ንቅሳት (Tattoos) ከድሮ ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋል ባህላዊ የውበት መገለጫ፣ ማጌጫ እና መዘነጫ ነው። በሰውነት ላይ ሊታዩ የሚችሉ ንቅሳቶችን በመነቀስ ማጌጥ የተለመደ ነበር። በተለይም ሴቶች ከፊታቸው ጀምሮ ድዳቸውን፣ እጃቸውንና መሰል ቦታዎች ላይ በተለያዩ ዲዛይኖች በመነቀስ በንቅሳታቸው ተውበው፤ አምረውና ደምቀው የሚታዩበት እንደነበርም ይታወሳል።
ንቅሳትን በአብዛኛው ሴቶች የሚነቀሱና ጎልተው የሚታዩበት ይሁን እንጂ ብዙ የሚነቀሱ ወንዶችም አይጠፉም። በተለይ ድዳቸው በመድማት የሚቸገሩ ሰዎች ቢነቀሱ ደሙ እንደሚቆምላቸው እንዲነቀሱት የሚመከረ በመሆኑ ጥቂት የማይባሉ ወንዶች ይነቀሳሉ። ድዳቸውን የተነቀሱ ሰዎች ጥርስ ጉራማይሌ የተወቀረ (የተወቀረች) ተብለው ውበታቸው ጎልቶ እንዲታይ ያደረጋቸዋል። ከዚህም ባሻገር ከሌሎች እንደመለያ ምልክት ሆኖ ያገለግላቸዋል።
ይህ ንቅሳት እያልን የምንጠራው የውበት መጠበቂያ አሁን ላይ ሀገርኛ ስሙን ቀይሮ ‹‹ታቱ (Tattoos)›› በሚል የእንግሊዝኛው ቃል ተተክቶ በአዲስ መልኩ ብቅ ካለ ሰንበትበት ብሏል። ምስጋና ለቴክኖሎጂ ይግባውና አሁን ላይ የሰው ልጆችን ድካም እና ጊዜ የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎች እየዘመኑ መጥተዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በባህላዊ መንገድ ሲሰራ የነበረው ንቅሳት (ታቱ) ዘምኖ በዘመናዊ መንገድ እየተሰራ ይገኛል።
የታቱ ወይም የንቅሳት አድናቂ መሆኗን የምትናገረው ወጣት ሩታ ሳምሶን በቀኝ ትከሻዋ በኩል ጀርባዋን ተነቅሳዋለች። የለበሰችው ልብስም ንቅሳቷን አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ሩታ እንደምትለው፤ ንቅሳት ወይም ታቱ ውስጣዊ ስሜቷን የምትገልጽበት ነው። የተነቀሰችው የምትወደውን ምንም ጊዜ ከውስጧ የማታወጣው ዘላለም አብሯት ሊኖር የሚችል እንደሆነ ነው ያጫወተችን። የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል እንደተነቀሰች የምትናገረው ሩታ፤ ‹‹እኔ ምንም ጊዜ አብሮኝ ያለ ለዘላለም አብሮኝ የሆነውን ክርስቶስ በሰውነቴ ላይ ስላደረግኩት ሁሌም ደስ ይለኛል›› ብላለች፡
ወጣት አብነት ዘሪሁን የንቅሳት (ታቱ) ባለሙያ ነው። በድሮ ጊዜ ስለነበረውና አሁን ላይ ስሙን ቀይሮ ስለመጣው እንዲሁም የዘመናዊነት መገለጫ ሆኖ እየተስተዋለ ስላለው ንቅሳት (ታቱ) ሲናገር፤ ቀደም ሲል ሰዎች ንቅሳት (ታቱ) ይነቀሱ የነበረው በባህላዊ መንገድ በሰው እጅ እንደ መርፌ፣ አጋም እሾህ አይነት መሳሪያዎችን በመጠቀም ነበር። ይሁንና አሁን ላይ ንቅሳት ለመስራት የሚያስችል ዘመናዊ ማሽን በመኖሩ ድካም ቀንሶ ጊዜንም ቆጥቧል።
እሱ እንደሚለው፤ ቴክኖሎጂው የንቅሳት ሥራን ቀላል አድርጎታል። ቀደም ሲል ንቅሳት ለመሥራት የሚያስፈልገው ቀለም በባህላዊ መንገድ ከተለያዩ እጽዋት የተቀመመና በቤት ውስጥ የሚገኝ ጥላሸት እንደነበር አስታውሶ፤ አሁን ላይ ግን በዘመናዊ መንገድ የተዘጋጀ ቀለም መኖሩን ይናገራል።
ንቅሳት ወይም ጉራማይሌ ንቅሳት በራሱ የተለየ ውበት የሚሰጥ ነው የሚለው ባለሙያው፤ ሰዎች ድድን የሚነቀሱት ለውበት ብቻ ሳይሆን ለጤናም ነው። በተለይ ቀደም ሲል ባሉት ጊዜያት ድዱ እየደማ የሚቸገር ሰው ድዱን ቢነቀስ መድማቱ እንደሚቀንስለት ነው የሚነገረው።
ንቅሳት ቀደም ባለው ጊዜ እንደውበት መጠበቂያ ተደርጎ ይታይ ስለነበር በርካታ ሰዎች በፊታቸው፣ በእጃቸው፣ በአንገታቸው፣ በደረታቸው፣ በጥርሳቸውና በሌሎች የሰውነት ክፍላቸው ላይ በመነቀስ ተውበው ይታዩ ስለነበረ በአብዛኛው ሰው ይፈልገው ነበር። ይሁንና ንቅሳት (ታቱ) ከተወሰነ ጊዜ በፊት የባላገርነትና የኋላቀርነት መገለጫ ሆኖ በመቆጠሩ ተቆጥሮ ብዙዎች የተነቀሱትን ንቅሳት ለማስለቀቅ ከላይ ታች ይባል እንደነበር ነው ወጣት አብነት ያስታወሰው።
አሁን ላይ ደግሞ ለንቅሳት ይሰጥ የነበረው አመለካከት እየተቀየረ በመምጣቱ አብዛኛውን ሰው በተለይም ወጣቱ እየተጠቀመበት መሆኑን ወጣት አብነት ይናገራል።
እዚያ ሥልጣኔ ላይ እስከምንደርስ ግን አስገዳጅ መሆኑ አልቀረም። እዚህ ላይ ክርክር ይነሳል። በአንድ በኩል፤ ተማሪዎች ወደ ፈተና እየገቡ የታጠቁ የፀጥታ አካላትን ሲያዩ ምን አልባት ‹‹ምን ይፈጠር ይሆን?›› የሚል ጭንቀት ይፈጠርባቸው ይሆናል። ልጆች ናቸውና ለደህንነት ሲባል ብቻ የተያዘ መሆኑን ቶሎ አይረዱ ይሆናል።
በሌላ በኩል ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ ደህንነትና ነፃነት ሊሰማቸው ይችላል። ምክንያቱም እነዚያ ፖሊሶች በዙሪያቸው የቆሙት ለተማሪዎች ደህንነት ነው። ደህንነት ሲባል የግድ ከሽብር ጋር ብቻ አይደለም፤ ድንገተኛ አደጋ (የተፈጥሮም ሆነ የትራፊክ አደጋ) ቢያጋጥም ከማንምና ከምንም በፊት ቀድሞ የሚገኘው የፀጥታ አካል ነው። ስለዚህ በብዙ ምክንያቶች በፖሊስ መታጀባቸው ትልቅ ደህንነትና ነፃነት እንዲሰማቸው ያደርጋል።
በሌላ በኩል በሀገራቸው ያለውን ነባራዊ ሁኔታም ያውቃሉ። ወቅቱ የመንደር ሽፍቶች የበዙበት ነው። እነዚህ የመንደር ሽፍቶች ፖሊስ ባለበት አካባቢ ዝር አይሉም። ይህን ደግሞ ልጆች ያውቃሉ። ስለዚህ በፖሊስ መታጀባቸው ከእነዚህ ሁሉ ስጋቶች ነፃ ያደርጋቸዋል።
በዚሁ እግረ መንገድ ግን ስለ ፖሊስና ሕብረተሰብ (ፕሮግራሙን ማለቴ አይደለም) እንተዛዘብ። ይህን ትዝብት ጥሩ ለማድረግ በቅርቡ አንድ ጓደኛዬ የነገረኝ ገጠመኝ ማሳያ ይሆነኛል።
ለአንድ የሞባይል ሽያጭና ጥገና ቤት የሚጠገን ስልክ ሰጥቶ እስከሚሰራ ድረስ እዚያው አካባቢ ዘወር ዘወር እያለ ነው። ፖሊሶቹ ምን እንደመሰላቸው አላውቅም (ክስተቶቹን ራሱ ነው የተረከልኝ) አናገሩት። ‹‹ምንድነው?›› ሲላቸው፤ ለረጅም ደቂቃዎች እዚህ አካባቢ ቆመሃል፤ ምን ለማድረግ አስበህ ነው? ይሉታል። እሱም ሞባይል እያስጠገነ መሆኑን ሲነግራቸው አላመኑትም። ሞባይል ቤቱ ጋ ሄደው ስልክ እያሰራ መሆኑን አረጋገጡ።
በእነዚህ እንቅስቃሴዎቻቸው ውስጥ መታወቂያ ጠይቀውት የመንጃ ፈቃድ አሳይቷል። ሞባይል እያስጠገነ መሆኑን ሲያረጋግጡ ‹‹ተገላገልኩ›› ብሎ ነበር። አረጋግጠው እንደጨረሱ ‹‹መንጃ ፈቃድ መታወቂያ አይሆንም›› አለው መታወቂያውን የያዘው ፖሊስ። ይሄኔ ነው የልጁ ብልግና ነጥሮ የወጣው። ‹‹መንጃ ፈቃድ መታወቂያ አይሆንም›› ሲለው፤ ፖሊሱን አጸያፊ ስድብ ተሳደበ። ይሄኔ ፖሊሱ ልጁን በጥፊ መታው። ሌሎች ፖሊሶች መጡ። ተይዞ ጣቢያ ሄደ። እዚያ የሆነውን ሁሉ ተናግሮ የፖሊሶች አለቃ ነገሩን ቀለል አድርጎ ለቀቀው። ልጁ ደግሞ ‹‹ፖሊስ ጣቢያ ስደርስ ያላልኩትንና ያላደረኩትን ነገር እንዳደረኩ አድርገው ዋሽተዋል›› በሚል ካልከሰስኩ አለ። በመጨረሻም ጥፋተኝነቱን ነግሬው ነገሩ ተቋጨ።
ይህ የቅርብ ጊዜ ገጠመኝ እና እኔም ክስተቱን በቅርበት የሰማሁት ስለሆነ እንጂ እንዲህ አይነት አግባብነት የሌላቸው የፖሊስና ግለሰቦች ግጭቶች አሉ።
በመጀመሪያ የልጁን አለመሰልጠን ልብ በሉ። ፖሊስ አጠራጣሪ ነው ብሎ የገመተውን ነገር ማረጋገጥ ሥራው ነው። ፖሊሰ ፀሐይና ዝናብ የሚፈራረቅበት የሕብረተሰብን ደህንነት ለማረጋገጥ ነው። ይህን የሚያደርገው ደግሞ ነገሮች ከሆኑ በኋላ ብቻ ሳይሆን ያጠራጥራል ያለውን ነገር ሁሉ በመጠየቅ ነው። እንዲያውም በብዛት የሚወቀሱት እኮ አንድ ነገር ከተፈጸመ በኋላ ነው የሚደርሱ በሚል ነው። የልጁ አላዋቂነት የፖሊስ ሥራ ይሄ መሆኑን አለማስተዋሉ ነው። በራሱ ንጽህና እርግጠኛ ቢሆንም ለምን ተጠረጠርኩ ብሎ መደንፋት አለመሰልጠን ነው።
ሲቀጥል፤ ፖሊሶች ስህተት ቢሆኑ እንኳን በንግግርና በውይይት ስህተታቸውን መንገር እንጂ ‹‹ሌባ ቢሆን ኖሮ አትይዙትም ነበር›› እያሉ እልህ ማስገባት አላዋቂነት ነው። ከዚህም ሲያልፍ በሙያና ብቃታቸው ላይ፣ በትምህርት ደረጃቸው ላይ (ለዚያውም ሳያውቀው) ፀያፍ ስድብ ንቅሳት (ታቱ) በአሁን ወቅት በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱን አጫውቶናል። ዘመናዊውን ንቅሳትን የሚሰሩት ወጣቶች እንደሆኑና ንቅሳት ለውበት እንዲሁም የውስጥ ፍላጎታቸውን የሚገልጹበት እንደሆነና የአመለካከት ለውጥ መኖሩን ነው ያስረዳው።
ወጣት አብነት እንደሚለው፤ ወጣቱ ንቅሳት (ታቱ) በሰውነት ክፍሉ ላይ የሚነቀሰው የሚወደውን ሰው ለማስታወስ አንዱ ሲሆን፤ የዚያን ሰው ስም ወይም ፎቶ የራሱ ሰውነቱ ላይ ተነቅሶ ሊያስታውሰው ይፈልጋል። ንቅሳት ሰው የራሱ ሰውነት ተጠቅሞ የራሱን ሀሳብ፣ ስሜትና ውስጠት የሚገልጽበትና መልዕክት የሚያስተላልፍበት አንዱ መንገድ ነው። አሁን ላይ ማህበረሰቡ ስለንቅሳት ያለው አመለካከት ከዚህ የተሻለ ሁኔታ እያሳደገው መምጣት እንዳለበት ይጠቁማል።
ንቅሳትን በተለያዩ ዲዛይኖች የሚሰራ ሲሆን እንደየሰው ፍላጎት መሠረት ተደርጎ ይሰራል። ቀደም ሲል ንቅሳት ለመሥራት የስዕል ችሎታ ላለው ሰው ተነግሮ የሚሰራው ሰው የሚፈለገውን ዲዛይን እንዲሳልለት ተደርጎ ይሰራ እንደነበር አስታውሶ፤ አሁን ላይ ግን ቴክኖሎጂው ይህንን ሁሉ ችግር በመቅረፉ አንድ ሰው የሚፈልገውን የንቅሳት ሀሳብ ይዞ ይመጣል። ሀሳቡ በወረቀት ላይ ከታተመ በኋላ የሚፈልገው አይነት ከሆነ የሚነቀሰው እንደሆነ ነው የገለጸው።
ንቅሳት ሰዎች ውብ ሆነው እንዲታዩ የሚጠቀሙበት ስለሆነ የሚሰራው ሰው ክህሎት፣ ችሎታ እና ሙያው አድናቆትና ውስጣዊ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል። ይህ ሲሆን የሚሰራውን ሥራ ያቀላል፤ ደንበኞችም የሚፈልጉትን ያገኛሉ።
በተለይ በአሁን ወቅት አብዛኞቹ ሰዎች መነቀስ የሚፈልጉት እጃቸውና እግራቸው ላይ ሲሆን ወንዶች በአብዛኛውን ደረት ላይ፣ ሴቶች ደግሞ ጀርባ እና ትከሻዎቻቸው ላይ አብዝተው ይነቀሳሉ። አንድ ሰው በተፈጥሮው እንደ አለርጂ አይነት ነገር ካለበት ንቅሳት ሲነቀስ ጉዳት ሊኖረው እንደሚችልም ጠቁሟል።
አንድ ዲዛይን ለመሥራት እንደየሥራው ዲዛይን የሚወሰደው ጊዜ የተለያዩ መሆኑን ጠቅሶ፤ ዲዛይኑ ጥልቅ ከሆነ እስከ አራት ሰዓት ያህል ሊፈጅ እንደሚችል ወጣት አብነት ይናገራል። የንቅሳት ዋጋን በሚመለከትም ከ500 ብር ጀምሮ እስከ 15ሺ ብር የሚደርስ የዲዛይን ተመን ያለው ሲሆን ጥልቅና ውስብስብ የሆነ ዲዛይን ሲኖር ዋጋ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል አስረድቷል። ለንቅሳት የዋጋ ውድ መሆን ምክንያቱ የጥሬ እቃዎቹ ከውጭ የሚመጡ በመሆናቸው እንደሆነም አመላክቷል።
በንቅሳት ሥራ ላይ ተግዳሮት የሚሆነው ዶላር መጨመር ጥሬ እቃ እንዳናስገባ ያደርገናል የሚለው ወጣት አብነት፤ ሥራ ቢኖር እንኳን ጥሬ እቃ ከሌለ መሥራት አንችልም ይላል። የንቅሳት ሥራ በሰዎች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ የሆነ ሰዓት ሥራ ይኖራል የሆነ ሰዓት ደግሞ ሥራ ላይኖር ይችላል። ስለዚህ ሥራው የሚሰራው በቀጠሮ ሲሆን መሥራት የሚፈልግ ሰው ከመምጣቱ በፊት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ፕሮግራም አስይዞ ይሰራል።
ሰዎች ንቅሳት ፈልገው እንደሚሰሩት ሁሉ ባልፈለጉት ጊዜ ደግሞ ማጥፋት የሚችሉበት መንገድ ስለመኖሩ ያስረዳው ወጣት አብነት፤
በንቅሳት ሥራ ለሦስት ሰዎች የሥራ እድል መፍጠር የቻለው ወጣት አብነት፤ ንቅሳት ሰዎች ውስጣቸውን የሚገልጹበት እንጂ ‹‹ዱርዬ›› የሚል ግምት የሚያሰጣቸው እንዳልሆነ በመጥቀስ ሰው ውበትን በሚፈልገው መልኩ ሊገልጽ እንዲችል መፍቀድ አለብን የሚል አመለካከት አለው።
ወርቅነሽ ደምሰው
አዲስ ዘመን ሐምሌ 24/2015