ብዙዎች ‹‹የመድረኳ ንግስት…..እቴጌ›› እያሉ ይጠሯታል። እርሷ የትኛውም አይነት ስም የሚበዛባት አይደለችም። ከዚህም ባሻገር ሌላ አንድ እውነታ አለ፤ እርሷ የጥበብ ሰው ብቻ ሳትሆን ፈጣሪ ጥበብ እንዳትጠፋ ሲል በውስጧ በክብር ያኖረባት እንቁ የጥበብ ሙዳይ ናት። የሙዚቃ ግጥም ደራሲ፣ የመድረክ ላይ ተዋናይ፣ የቴአትር ጸሐፊ፣ አዘጋጅ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች… ከቶ ማን እንበላት? እንቁ የጥበብ ሙዳይ ዓለምፀሐይ ወዳጆ!lingerie and sex toyscouples sex toys for womenbest male sex toyscouple sex toysbest couples sex toyssex toy storebest sex toys for menbest sex toy storebest sex toys for womensex toys for womensex toy storessex toy store onlinebest lesbian sex toyssex toys adam and evesex toys for womenvibrator sex toybest female sex toyamazon sex toysadult sex toyslovense sex toybest mens sex toycheap sex toyssex toy shopass sex toy for mansex toy storesbest sex toys for womenmost popular sex toyssex toys for lesbianssex toyswholesale sex toyssex toys storelong distance couples sex toysgay sex toystop male sex toysbest sex toys for womenbest male sex toysex toys and lingeriechina lesbian sex toyssex toys storebest cheap sex toys for mencouples sex toys
ገና የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሆና አቻዎቿ ከፊደላት ጋር ለመተዋወቅ በሚዳክሩበት እድሜ እርሷ ግን ተሻግራ ሄዳ ብቻዋን ቁጭ ብላ ከጥበብ ጋር ስታወጋ ነበር። በውስጧ የበቀለችው እንቡጥ ጥበብ በስነ ጽሁፍ እየዳበረች ከእድሜዋ እኩል ተመንድጋ ግዙፍ የጥበብ ዋርካ ሰራች። ከትወና እስከ ቴአትር ዝግጅት፣ ከሙዚቃ ግጥሞች እስከ ልዩ ድርሰቶች፣ ከብሔራዊ ቴአትር እስከ አሜሪካን ድረስ በልዩ የስነ ጥበብ ችሎታዋ እንደ ማለዳ ፀሐይ ፈክታ ታይታበታለች። በትወና ብቃቷም የተመልካቹን ቀልብ የምትሰልበው ዓለምፀሐይ ወዳጆ በሴት ተዋናይ ዘርፍ የመጨረሻውን ጫፍ መንካት የቻለች ናት ሲሉም ብዙዎች ለእርሷ ያላቸውን አድናቆት ይገልጹታል። የሴትነት ገመድ እልፍ ሴቶችን ከህልማቸው እየጎተተ ቁልቁል በሚጥልበት ሰዓት ተነስታ ሁሉንም እየተጋፈጠች የሞራልዋን ሃያልነትና የታላቅነቷን ጥግ ለማሳየት በቅታለች። አይሆንም አይቻልም የሚሉ ነገሮች ፈጽሞ እረፍት አይሰጧትም። ሁሉንም ፈተናዎቿን በድል ታጠናቅቃቸዋለች።
የጥበብ ፈርጧ ዓለምፀሐይ ወዳጆ ጥቅምት 9 ቀን 1948 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደች። ስትወለድ ብቻዋን አልነበረም፤ በዓይን የማይታይ በእናቷ ማህጸን ውስጥ ሳይሆን በእርሷ ልብ ውስጥ የተጸነሰ የጥበብ ዘር ነበር። ልጅነቷን ያሳለፈችው ከዚህ ጥበብ ጋር እየተጫወተች ነው። ይህች ዘር ከለም አፈር ውስጥ እንደወደቀች የስንዴ ዘር የልቧን ግድግዳ ሰንጥቃ የወጣችው በፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ውስጥ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ነበር። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከክበባት ጀምሮ የምታደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች የተመለከቱት መምህራኖቿ አንዳች እምቅ ኃይል ከውስጧ እንዳለ ተገንዝበው ነበር። የዓለምፀሐይን ጥበብ እየኮተኮቱ ፍሬውም ያማረ እሸት እንዲሆን አድርገውታል። በሀብተ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የነበራትን ቆይታ ካጠናቀቀች በኋላ ቀጣዩ ማረፊያዋ የመድሃኒዓለም ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር። የዓለምፀሐይ የስነ ጽሁፍ ችሎታ መጎምራቱን ያበሰረችበት የመጀመሪያው ልዩ አጋጣሚ ያገኘችው ከዚህ ትምህርት ቤት ነው።
በአንድ ወቅት በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ የስነ ጽሁፍ አርበኞች መካከል ውድድር ተካሄደ። ዓለምፀሐይ ወዳጆም ሁሉንም ጥላ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቀቀች። ከብዙዎች ፊት በኩራት ቆማም የመጀመሪያውን ብሔራዊ የጥበብ ኒሻን አጠለቀች። ጥሩ አጋጣሚና መልካም እድል ነበር።
የ12ኛ ክፍል ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ በውስጧ የተቀጣጠለውን የትወና ብቃት እንድታወጣ ይረዳት ዘንድ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ደጅ አቀናች። በዚያም በውስጡ ይሰጥ የነበረውን የ2 አመት የትወና ስልጠና ወሰደች። ከዚህ በኋላ ነበር እንግዲህ አቻ ያልተገኘላት የሴት ተዋናይ ሆና የቀጠለችው። መስራት የጀመረችውም ገና ከመመረቋ አንስቶ ነበር። በብሔራዊ ቴአትር መስራት ከጀመረች በኋላ ታዲያ ብሔራዊ ቴአትር ያለ እርሷ የማይደምቅ የማይሞቅ ሆነ። እንቁና ድንቅ ሆና ለበርካታ አመታት በብሔራዊ ቴአትር ውስጥ ነግሳለች። ባላት ነገር በቃኝ ብላ ጉዞዋን የማታቆም የትጋት ተምሳሌት በመሆኗ የሙያ ብቃቷን ለማዳበር ወደ ጀርመን፣ የሶቪየት ህብረት፣ ቡልጋሪያ እና ወደ ቼኮስላቪያ በማቅናት ብቁ የሚያደርጓትን የሙያ ስልጠናዎች ወስዳለች። በባህል ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የባለሙያዎች ምክር ቤት ዓለምፀሐይ ወዳጆን መሪ ተዋናይ አድርጎ ሰይሟታል።
ከምግባር እስከ ተግባር ሁሉን አድሎ የሰጣት ይህቺ የጥበብ ሙዳይ በውስጧ ከያዘቻቸው እንቁ ተሰጥኦዎቿ መካከል አንዱ የሙዚቃ ግጥም ድርሰቶቿ ናቸው። በዘመኑ እውቅና ተወዳጅ ከነበሩት ድምጻውያን መካከል የእርሷን ደጅ ያልጠና የለም ብሎ ለማለት ይቻላል። ከ50 በላይ ለሚሆኑ ድምጻውያን የሙዚቃ ግጥሞችን በመስራት አጃኢብ የሚያሰኙ ልዩ ስጦታዎችን አበርክታለች። ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሉቀን መለሰ፣አስቴር አወቀ፣ መልካሙ ተበጀ፣ ነጻነት መለሰ፣ ሂሩት በቀለ፣ ማህሙድ አህመድ፣ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ዳዊት መለሰ፣ ኩኩ ሰብስቤ፣ በዛወርቅ አስፋው፣ ፀሐዬ ዮሃንስ ኧረ ስንቱ ይጠቀሳል። ከእነዚህ መሃከል ለአንጋፋው ድምጻዊ የክብር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ የጻፈችው ‹‹ኢትዮጵያ›› የተሰኘው ሙዚቃ ዓለምፀሐይ የችሎታዋን ልክ ያሳየችበት ግሩም ድንቅ ስራ ነበር።
ከምትሰራቸው ስራዎች ባሻገር በርካታ ማህበራዊ በሆኑ ነገሮች ላይ የነበራት ተሳትፎ እጅግ የላቀ ነው። ሙያዋ ሲደፈርም ሆነ ሲነካ አትወድም። ዓለምፀሐይ በሙያዋ ለመጣባት ልክ እንደ አራስ ነብር ናት። ለሙያው ብቻ ሳይሆን በሙያው ዙሪያ ላሉ ሰዎች መብት መከበር ፊት ለፊት ትጋፈጣለች። ፈጽሞ በደልን ተመልክታ ለማለፍ አትችልም። ምናልባትም ከፖለቲካው ጋር በግንባር ያጋጫት አንደኛው ምክንያት ይሄው ባህሪዋ ነው። በተለያዩ ጊዜያትም ልዩ ልዩ ማህበራትን ለማቋቋም ትግል አድርጋለች። እንዲቋቋም ካደረገቻቸው መካከል አንደኛው የተውኔት ሙያተኞች ማህበር ነው። ማህበሩ ከክፍያ ጀምሮ የተዋንያኑን ጥቅምና መብት ለማስከበር ችሏል። በኢትዮጵያ ውስጥ ዓለም አቀፉ የቴአትር ቀን እንዲከበር ያደረገችው ዓለምፀሐይ ወዳጆ ናት። እርሷ ጋር የነበረው የጥበብ ብርሃን በትውልዱ ሁሉ ይበራ ዘንድ ምኞቷ ነበርና በሳምንት ለሁለት ቀናት ወደ ህጻናት አምባ ጎራ እየሄደች ህጻናቱን ታስተምር ነበር።
ዓለምፀሐይ ወዳጆ በጥበብ ሥራዎቿ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዋም ትታወቃለች። ፖለቲካው በሕዝቡ ላይ የሚጭነውን ቀንበር አሜን ብሎ ለመቀበል ውስጧ አይፈቅድላትም። ሁሉንም ነገር እንደ አመጣጡ ከመጋፈጥ ወደኋላ ብሎ ነገር አታውቅበትም። በደርግ ዘመን በነበረው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከትምህርት ቤት ጀምሮ የተማሪዎች መሪ ነበረች። የተማሪዎች የመብት ጥያቄና አመጽ ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል አንዷና ዋነኛዋ ዓለምፀሐይ ወዳጆ ናት። በወቅቱ ትሰራበት የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ባለሙያዎች አንድ ትልቅ ጥያቄ ነበራቸው። ‹‹በመንግስት ስር ሆነን ደሞዛችንም በመንግስት ይከፈለን አሊያም የሰራተኞች ማህበር ይጠቅልለን›› የሚል የመብት ጥያቄ ይዘው መንግስትን በማስፈቀድ ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ። በእለቱ ሰልፉን ተገን በማድረግም ኢህአፓ ውስጥ ለውስጥ እየገባ ወረቀት መበተን ጀመረ። በከተማው ውስጥም ሌላ ትርምስ ተፈጠረ። በወቅቱ ዓለምፀሐይ አያቷ አርፈው ሃዘን ላይ የነበረች ቢሆንም መንግስት ይህን ሴራ የጠነሰሱት እነ ዓለምፀሐይ ናቸው በሚል ይፈልጋት ጀመር። በዚህን ሰዓት ታዲያ እንዳትታወቅ እራሷን ወደ ባላገር ሴትነት ቀይራ ለስድስት ወራት ሌላ ሰው መስላ ነበር ያሳለፈችው። አንድ ቀን ግን ታማ ግዴታ ሆስፒታል መሄድ ስለነበረባት ወደዚያው አመራች። ከሆስፒታሉ ውስጥ ድንገት ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ፊት ለፊት ተገናኝታ ቢጠሯት ጊዜ ዓለምፀሐይ አይደለሁም በማለት እራሷን ስለመካድዋ ታስታውሳለች። ዓለምፀሐይ ወዳጆ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አያስፈልግም ብላ ባመነችባቸው ጉዳዮች የነበራት ትግል የሚበርድ አልነበረም። በውስጧ የነበረው ግለት በኢህዴግ መንግስትም አልበረደም። የዚህን ጊዜ ግን ተሸሽጋም የማታመልጠው ነበርና የስደትን ዳና ተከትሎ መሄድ የግድ ሆነባት። ሆድ እየባሳት የብሔራዊ ቴአትርን ደጅ በናፍቆት ተሰናብታው ጉዞዋን ጀመረች።
ዓለምፀሐይ ኑሮዋን በአሜሪካን ካደረገች በኋላ ለአፍታም ቢሆን ከጥበብ መንገድ ለመራቅ አልቻለችም። ምናልባትም ለኑሮዋ ምቾችን ሊያስገኙላት የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ በመተው ሁለተናዋን ለጥበብ መገበርን መርጣለች። በውስጧ እየተንቀለቀሉ እረፍትን የማይሰጧትን የጥበብ ሃሳቦች በመከተል ያልሞከረችው ነገር አልነበረም። ጋዜጣ እያሳተሙ ማሰራጨት፣ የኪነ ጥበብ ምሽት ማዘጋጀት፣ የተለያዩ ማህበራትን ማቋቋም በሁሉም ላይ ያላትን አቅም በሙሉ በማሟጠጥ ሃሳቧን ከግብ ለማድረስ ትግል አድርጋለች። ጥበብ መክና እንዳትቀር ካላት የተለየ ጉጉት የተነሳ መጽሐፍ የማሳተም አቅሙ እያላቸው ነገር ግን በገንዘብና በተለያዩ ምክንያቶች ለማሳተም ያልቻሉትን ጸሐፊያን ሌሎችን በማስተባበር ህልማቸውን እውን አድርጋለች። በዚህም ሶስት መጽሐፎች ለመታተም በቅተዋል። ከሰራቻቸው ትልልቅ ሥራዎች መካከል አንዱ በሀገረ አሜሪካን ምድር ‹‹ጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል›› የተሰኘ የኪነ ጥበባት ማዕከል ማቋቆም መቻሏ ነው። በርካታ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን እንዲሁም የጥበብ ሰዎችን ወደ አንድ የጥበብ ማዕድ አሰባስባለች። ለ27 አመታት ያህልም ኑሮዋን ከዚያው በማድረግ ቆይታለች። እንቁዋ የጥበብ ሴት ከዚህ ሁሉ በኋላ የናፈቃትን የሀገርዋን አፈር ለመርገጥ የበቃችው ከጥቂት አመታት በፊት ነበር። የፖለቲካ እስረኛ ሆነው በውጭ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ የተደረገው የምህረት አዋጅ ለእርሷም ጥሩ አጋጣሚን ፈጥሮላታል። ወደ ሀገሯ በገባችበት ወቅትም የቀድሞ የሙያ አጋሯቿ ጨምሮ በብሔራዊ ቴአትር ሞቅ ደመቅ ባለ ዝግጅት አቀባበል አድርገውላታል። በዚህ ዝግጅት ላይ ዓለምፀሐይ ንግግር ለማድረግ ከመድረኩ ላይ ወጣች። ዳግም ሀገሯን ለማየት በመብቃቷና በነበረው የፍቅር አቀባበል የደስታ ሲቃ እየተናነቃት ‹‹ቀድሞም ቢሆን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊ ተስፋ ቆርጬ አላውቅም ነበር›› ስትል ውስጧ የነበረውን የተስፋ እምነት ትክክል መሆኑን አረጋገጠች። ረዥም እድሜን ከጤና ጋር ለእንቁዋ የጥበብ ሙዳይ።
ሙሉጌታ ብርሃኑ
አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2015