የለውጡን ዋዜማ ጨምሮ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በበርካታ አከባቢዎች ለተከሰቱት ግጭቶችና መፈናቀሎች መነሻቸው ህብረተሰቡ እንዳልሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ገለጹ፡፡
ኃላፊው አቶ ንጉሱ ጥላሁን ትናንት በጽህፈት ቤቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፤ ባለፉት ጊዜያት በአገሪቱ የዜጎች መፈናቀል ቢከሰትም ህብረተሰቡ ለግጭትና መፈናቀል መነሻ እንዳልሆነ፣ ግጭቶችና መፈናቀሎች ሲከሰቱም ህብረተሰቡ እንደየባህሉ በመደጋገፍና በመረዳዳት የነበረውን እሴቱን ጠብቆ አቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበራዊ ሚዲያውና ሌሎች አካላት ለግጭቱ መስፋፋት ትልቅ ሚና ነበራቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ንጉሡ ማብራሪያ፤ በለውጡ ሂደት ውስጥ አንደኛው ዜጎች በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን በየትኛውም አካባቢ ሰርቶ የመኖር መብታቸውን ተጠቅመው ሰርተው እንዲኖሩ መንግስትም ይህንን መብታቸውን እንዲያስከብር ታሳቢ ተደርጎ ሲሰራ ቢቆይም፤ አሁንም ችግሩ ቀጥሏል፡፡
በዚህ ምክንያት በርካታ ዜጎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ በአገሪቷ በሁሉም አካባቢዎች ባጋጠሙት ግጭቶችና መፈናቀሎች የመንግስት ሰራተኛን ጨምሮ በመንግስት፣ በማኅበረሰቡና በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አማካኝነት ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በዚህ ውስጥ ህብረተሰቡ ለተፈናቃዮች ሲያደርግ የነበረው ድጋፍና ተሳትፎ ተስፋ የሚሰጥና የሚያኮራ ተግባር ነው፡፡ ይህም ከመጀመሪያውም ቢሆን ህብረተሰቡ ለግጭት ለመፈናቀል መነሻ እንዳልነበረ ማሳያ ነው፡፡
አቶ ንጉሡ ለዚህ ተልዕኮ የቆሙ ተከሰቱና ያልተከሰቱ የሚቀንስ ውጤታማ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራ ስታከናውኑ መንግስት ከጎናችሁ ሆኖ ይደግፋችኋል ብለዋል፡፡
በኢጣሊያን ጦርነት ዋዜማ ለጦር ቁስለኞች ሰብዓዊ እርዳታ በማድረግ ከ1927 ዓ.ም ማግስት ጀምሮ ላለፉት ስምንት አስርት ዓመታት ሰብዓዊ ድጋፍ እየሰጠ የሚገኘው አንጋፋው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአሁኑ ሰዓት ከ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን አባላትና ከአርባ ሺ በላይ በጎ ፈቃደኞች አሉት፡፡
ማህበሩ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ የአባላቱን ብዛት ከእጥፍ በላይ ለማሳደግና የበጎ ፈቃደኞቹን ቁጥርም ቢያንስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንዲሆኑ ለማድረግና በአፍሪካ በአባለቱ ብዛትም ሆነ በበጎ ፋቃደኞች ቁጥር ግንባር ቀደም ብሔራዊ ማህበር ለመሆን የሚያስችል የንቅናቄ ዕቅዱንም በበላይ ጠባቂው በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አማካኝነት በትናትናው ዕለት በይፋ አስጀምሯል፡፡
ነገሮችን በመደባለቅ የጥላቻና ቂም በቀል ሥራዎችን በማሰራጨት የበለጠ ግጭት እንዲከሰትና ህብረተሰቡ ስጋት እንዲያድርበት፣ ተስፋ እንዲቆርጥና አገር አደጋ ላይ እንድትወድቅ የማድረግ ሥራ በስፋት እየሰሩ በመሆናቸውን ችግሮቹን ማስወገድና የህግ የበላይነትን መረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን፤ ህግንና ስርዓትን ለማስከበር በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት በጥብቅ መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበው፤ መንግስትም በትኩረት እንደሚከታተለው ጠቁመዋል፡፡
ግጭቶች ከተከሰቱና መፈናቀል ካጋጠመ በኋላ የመንግስት ሚና ዜጎች ለበለጠ ጉዳት እንዳይዳረጉ ተፈናቅለው ባሉበት ቦታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ማድረግ ነው ያሉት ኃላፊው፤ የውሃ፣ የመጠለያና የመድሃኒት አቅርቦት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ መሰራቱን፤ በተለይም በቅርቡ የክረምቱ ወቅት የሚገባ በመሆኑ ያልተጠበቁ በሽታዎች ሊከሰቱ ስለሚችሉ መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ ዓለም አቀፍ የመድኃኒት ግዥ በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
አቶ ንጉሡ ተፈናቃዮች በቋሚነት ወደ ነበሩበት ቦታ ተመልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ማመቻቸትም ቀጣይ ተግባር መሆኑን ተናግረው፤ ለዚህም ከተፈናቃዮች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት እንደሚደረግ፣ወደቀድሞ ቦታቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ሲሆኑ ሊመለሱ እንደሚችሉ፤ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን መንግስት ባሉበት ቦታ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ህጻናት፣ እናቶችና አዛውንቶች ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የከፋ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያቀፈ አደረጃጀት ተመስርቶ ድጋፉን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ጥረት መደረጉን፤ በሁሉም አካባቢዎች በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስና ዜጎች በተረጋጋና በእንክብካቤ እንዲቆዩ ጥረት እንደሚደረግ አቶ ንጉሱ ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ከ875 ሺ በላይ ዜጎችን ወደነበሩበት ቦታ የመመለስ ሥራ መሠራቱን፤ ሕግን በማስከበር ሂደትም መፈናቀልን ያስከተሉ ከ2 ሺ 517 በላይ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት እንዲታይ የመለየት ሥራ መከናወኑንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም 1ሺ 300 ያህሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን አቶ ንጉሡ ጠቁመዋል፡፡
አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2011
በአዲሱ ገረመው