (እባጭ መኖሩን እና አለመኖሩን ማየት፤የቀለም ለውጥ መኖሩን ማየት)
- በሁለቱም ብብታችን ውስጥ እባጭ አለመኖሩን መፈተሽ
- ተመጣጣኝ የሆነ የሰውነት ክብደት እንዲኖረን ማድረግ።
- የአልኮል መጠንን ማስወገድ
- ቋሚ የሆነ የህክምና ክትትል እንደ ዕድሜዎ የአልትራሳውንድ እና የማሞ ግራፊ ምርመራ ማድረግ (በሀኪም የሚታዘዝ)
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
- የሆርሞን ህክምናዎችን እና ለጨረር ተጋላጭነትን መቀነስ ናቸው።
ህክምናው እና ምርመራው
የጡት ካንሰር ለቅድመ ጥንቃቄው እና ህመሙን ለማረጋገጥ ሲባል የሚደረጉ ምርመራዎች ያሉ ሲሆን በዋናነት፡-
- የአልትራሳውንድ የማሞግራፊ የሲቲ ስካን ምርመራዎች ዋናዎቹ ናቸው።
- ሌሎች ከእባጭ የሚወሰዱ እና ምርመራ የሚደረጉም ይኖራሉ። ይህ ምርመራ የካንሰር ዓይነቱን ለመለየት ያስችላል።(Biopsy)
- ሌሎች ምርመራዎች የካንሰር መሰራጨትን ለመፈተሽ (ለመመርመር) የሚደረጉ ይኖራሉ፤ለምሳሌ (የ X-Ray ወይንም ራጅ ምርመራ)
አንድ ጊዜ የጡት ካንሰር መኖሩ ከተጋለጠ በኋላ የጡት ካንሰርን መሰራጨት አለመሰራጨቱን የታካሚውን የጠቅላላ የጤና ሁኔታ እንዲሁም የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ህክምናው የሚደረግ ይሆናል።
ህክምናው ከላይ እንደተጠቀሰው የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የቀዶ ህክምና፤የጨረር ህክምና፤የኬሞቴራፒ እና የሆርሞን ህክምና ሊደረግ ይችላል።
- የታካሚዎቹ የመዳን ተስፋ ወይም የኑሮ ዘመን እንደ የካንሰር ዓይነቱ እና የስርጭቱ (በሰውነት የመሰራጨት) የሚወሰን ይሆናል።
- አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 17/2011