አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ባካሄደው ኦፕሬሽን በመዲናዋ የተለያዩ ወንጀሎችን በተደራጀ መልኩ ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን እና ለወንጀል ተግባር ሲውሉ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ትናንት በሰጡት መግለጫ፤ ፖሊስ በልደታ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ ክፍለ ከተማዎች ባካሄደው ጥናት ላይ በተመሰረተ ዘመቻ እና ድንገተኛ ፍተሻ አካሂዷል፡፡
በዚህም ሰነድ የሌላቸውን እና ህጋዊነታቸው ያልተረጋገጠ 260 ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። በህገ ወጥ ተግባር ላይም ማለትም በቅሚያ፣ በዝርፊያ፣ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና መድኃኒት ዝውውር ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተጨማሪም ከአደገኛ እፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ትልልቅ ሆቴሎች የሚያርፉ የውጭ ሀገራት ዜጎችን በደላላ እና በሆቴል ሠራተኞች በኩል በማግባባት ሺሻ እና ባእድ ነገር ተቀላቅሎ ወደ ሚጨስባቸው ስፍራዎች በመውሰድ የወንጀል ድርጊት እንዲፈፀምባቸው ያደረጉ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡
በቅንጅት የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ከ250 ሺ ብር በላይ ትልልቅ ህንፃዎችን በመከራየት የወንጀል ድርጊት ሲፈፅሙ እንደነበርም አመልክተዋል።
በሦስት ክፍለ ከተሞች በተደረጉ ዘመቻዎች ከ2 ሺ 500 በላይ የሺሻ ማጨሻ እና መገልገያዎች ከዋና ዋና የድርጊቱ ፈፃሚዎች ጋር ተይዘዋል። ግማሽ ኪሎ የሚደርስ አደገኛ እፅም በዘመቻው ተይዟል።
እንዳልሆነም ነው የሚያብራሩት፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የህገ መንግሥት ጉባዔ አባል አቶ ክፍለፅዮን ማሞ ፣ሁል ጊዜ ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ለህግ እንደሆነ ይገልጻሉ ::ህግን በአግባቡ መተግበር ብዙ ወጪ እንደማያስወጣ ጠቅሰው፣ በህግ ደረጃ ማንም ሰው ከህግ በላይ እንዳልሆነም በመግለጽ የአቶ ሙልዬን ሃሳብ ያጠናክራሉ፡፡
በአገሪቱ ህግና ሥርዓት መስፈኑ ለሁሉም እንደሚጠቅም ጠቅሰው፣ ከክልሎቹ ጋር በመወያየት ተጠርጣሪውን አሳልፈው እንዲሰጡ ማድረጉ የተሻለ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡
እንደ አቶ ክፍለጽዮን ገለጻ፤ቁጭ ብሎ ቃላት መወራወር ብቻ ሳይሆን መነጋገርና መወያየት ያስፈልጋል ::በአንድ ክልልና በፌዴራል መንግሥት መካከል በህገ መንግሥቱ የተቀመጡ የስልጣን ክፍፍሎች አሉ።
በመብት፣ስልጣንና ጥቅም ዙሪያ ፌዴራልና ክልሎች እንዲሁም ክልሎችም እርስ በርሳቸው የሚያግባባቸው ጉዳይ ሊኖር ይችላል ::በአንድ ፌዴራላዊ ሥርዓት ውስጥ ለመኖርም ስምምነት ይደረጋል፡፡ በወንጀል ህጉ ላይ ክልል በሚል የተጠቀሰ ነገር እንደሌለ ተናግረው፣ የወንጀል ህጉ የሚመሰረተው በህገመንግስቱ ላይ ነው ::ህጉ ሲተረጎም መሰረት የሚያደርገውም ህገ መንግሥቱን ነው፡ ሲሉ ያብራራሉ፡፡
‹‹ክልል አልተባበር ካለና የፌዴራል መንግሥቱ ገብቶ ቢይዝ ምን ሊከትል ይችላል? የሚለውም መታየት›› ይኖርበታል፡፡›› የሚሉት አቶክፍለጽዮን፣‹‹የፌዴራል መንግስቱ ‹ያለኝን አቅም ተጠቅሜ ሄጄ ይዤ አመጣለሁ› የሚል ከሆነ ይህን ዓይነቱን እርምጃ ህገ መንግሥቱ ይፈቅዳል ወይስ አይፈቅድም የሚለው የህገ መንግሥት ትርጉም ይሆናል። ›› ሲሉ ያብራራሉ፡፡ዋናው ነገር የክልሎችና የፌዴራል መንግሥቱ ግንኙነትና ስምምነት መጠበቅ ያለበት መሆኑ ላይ ነው፡፡›› ይላሉ፡፡
እንደ አቶ ክፍለፅዮን ገለፃ፤አለመግባባት ሁሌም ይፈጠራል፤ነገር ግን አለመግባባቱን በውይይት ለመፍታት ቅድሚያ መስጠት ይገባል ::ሌላ ምንም መፍትሄ የለውም ::እንኳን በግለሰቦች ጉዳይ አይደለም ለሌሎች አበይት ጉዳዮችም ከህግና ከውይይት ውጪ ሌላ መፍትሄ የለም ::
‹‹ የተጨበጠ ነገር ካለና ያንን መሰረት በማድረግ ተጠርጣሪው ያለበትን ክልል ‹አስረክብ ሲባል አላስረክብም› የሚልበት ምክንያት ካለም ያንን ለህዝቡ ማቅረብ ይገባል፡፡››ይላሉ፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ሙልዬ፣‹‹ፌዴራል ፖሊስም ሆነ መከላከያ ታዲያ የት ላይ ሆነው ነው የሚሰሩት?›› ሲሉ ይጠይቁና፤ የፌዴራል መንግሥት እንደነዚህ ያሉ ተጠርጣሪዎችን በኢትዮጵያ በየትኛውም ክልል ህጋዊ በሆነ ስርዓት ተጣርቶ ጉዳያቸው የሚቀጥል ተጠርጣሪዎችን ለህግ የማቅረብ ኃላፊነት፣ ግዴታም ሆነ ስልጣን አለው ::ይህን ባያደርግ በህገ መንግሥቱ ተጠያቂም ይሆናል፡፡››ነው የሚሉት፡፡
እንደ አቶ ሙልዬ ማብራሪያ ፤የፌዴራል ፖሊስ ከየትኛውም ሥፍራ በወንጀል የተጠረጠረን ሰው የማምጣት መብት አለው ::የፌዴራል ፖሊስ በራሱ የክልሎች ስብስብ መሆኑም ለዚህ ይጠቅማል ::ሊከለክለው የሚችል አካል መኖር የለበትም፤ እንዲያውም የክልሉን ልዩ ኃይል ትብብር ሊጠይቅ ይችላል፡፡
‹‹ከዚህ በስተቀር የፍቀድልኝ ዓይነት ነገር በህግ አይሰራም፡፡››ሲሉ ጠቅሰው፣ ጉዳዩ ከፌዴራል ፖሊስ በላይ ሲሆን ደግሞ መከላከያውን መጠቀም እንደሚቻል ይገልጻሉ ::ይህን በማድረግ የፌዴራል መንግሥቱ ህገ መንግሥቱን የማስከበር ኃላፊነት እንዳለበት በማስገንዘብ፡፡
አቶ ክፍለፅዮን ጉዳዩ ከህግ በላይ ከሆነም የሚሆነው የፖለቲካ ጉዳይ እንደሆነ በመጥቀስ፣በህግና በፖለቲካ መካከል የተሰመረ ድንበር መኖሩን ይናገራሉ፡፡‹‹ሁልጊዜ ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ለህግ በመሆኑ፣ ህግ በአግባቡ የሚተገበር ከሆነ ወደ ግጭትም አያስገባም ::ከህግም ከፖለቲካም መፍትሄ በላይ የሚሆን ከሆነ ግን በሦስተኛ ደረጃ ወደ ግጭት ነው የሚገባው፤ ይህ ደግሞ የማይፈለግ ነው ::››ሲሉ ያመለክታሉ፡፡
በአንድ አገር ውስጥ ያሉ ክልሎች የውስጥ ጉዳዮችን ብቻ ሳይሆን በመንግሥታትም መካከል ያለ ግንኙነት የሚወሰነው በዚህ መሆኑን ጠቅሰው፣በመጀመሪያ ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ጋር በተያያዘ በመንግሥታት መካከል የህግ ግንኙነቶች መኖራቸውን፣ሀገሮቹ የማይስማሙ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፖለቲካ ሊወስዱ እንደሚችሉ እና ከዚያ ሲብስ ደግሞ ወደ ማዕቀብና ሌሎች ጉዳዮች እንደሚወስዱ ይህ ደግሞ የማይፈለግ ዓይነት ውሳኔ ነው ሲሉ ዳኛው ያብራራሉ፡፡
‹‹አሳልፎ መስጠት አለመስጠት የሚባለው ነገር እንዴት በአንድ አገር ውስጥ ሊኖር ይችላል፡፡››ሲሉ የሚጠይቁት አቶ ሙልዬ፣‹‹አሳልፎ መስጠት አገር ከአገር ጋር የሚፈጸም መሆኑን ይናገራሉ ::
በኢፌዴሪ ህገ መንግሥት የፍርድ ቤቶች ጣምራነትና ስልጣንን አስመልክቶ አንቀፅ 80 ንዑስ አንቀፅ 1 ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ጉዳዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ስልጣን እንዳለው ተደንግጓል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃዎች መውሰድ የጀመረች ሲሆን፣ ለዚህም በቅርቡ ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በተባሉ 26 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱ ይታወሳል ::ከእነዚህም መካከል አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በሌሉበት ክስ የተመሰረተባቸው አራቱ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ናቸው ::
በሀገራችን አንዳንድ ክልሎች እየተፈጸመ ባለው የማፈናቀል ተግባር ሚና የነበራቸውን ተጠርጣሪዎች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የመንግሥት መዋቅሩ ከለላ በመስጠት አሳልፎ አለመስጠት እየታየበት መሆኑንም የሰላም ሚኒስትሯ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በየደረጃው በማፈናቀል ተግባር ላይ የተሳተፉየፖለቲካና የፀጥታ ኃይል አባላትም በክልሎችና በከፍተኛ አመራሩ ትብብር ማነስ በህግ ጥላ ስር ለማዋል መቸገሩንም አስታውቋል።
የሠላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የ2011 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንዳስታወቁት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን 4043 መዝገቦች ላይ ምርመራ ተደርጎ በ2276ቱ ላይ ዓቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት ተልኳል።
ከማፈናቀል ጋር በተያያዘ እስካሁን ክስ የተመሰረተው በ4 መቶ 68 ላይ ብቻ ነው። ከእነዚህም 420ዎቹን አፈናቃዮች በህግ ጥላ ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
አቶ ክፍለፅዮን፣ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ በሚደረገው ግብግብ ወደ እርምጃ የሚኬድ ከሆነ ምን ዓይነት ውጤት ይኖረዋል የሚለው መታየት እንዳለበት ያመለክታሉ ::አቶ ሙልዬ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ህግ ፊት እንዲቀርቡ የማይደረግ ከሆነ ስርዓት አልበኝነት ይመጣል ::የፈለገው አካል በጉልበቱ የፈለገውን ያደርጋል፤ ህገ መንግሥቱና ህጉ አደጋ ላይ ይወድቃሉ ::አገርም የመፍረስ ስጋት ያድርባታል ::በማለት ያክላሉ።
በመሆኑም የትኛውም ኃላፊነት የተሰጠው የፍትህ አካል እንዲሁም የፀጥታ ኃይል በመተባበር ማንም በወንጀል የተጠረጠረ አካል በህግ ፊት እንዲቀርብና ፍትሐዊ በሆነ ዳኝነት እንዲዳኝ ማድረግ ይጠበቅበታል ::
አዲስ ዘመን ግንቦት 6/2011
በጋዜጣው ሪፖርተር