ኡጋንዳ ሶማሊላንድ ከሶማሊያ እንድትዋሃድ

ኡጋንዳ ሶማሊያ እና ተገንጥላ ራሷን እያስተዳደረች ያለችው ሶማሊላንድ ውህደት እንዲፈጥሩ ለማድረግ እንደምታደራድር አስታውቃለች። ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ከተገነጠለች ሦስት አስርት አመታትን አስቆጥራለች።

የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮሪ ሙሰቨኒ የማደራደሩን ሚና ለመወጣት የተስማሙት ባለፈው አርብ የሶማሊላንድ ልዩ መልዕክተኛ ጃማ ሙሳ ጃማ በኡጋንዳ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ መሆኑን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

«ፕሬዚዳንት ሙሰቨኒ በሶማሊላንድ እና ሶማሊያ መካከል ውህደት ለማመቻቸት ተስማምተዋል» ብሏል መግለጫው። ሶማሊላንድ ከሶማሊያ የተገነጠለችው በፈረንጆቹ በ1991 ቢሆንም የነፃ ሀገርነት ዓለምአቀፍ እውቅና አላገኘችም።

ሙሰቨኒ እንደስትራቴጂ ሲታይ ስህተት ስለሆነ መገንጠልን አንደማይደግፉ ገልጸዋል። ይህ ውህደት የአፍሪካ ቀንዷን ሶማሊያን የአልሸባብ ጥቃትን ጨምሮ በሌሎች ቡድኖች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመቋቋም አቅም ይፈጥርላታል።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን  መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You